ከነጭ እና ቀይ ሽንኩርት የሚመጣ የአፍ ጠረንን መቀነሻ ዘዴዎች

 

ከነጭ እና ቀይ ሽንኩርት የሚመጣ የአፍ ጠረንን መቀነሻ ዘዴዎች

 

 

 

Image result for ነጭ እና ቀይ ሽንኩርትImage result for ነጭ እና ቀይ ሽንኩርት

 

 

ነጭ ሽንኩርት እና ቀይ ሽንኩርት ምግብን በማጣፈጥና በተለይ ደግሞ ነጭ ሽንኩርት ምግብ ማጣፈጥ ብቻ ሳይሆን በተለያየ መንገድ ለጤንነታችንም በጣም ጠቃሚ እምደሆነ ይታወቃል።

ቢሆንም ግን ሁለቱም ነጭ እና ቀይ ሽንኩርት በተለይ በጥሬነታቸው ከተበሉ አንዳንድ እንደ ሆድን ማቃጠል አይነት ደስ የማይሉ ውጤቶች እንዳሏቸው ይታወቃሉ። ከነሱም አንደኛው መጥፎ የአፍ ጠረን ነው።

ነጭ ወይም ቀይ ሽንኩርት(በተለይ ነጭ ሽንኩርት) ሲሸረካከቱና ሲጨፈለቁ ከሌሎችም ነገሮች ጋራ allyl methyl sulfide የሚባል ንጥረ ነገር ከውስጣቸው ይለቃሉ። ይህ ንጥረ ነገር ደግሞ ሆዳችን ውስጥ ገብቶ ወደደማችን እንደሌሎች ነጥረ ነገሮች ተመጦ ይገባል። ከገባም በኋላ ላባችንና የአፍ ጠረናችን ለ አንድ ሙሉ ቀን ለሚያክል ጊዜ መጥፎ ሽታ እንዲይዝ ያደርጋል።

 

ከዚህ በታች የአፍ ጠረናችን በዚህ ንጥረ ነገር ምክንያት የያዘውን መጥፎ ጠረን እጅግ አድርገን እንዴት እንደምንቀንስ እንመለከታለን።

 

1) ሶስት የተቆላ የቡና ፍሬ አኝኮ አፍን መግሞጥሞጥ

2) እንደ ፖም ኮክ እና ወይን አይነት ፍራፍሬ መብላት:-

ፍራፍሬዎች ሲገመጡ ወይም ሲቆረጡ oxidize(ቀለማቸውን እንዲቀይሩ) እንዲሆኑ የሚያደርጋቸው ባህሪያቸው ከነጭ ሽንኩርት እና ሽንኩርት የሚመጣ መጥፎ የአፍ ጠረንንም የሚዋጋ ባህሪይ ነው።

3) እንደ ሰላጣ፣ ቆስጣ፣ ጎመን፣ ድንች አይነት አታክልቶችን መብላት:-

አንዳንድ አትክልቶች ከ ነጭ ሽንኩርት እና ቀይ ሽንኩርት የሚመጣን የአፍ ጠረን ለመቀነስ ጥሩ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ

4) ወተት መጥጣት፡-

ወተት በተለይ ከ ነጭ ሽንኩርት የሚመጣ መጥፎ የአፍ ጠረንን እጅግ እንደሚቀንስ ይታወቃል

4) green tea መጠጣት

5) ዳቦ መብላት:-

የካርቦሃይድሬት እጥረት ከመጥፎ የአፍ ጠረን ጋር ተያያዥነት አለው። ዳቦ ደግሞ በ ካርቦሃይድሬት የበለጸገ ምግብ ነው

6) እንደ ሎሚ ጭማቂ እና ግሬፕ ፍሩት ጭማቂ አይነት አሲድ የበዛባቸው መጠጦችን መጠጣት

7) ማስቲካ ማኘክ

8) ጥርስ በጥርስ ሳሙና እና በጥርስ ብሩሽ መቦረሽ

9) በ mouth wash መግሞጥሞጥ

ሌላ ማወቅ ያለብን ነገር

 

- ነጭ እና ቀይ ሽንኩርት መብላት በአፍ ብቻ ሳይሆን መጥፎ ሽታ የሚያመጣው ንጥረነገር ደም ውስጥም ስለሚገባ ላባችንንም መጥፎ ጠረን እንዲያመጣ ሊያደርግ ይችላል። ስለዚህ እንደ ሽቶ አይነት ነገር ትንሽ መጠቀም ከላባችን ልብሳችን ላይ ለተጣበቀው ሽታ መቀነስ አስተዋጽኦ ያደርጋል።

 

- ከ ነጭ እና ቀይ ሽንኩርት የሚመጣ ሽታ በጊዜ እራሱ ይጠፋል።

 

Source: tekamii.blogspot

 

  

Related Topics