ቀይ ቀበሮዎች የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ውበት ናቸው፤

በባሌ ተራሮች -ድብቅ ዓለም

 ቀይ ቀበሮዎች የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ውበት ናቸው፤

 

 Image result for በባሌ ተራሮች -ድብቅ ዓለም

አሁን ወደ አስጎብኛችን አቶ ሙስጠፋ ልመልሳችሁ፡፡ የባሌ ተራሮች ከፍተኛ አካባቢዎች በተለያዩ መንገድ የተፈጠሩ ሀይቆች፣ እርጥበት አዘል መሬቶች፣ የእሳተ ጎሞራ ቅሪቶችን አቅፎ መያዙን አቶ ሙስጠፋ ይናገራሉ፡፡__ፓርኩን ልዩ የሚያደርገው ሌላው ነገር በኢትዮጵያ ትልቁና ወደ ሰባት ሺ ኪሎ ሜትር ስኩዬር የሚሸፍነው «የሐረና ደን» በውስጡ በመገኘቱ ነው፡፡ _ከነዚህም ውስጥ አንድ ሺ ኪሎ ሜትር ስኩዬር የሚሸፍነው በብሔራዊ ፓርኩ ውስጥ ሲገኝ የተቀረው ስድስት ሺ ኪሎ ሜትር ስኩዬሩ ደግሞ በኦሮሚያ ክልል የደንና ዱር እንስሳት ኢንተርፕራይዝ ይተዳደራል፡፡

የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት ጊዜያዊ መዝገብ ውስጥ ተካቷል፡፡ ከ1ሺ 600 በላይ ልዩ ልዩ ዓይነት ዕፅዋት፣ 78 ዓይነት አጥቢ የዱር እንስሳትና ወደ 200 የሚጠጉ አዕዋፋት በፓርኩ ተጠልለው ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም መካከል 32 ዓይነት ዕፅዋት፣ 31 የሚጠጉ ብርቅዬና ድንቅዬ የዱር እንስሳትና ስድስት ዕፅዋት በብሔራዊ ፓርኩ ካልሆነ በስተቀር በሌላው ዓለም ፈጽሞ አለመገኘታቸውን አቶ ሙስጠፋ አጫወቱን፡፡

በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ክልል ውስጥ ከሚገኙ 78 የሚደርሱ አጥቢ የዱር እንሰሳት 17ቱ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ብርቅዬ እንስሳት ናቸው፡፡_ከዚህ ባሻገር ለሳይንስና ኢኮሎጂ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው በደረታቸው የሚሳቡ ልዩ ልዩ እንስሳትን ፓርኩ አቅፎ ይዟል፡፡ ልዩ ጣዕም ያለው የጫካ ቡናና በሀገራችን ለባህል መድኃኒትነት ከሚውሉ እፅዋት 40 ከመቶው ይገኙበታል፡፡

በእፅዋት እና በእንስሳት ብዝሃ ህይወት መበልፀግ ደረጃ ፓርኩ ከዓለም 34ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 12ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡን ስንሰማ ይበልጥ ኩራት ተሰማን፡፡ የዓለም አቀፍ የወፎች ድርጅት የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን የአፍሪካ አራተኛው «በርዲንግ ሳይት» ብሎ መዝግቦታል፡፡ በተጨማሪም በ “Bird lite International” በአለም ከሚገኙ አስፈላጊ የአዕዋፍ መኖሪያ ቦታዎች አንዱ ሲል መስክሮለታል፡፡ በፓርኩ ከ280 በላይ የአዕዋፍ ዝርያዎች የሚኖሩ ሲሆን ሰባቱ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ መሆናቸው ደግሞ ፓርኩን ልዩ አድርጎታል፡፡

በባሌ ብሔራዊ ፓርክ ዋቢ ሸበሌ፣ ዌብ፣ ዱማል፣ ያዶት እና ወልመል የተሰኙ ወንዞች ይፈሱበታል፡፡በፓርኩ ውስጥ ከሚገኙ የዱር እንስሳት መካከል ቀይ ቀበሮ፣ ኒያላ፣ አጋዘን እና ሌሎችም ይጠቀሳሉ፡፡ ባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን አስቃኝቼ በውስጡ ሥለሚገኙት ብርቅየ እንስሳት አለማውራት ተገቢ አልነበረምና ጥያቄየን ወደ አስጎብኛችን አቶ ሙስጠፋ ሰነዘርኩ፡፡ እርሳቸውም በደስታ አብራሩልኝ፡፡ ለቀይ ቀበሮ ልዩ ፍቅር ነበራቸውና ከእርሷ ጀመሩ፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ ቀበሮ አኗኗር በመንጋ ነው፡፡ አንድ መንጋ ከ3እስከ13 አባላት ሊኖሩት ይችላል፡፡እያንዳንዱ መንጋ የራሱ የመኖሪያ አካባቢ ሲኖረው የአካባቢውን ድንበር ወንድ ቀይ ቀበሮዎች ያስከብሩታል፡፡ በርቢ ወቅት ሴት ቀይ ቀበሮ ከመንጋው አባላት ወንዶች ውጪ ግንኙነት ማድረግ አይፈቀድለትም፡፡ ከመንጋው አባላትም ጠንካራው ወንድ ከሴቶች ጋር ግንኙነት በማድረግ የተሻለ እድል እንዳለው ነው የሚገለጸው፡፡ የኢትዮጵያ ቀይ ቀበሮ ከማህበራዊ አኗኗራቸው ባሻገር በጠንካራ አዳኝነታቸው ጭምር እንደሚታወቁ አብራሩልን፡፡

ምንጭ ፡- ሪፖርተር ጋዜጣ