የውበት እና የጤንነት መጠበቂ መንገዶች መኖራቸው ይታወቃል

ጥርት ያለ ለስላሳ ገጽታን እንዴት ልንላበስ እንችላለን?

 

Image result for የፊት ጥራት

በራሳችን ልናዘጋጃቸውና ልንጠቀማቸው የምንችላቸው ከባእድ ንጥረነገሮች (ኬሚካሎች) ነፃ የሆኑ ተፈጥሮአዊ ይዘታቸውን የጠበቁ የውበት እና የጤንነት መጠበቂ መንገዶች መኖራቸው ይታወቃል ፡፤ በዚህ ዝግጅት የፊት ቆዳ ውበትን መጠበቅ የሚያስችል ተፈጥሮአዊ አማራጭ እናስተዋውቆ፡፡

 

የፊታችን ቆዳ በጸሀይ ብርሀን፣ በእድሜ መግፋት እንዲሁም በሌሎች ምክንያቶች ጉዳት የደረሰበት እንደሆነ በቀላሉ እንዲያገግም፤ብሩህ እና ለስላሳ እንዲሆን የሚከተሉትን ቀላል መፍትሔዎች መጠቀም ይቻላል፡፡

 

በፓፓያ የታከመ ገጽታ

 

አንድ ለምግብነት የደረሰ ፓፓያ ማዘጋጀት ይኖርብናል። ፓፓያውን ማጠብና ማድረቅ ከዚያም ሁለት ቦታ እኩል መክፈልና ከውስጡ የሚገኙትን ፍሬዎች ማውጣት አለብን፡፡ ፍሬዎቹ ከፓፓያው እንዲለያዩ የሚያስችለውን በውስጠኛው ክፍል የሚገኘውን ቀጠን ያለ ሽፋን ማውጣትና የውጪኛውን ቆዳ መላጥ አለብን፡፡ በመቀጠልም የፓፓያውን የውስጠኛ ክፍል በመላግ ፊትን መቀባት፡፡ መዘንጋት የሌለብን ነገር ቢኖር ከመቀባታችን በፊት ፊታችንን ታጥበን ንፁህ መሆን እንዳለበት ነው። በአፋችን እና በአይናችን አካባቢ የሚገኑ የተሸበሸቡ ቆዳዎች ያሉ እንደሆነ ህክምናው ለንደዚህ አይነት የቆዳ ችግሮችም ጥሩ መፍትሔ ሰለሆነ በደንብ ማዳረስና መቀባት ተገቢ ነው፡፡ ይህ ህክምና ከፊት ባለፈ ለእግር፤ ለአንገት እንዲሁም ፀጉራችን ከግንባራችን እየሸሸ ያለ እንደሆነ ውጤታማ እንደሆነ የተደረሰበት በመሆኑበነኚህ ቦታዎች ላይ በደንብ መቀባት ተገቢ ነው፡፡

 

ከተቀባን በኋላ ከ 15 አስከ 20 ደቂቃ እንዲደርቅ እንተወውና ከዚያ በኋላ በውሃ እናፀዳዋለን፡፡ ይህም ህክምና በሳምንት ለሁለት ጊዜ ያህል መጠቀም የሚገባ ሲሆን በፓፓያው ውስጥ የሚገኝ ኢንዛይም በፀሀይ ብርሃን ምክንያት፣ በእድሜ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ለሚፈጠር የቆዳ መሸብሸብ እና መሻከር ፍቱን መፍትሔ ነው፡፡ በውጤቱም የሰውነታችን ቆዳ ጥርት ያለ እና ለስላሳ ይሆናል፡፡

ምንጭ፦selamall