ካንሰር አደገኛና እስከሞት ድረስ ሊያደርስ የሚችል በሽታ እንደሆነ ይታወ

በካንሰር የመያዝ ዕድልዎን ለመቀነስ ምን ማድረግ አለብዎት?

 

 

ካንሰር አደገኛና እስከሞት ድረስ ሊያደርስ የሚችል በሽታ እንደሆነ ይታወቃል።

 

ካንሰር በተለያዩ አይነት ምክንያቶች ሊነሳ ይችላል። ካንሰር እንዳይነሳብን እድሉን ለማጥበብ ማድረግ የምንችላቸው ነገሮች ቢኖሩም እንደማይዘን 100% የሚያረጋግጥልን መፍትሄ የለም።

 

ለማንኛውም በካንሰር የመያዝ ዕድልን ለመቀነስ አብዛኞቹ ባለሙያዎች የሚስማሙበት የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል ነው በሚል ነው።

 

ስለዚህ በካንሰር የመያዝ ዕድላችንን ለመቀነስ እነዚህ ልንከተላቸው የሚገባቸው ቀላል የአኗኗር ዘይቤዎች ምን ይመስላሉ።

 

1) ከትንባሆ መራቅ:-

 

ይህ አለማጨስ፣ ትንባሆ አለማኘክ ወይም ደግሞ የሚጨስበት አካባቢ አለመሆንን ያካትታል።

 

ማጨስ ከብዙ አይነት የካንሰር አይነቶች ጋር ግንኙነት እንዳለው መረጃዎች ያሳያሉ። ከነዚህ ውስጥ በገዳይነቱ በጣም የሚታወቀው የሳምባ ካንሰር ነው።

 

ትንባሆ ማኘክም እንደዚሁ በተለይ ለአፍ ካንሰር እንደሚዳርግ መረጃዎች ያሳያሉ።

 

ሲጋራ የሚጨስበት አካባቢ መሆንም በሳንባና በሌሎች አይነት ካንሰሮችም የመያዝ እድልን ይጨምራል ተብሎ ይታሰባል

 

2) ጤነኛ የአመጋገብ ዘይቤን መከተል:-

 

ጤነኛ የአመጋገብ ዘይቤን መከተል በጠቅላላው በካንሰር እንዳንያዝ አስተዋጽኦ አለው ተብሎ ይታመናል።

 

ጥሩ የአመጋገብ ዘይቤ

 

- ጠቅላላ አመጋገብን በአትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ጥራጥሬ እና እህላ እህሎች የተመሰረተ ማድረግ(ለውዝ ሳይበዛ ጥሩ ነው)

 

- ከመጠን በላይ አለመወፈር ወይም የሚያወፍሩ ምግቦችን አለማዘውተር

 

- አልኮሆል(የሚያሰክሩ መጠጦች) የሚጠቀሙ ከሆን በልኩ መጠቀምን ያካትታል።

 

3) ዘወትር እንቅስቃሴ ማድረግ:-

 

እንቅስቃሴ ማድረግ ጤነኛ የክብደት መጠን እንዲኖረን ከሚያደርገው አስተዋጽኦ አልፎ እሱ እራሱ እንደ ጡት ካንሰር እና ሌሎች አንዳንድ የካንሰር አይነቶች እንዳይነሱ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ይታመናል።

 

4) እንደ hepatitis B እና HPV ላሉ በሽታዎች ከተቻለ ክትባት መውሰድ:-

 

Hepetitis B የጉበት ካንሰር እንዲነሳብን እስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ይታመናል። HPV ደግሞ የብልት ካንሰርና ኪንታሮት እንዲነሳ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ይታመናል። ስለዚህ ከተቻለ በተለይ አኗኗሮ ለነዚህ በሽታዎች ተጋላጭ የሚያደርግ አይነት ከሆነ አስቀድሞ ክትባት መውሰድ ካንሰርን ከመከላከያ መፍትሄዎች አንዱ ነው ተብሎ ይታሰባል።

 

5) ከአንዳንድ አደገኛ ባህሪይዎች መቆጠብ፡-

 

ለምሳሌ የግብረስጋ ግንኙነት ሲያደርጉ ወይ መቆጠብ ወይ መጠቀም። ምክንያቱም እንደ HIV እና HPV አይነት ጥንቃቄ ከጎደለው የግብረስጋ ግንኙነት ሊከሰቱ የሚችሉ በሽታዎች ለ ብልት፣ ጉበት፣ ሳንባ ካንሰርና ለኪንታሮት ተጋጭለታችንን ያሰፋሉ ተብሎ ይታመናል።

 

ሌላም ደግሞ መርፌን አለመጋራት ከጥንቃቄዎቹ አንዱ ነው።

 

6) regular checkup (ተለምዶአዊ የጤነት ክትትል) ማድረግ:-

 

በዓመት ወይ በሁለት ዓመት አንዴ ጠቅላላ የጤነት ምርመራ(ካንሰርንም ሊያጋልጥ የሚችል) ቢደረግ አንዳንድ እንደጡት ካንሰር አይነት የካንሰር አይነቶች በእንጭጭነታቸው ከታወቁ ሙሉ በሙሉ የመዳን ወይም ሳይከሰቱም የመክሸፍ እድላቸው እጅግ ከፍተኛ ስለሆነ regular checkup ካንሰር እንዳይከሰት ወይም ሳይሰራጭ እንዲቀጭና እንዲድን እጅግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መፍትሄ ነው።

Source: tekamii.blogspot

 

 

  

Related Topics