የቴክኖሎጅ ጠበብት ኢንጅነሮች ኦክቶፐስን በተንቀሳቃሽ ማሽን (ሮቦት) መል

በአየር የተሞላው ኦክቶፐሱ ሮቦት

 

በአየር የተሞላው ኦክቶፐሱ ሮቦት

 

የቴክኖሎጅ ጠበብት ኢንጅነሮች ኦክቶፐስን በተንቀሳቃሽ ማሽን (ሮቦት) መልክ ስለመስራታቸው እየተናገሩ ነው።

ባለሙያዎቹ እንደሚሉት የባህር እንስሳውን ባለ ስድስት እግር ተሳቢ በሮቦት መልክ እጅግ አነስተኛ በሆነ መጠን ሰርተውታል።

ኦክቶቦት የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ ሮቦት ግን በተገጠሙለት ብረታ ብረት መሳሪያዎች የሚንቀሳቀስ ሳይሆን በአየር የሚሞላ እና በዝግታ የሚንቀሳቀስ ተሳቢ ነው።

ሲልከን ከተባለው ንጥረ ነገር ፈሳሽ ውህድ የተሰራው “ለስላሳው ኦክቶቦት” ለመንቀሳቀስ የፋብሪካ ውጤት ባትሪ ወይም ኤሌክትሪክ ሲስተምን አይጠቀምም።

ከዛ ይልቅ ወደ እግሮቹ በሚገባው አየር አማካኝነት በዝግታም ቢሆን መንቀሳቀስ የሚችልበትን እድል ያገኛል ነው ያሉት።

ተመራማሪዎቹ ከሲልከን ፈሳሽ ለተሰራው ሮቦት ልብ ለመስራት ኤሌክትሪክ ሳይሆን፥ እንደ ልብ የሚያገለግለውን ፈሳሽ ተጠቅመዋል።

ከዝልግልግ ፈሳሽ የተሰሩት ልቦቹ ጫፍ እና ጫፍ ትንሽ ወፈር ያሉት ክፍሎች ደግሞ አየር ወደ ሰውነቱ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ እንዲንቀሳቀስ ያደርጉታል።

ለዚህ ሂደት እንዲረዳው ደግሞ፥ በሃይድሮጅን ፐር ኦክሳይድ የተሞላ አነስተኛ ህዋስ ተሰርቶለታል።

መንቀሳቀስ ሲጀምር የመንከባለል አይነት አካሄድን የሚከተለው ኦክቶቦት፥ በሂደት ስምንት እግሮቹን (ካለው ስምንት እግር ውስጥ ስድስቱን እንደ እግሮቹ ሁለቱን ደግሞ እንደ እጅ ነው የሚጠቀምባቸው) በመጠቀም ይንቀሳቀሳል።

የአሁኑ ግኝትም ባለሙያዎቹ በዘርፉ ከዚህ ቀደም ከሰሯቸው ሮቦቶች የተለየ እና ምናልባትም ለሰው ልጆች አዲስ ምልከታን የሚፈጥር ነው ተብሏል።

ምናልባትም አንድ ቀን የሰ ልጅ የተለየ እርዳታን በሚፈልግባቸው የህክምና ስራዎች እና የተለዩ ተልዕኮዎች ላይ የመሰል ሮቦቶች እርዳታ ቢያስፈልገው ግኝቱ ተስፋን የሰነቀ መሆኑ ነው የሚነገረው።

ከሰውነት አንጻር ስስ ለሆነው የሰው ልጅ፥ በህክምናው ዘርፍ ተመሳሳይ ለስላሳ ሮቦቶችን መጠቀሙ አስተማማኝ እና ደህንነትን የሚፈጥር ነው ይሉል በስራው የተሳተፉት የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪው ሪያን ትሮቢ።

እናም ይህ ተጣጣፊና ለስላሳ ኦክቶቦት በርካታ የምስራች ይኖረዋል ሲሉም ተስፋቸውን ይገልጻሉ።

በፈሳሽ የተሞላው እና በአየር የሚንቀሳቀሰው ኦክቶቦት የሰው ለጅ ቀለል ያሉ ነገሮችን ለመስራት ላቀደበት የወደ ፊት እቅድም አንድ እርምጃን የሄደ ተብሎለታል።

ምንጭ-ኤፍ.ቢ.ሲ

 

  

Related Topics