የሆድ ህመም የተለመደ እና ምናልባትም በተደጋጋሚ የሚከሰት ችግር ሊሆን ይ

የሆድ ህመምን ለማከም እንዲህ ቢያደርጉስ!

 

 

የሆድ ህመም የተለመደ እና ምናልባትም በተደጋጋሚ የሚከሰት ችግር ሊሆን ይችላል።

ውጋት፣ የሆድ ቁርጠት፣ የሆድ መነፋት፣ ማቅለሽለሽ በተደጋጋሚ የሚከሰቱ የሆድ ህመም ችግሮች ናቸው።

ይህን ተከትሎም ምቾት የማጣት፣ የማስመለስ፣ ማቃጠል፣ አብዝቶ ማግሳት፣ የማስጨነቅ እና የማስቀመጥ ችግር ሊከሰት ይችላል።

ከምግብ አለመፈጨት፣ አብዝቶ ከመመገብ፣ ያልታወቀ የሆድ ውስጥ ቁስለት እንዲሁም የወተት ተዋጽኦን በአንድ ጊዜ ከልክ በላይ መጠቀም ለዚህ ችግር መንስኤ እንደሆኑም ይነገራል።

በዚህም ሆነ በሌሎች ተዛማጅ ችግሮች የሚከሰትን የሆድ ውስጥ ህመም ደግሞ ቤት ውስጥ በሚዘጋጁ ውህዶች ማከም ይቻላል።

ዝንጅብል፦ አንድ መካከለኛ ይዘት ያለውን ዝንጅብል አጥቦ በአግድሞሽ በስሱ መቆራረጥ።  ከዚያም አንድ ኩባያ ውሃ ማፍላትና የተዘጋጀውን ዝንጅብል የፈላው ውሃ ውስጥ ጨምሮ ለሶስት ደቂቃ ያክል ማቆየት።በድጋሚ ለአምስት ደቂቃ እሳት ላይ አቆይቶም ማውጣት እና ውህዱን መጠጣት፤ ይህንን በቀን ሁለት ወይም ሶስት ጊዜ ያክል መጠጣት።ቤኪንግ ሶዳ እና ሎሚ፦ አንድ ተለቅ ያለ ሎሚ፣ አንድ የሾርባ ማንኪያ ቤኪንግ ሶዳ፣ ሩብ የሻይ ማንኪያ የገበታ ጨው እንዲሁም አንድ ኩባያ ውሃ።

ከዚያም ሎሚውን ውሃው ውስጥ መጭመቅ እና ቤኪንግ ሶዳውንና የገበታ ጨውን ቀላቅሎ ማዋሃድ።

ይህንንም ከህመሙ እስከሚፈወሱ ድረስ በቀን ለሶስት ጊዜ ያክል ማድረግ።

ቁንዶ በርበሬ፦ አንድ የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬን በአንድ ተለቅ ባለ የሻይ ብርጭቆ ውሃ ለ10 ደቂቃ ያክል ማፍላት።

ከዚያም ትንሽ ቀዝቀዝ ማድረግና ጥቂት ማር በመጨመር ቀስ እያሉ መጠጣት።

የሩዝ ውሃ፦ በአንድ ተኩል ብርጭቆ ሩዝን በመስፈር አጥቦ ማዘጋጀት።

ከዚያም ስድስት የሻይ ብርጭቆ ውሃ ማፍላትና ሩዙን መጨመር።

ሩዙን ሳይከድኑ እንዲበስል ማድረግ እና ሩዙ ሲበስል እና ውሃው መጥለል ሲጀምር አንድ ተኩል የሻይ ማንኪያ ንጹህ ማር መጨመር።

ከዚያም ውሃውን አጥልሎ በቀን ሁለት ጊዜ መጠጣት።የውሃና የሎሚ ውህድ፦ አንድ ተለቅ ያለ መጠን ያለውን ሎሚ በአንድ ብርጭቆ ውሃ በማዋሃድ ቢችሉ በቀን እስከ ሶስት ጊዜ ያክል መጠጣት።

እርጎን ትንሽ ጨው አድርጎ አንድ ሁለት የሾርባ ማንኪያ ውሃ በመቀላቀል መጠቀምም ለዚህ ችግር መፍትሄ ነው።

 

Source: FBC

 

 

  

Related Topics