የአእምሮ ጤና ማጣት ማንኛውንም ሰው በማንኛውም የህይወት ጊዜ የሚያጠቃ ነ

የአእምሮ ጤና

 

 

 

የአእምሮ ጤና ማጣት ማንኛውንም ሰው በማንኛውም የህይወት ጊዜ የሚያጠቃ ነው። ሰው በብዙ ምክንያት የተነሳ የአእምሮ ጤና ማጣት ሊያዳብር ይችላል። ከባድ የህይወት ገጠመኞች እንደ የቤተሰብ ችግር ወይም አስቸጋሪ የስራ አጋጣሚ ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ የአእምሮ ጤና ማጣት ከኪሳራ፣ ሞት፣ አደጋዎች ወይም ሰዎች ከጦርነት ከሚያገኙት ልምድ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ሰዎች በዘር የአእምሮ ጤና ማጣት የሚወረሱ ሲሆንና ጭንቀትም አንዱ ምክንያት ሊሆን ይችላል።

 

ለአእምሮ ጤና ማጣት ያለው አመለካከት ከግዜ በሗላ እየተቀየረ መጥቷል። በዛሬው ጊዜ ብዛት ያላቸው የኖርዌይ ህዝቦች ለአእምሮ ጤና ማጣት ህመም ግልፅና ጥሩ አመለካከት አላቸው። ብዙዎችም የአእምሮ ጤና ማጣት ህመምተኛ ክትትልና እርዳታ ልክ እንደሌሎች የአካል ህመምተኞች በጤና ጥበቃ በኩል ማግኘት አለባቸው ይላሉ። ብዙዎች የአእምሮ ጤና ማጣት ህመምን መዳን ይቻላል ባይ ናቸው።

 

የስደት ሂደት

 

ብዙዎች ሰዎች ወደ አዲስ አገር ሲሰደዱ የአ እምሮ የስደት ሂደት የሚባል ይደርስበታል፣ በመጀመሪያው ወቅት ህይወት ጥሩ ሲሆን ሰውም ለአዲሱ አገር ጥሩ አመለካከት አለው። ከጊዜ በሗላ ብዙዎች የሚጨንቅ ስሜት ሲሰማቸውና ስለ አዲሱም አገር መጥፎ ነገር ማሰብ ይጀምራሉ። ከጊዜ ወደ ጊዜም ለብዙዎች ህይወት እየተስተካከለ ይሄዳል።

ምንጭ፡-.samfunnskunnskap

 

  

Related Topics