ቶርኔዶ በተፈጥሮ ውስጥ ከሚታዩ ነውጠኛ አደጋዎች አንዱ ነው፡፡

ቶርኔዶ/ነውጠኛ አውሎ ንፋስ

 

 

ቶርኔዶ በተፈጥሮ ውስጥ ከሚታዩ ነውጠኛ አደጋዎች አንዱ ነው፡፡ ቶርኔዶ ከፍተኛ ፍጥነት በመሽከርከር ከመሬት እስከ ሰማይ ደመናዎች በሚዘረጋ ትቦ መሳይ ቅርፅ የሚፈጠር ነውጥ ሲሆን አንድን አካባቢ በሰከንዶች ውስጥ አመሰቃቅሎ ድምጥማጡን ሊያጠፋ ይችላል፡፡ በዚህ ትቦ መሳይ ቅርፅ ዙሪያ የሚሽከረከረው ከፍተኛ የንፋስ ፍጥነትም በሰዓት ከ480 ኪ.ሜ በላይ የሚፈጥን ነው፡፡ ይህ ከመሬት ወደ ሰማይ ደመናዎች የሚዘረጋው ትቦ መሳይ ቅርፅ ቁመቱ እስከ 80 ኪ.ሜ የሚደርስ ሲሆን የግርጌው ስፋትም እስከ 1.6 ኪሎ ሜትር ሊደርስ ይችላል፡፡ አብዛኛዎቹ ቶርኔዶዎች በአይን በቀጥታ ይታያሉ፡፡ አልፎ አልፎ ግን ቶርኔዶዎች በጣም በፍጥነት ከየት መጡ ሳይባሉ ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ እንዲህ ያለው ሲገጥም ቅድመ ዝግጅት እንኳን ማድረግ አይቻልም፡፡
==የቶርኔዶ አደጋ ጠቋሚዎች==
• በአካባቢያችን የቶርኔዶ አደጋ ብዙ ጊዜ የሚከሰት ከሆነ፣ በአካባቢው የሚነፍስ ንፋስ ሙሉ በሙሉ በመቆም ፀጥ ካለ የቶርኔዶን መምጣት አመላካች ሊሆን ይችላል፡፡ 
• በሰማይ ላይ ተንጠልጥሎ ቁልቁል የሚመለከት ተለይቶ ያለ ደመናም የቶርኔዶን መምጣት ሊያመላክት ይችላል፡፡
==የቶርኔዶ እውነታዎች==
• ቶርኔዶ ያለምንም ማስጠንቀቂያ በድንገት እና በፍጥነት ሊከሰት ይችላል፡፡ 
• አቧራና ቆሻሻ ከመሬት በመነሳት ትልቅ ትቦ መሳይ ቅርፅ ያለው በፍጥነት የሚሽከረከር ከሆነ ወደ ቶርኔዶ ሊያድግ ስለሚችል ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡
• ቶርኔዶ አቧራው እስኪያስነሳ ድረስ በዐይናችን ላናየው እንችላለን፡፡
• ቶርኔዶ በማንኛውም አቅጣጫ ሊጓዝ ይችላል፡፡ 
• አብዛኛው ቶርኔዶ ወደ ፊት የሚጓዝበት ፍጥነት መጠን 48 ኪ.ሜ በሰዓት ነው፡፡ ነገር ግን በሰዓት እስከ 112 ኪ.ሜ ድረስ ሊፈጥን ይችላል፡፡ 
• ቶርኔዶዎች ሄሪኬንን ተከትለው ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ 
• ቶርኔዶ በማንውም ሰዓት ሊከሰት ይችላል፡፡
==ቅድመ ጥንቃቄዎች==
• ያልተለመዱ የአየር መለዋወጦችን በንቃት መከታተል፡፡ 
• ውርጭ የቀላቀለ ከፍተኛ ንፋስ ካለና በተለይ ወደ እኛ እየቀረበ የሚመጣ ከሆነ ልንርቀው ይገባል፡፡ 
• የጠቆረ ወይም ወደ አረንጓዴነት ያደላ ሰማይ ካላ መጠንቀቅ አለብን፡፡
• በሰማይ ላይ ለብቻው ተነጥሎ ጠቁሮ የተከማቸ ደመና ካለና በተለይ ደግሞ ደመናው ባለበት የሚሽከረከር ከሆነ ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡ 
• እንደ እቃ ጫኝ ባቡሮች ከባድ ድምፅ ያለው ንፋስ ከሆነ በፍጥነት ወደ መጠለያዎች መሄድ አለብን፡፡ 
• በመኖሪያ ቤታችን ፣በአነስተኛ ህንፃ፣ በትምህርት ቤት፣ በሆስፒታል፣ በፋብሪካ እና በሱቆች ውስጥ ከሆንን በፍጥነት ወደ ምድር ቤቶች ልንሄድ ይገባል፡፡ የምድር ቤቶች ከሌሉ ደግሞ በሮችን እና መስኮቶችን ዘግተን በምንገኝበት ክፍል ውስጥ መሃከል ላይ መሆን አለብን፡፡ 
• በመኪናዎች እና ተንቀሳቃሽ ቤቶች ውስጥ ከሆንን ደግሞ በፍጥነት ጥለን በመውጣት ወደ ተሻሉ መጠለያዎች መገስገስ አለብን፡፡ 
• በገላጣ ቦታዎች ያለምንም መጠለያ የምንገኝ ከሆነ ጭንቅላታችንን በእጃችን በመሸፈን ከአከባቢው ዝቅተኛ የሆኑ ቦታዎች ላይ ተለጥፈን መተኛት አለብን፡፡ 
• በድልድዮች ስር መግባት የለብንም፡፡ 
• ቶርኔዶን በሩጫ ለማምለጥ መሞከር የለብንም፤ የሚያዋጣን መጠለያ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን መጠቀም ነው፡፡ 
• አብዛኛውን ጊዜ በቶርኔዶ ከሚደርሱ አደጋዎች መካከል አደገኞቹ ንፋሱ ያነሳቸው የተለያዩ ቁሳቁሶች እረጅም እርቀቶችን ወደ ላይ በመወርወርና ተመልሰውም ወደ መሬት በመውደቅ የሚያደርሱት ጉዳት ነው፡
ምንጭ ፡- ሰርቫይቫል 101/Surviva