ቀለል ያለ እስታይል ይመቸኛል፡፡

አርቲስት እፀህይወት አበበ

 

 

Image result for beautiful ethiopian actress

 

ቀለል ያለ እስታይል ይመቸኛል፡፡

ተወልዳ ያደገች  አዲስ አበባ ነዉ፡፡ የምትኖረዉ  ፒያሳ ጣልያን ሰፈር ሲሆን በሙያዋ ሞዴልና የፊልም አክተር ነች፡፡የሰራቻቸዉ ያልወጡ  ፊልሞችን ጨምሮ በዉበት ለፈተና፤ቤርሙዳ፤ በአዳም ፊልሞች ላይ ሰርታለች፡፡

በርካታ የፊልም እስክሪብቶች መተዉላታል፡፡ ቤርሙዳ ግን እስክሪብቱ ለሷ የተለየ  ነበር ፡፡ ሀሳቡ የተለየ በመሆኑ ሀሳቡን በጣም ወዳዉ ነበር የሰራችዉ ፡፡ ዳይሬክተሩ አነጋገረኝ ተደራድረን ሰራሁት፡፡ክፍያዉ ግን ሚስጥር ነበር

ባህሪዋ አልቃሻ ነች ሲከፋት ታለቅሳለች፡፡ አሳዛኝ ፊልሞች ሳይ፤ አሳዛኝ የሰዉ ታሪክ፤ መጽሀፍትም ውስጥ የሚያሳዝን ነገር ሲገጥማት ታለቅሳለች፡፡  አስተዳጓ ለቤተሰቦቿ የመጀመሪያ ልጅ ነች ያደገችዉ  ከአያቶቼ ጋር ነዉ፡፡ ሞዴልግ መስራት የጀመረችዉ በልጅነቷ የመስራት ጉጉት ነበራት  እና ትምህርቱን ቅዳሜ  እሁድ ተምራ ጀመረች፡፡ ለመጀመሪያ የሰራችበት መድረክ መዘጋጃ ቤት በ1997 ነበር፡፡  ቀለል ያለ እስታይል ይመቸኛል በተለይ ሹርባ ትወዳለች፡፡ የሚያዝናናት ነገር  ሆረር እና ሰስፔንስ ፊልም ማየት  የእግር ገዞ ማየት እና ወክ ማድረግ ያዝናናታል፡፡ ትዳር መስርታለች በአሁኑ ግዜ የሁለት ልጆች እናት ነች፡፡ እና በተለያዩ የቴሌቭዥን ድራማዎችን በመስራት ላይ ነች፡፡

ምንጭ፡- ፋሽን መጽሄት

 

  

Related Topics