በሰውነት ቆዳ ላይ የሚከሰት መለስተኛየቆዳ ላይ ምልክት እና ህመም ብዙ ጊ

ለቆዳ ላይ ችግር ሎሚን እንዴት እንጠቀም?

 

Image result for የፊት ጥራት

 

በሰውነት ቆዳ ላይ የሚከሰት መለስተኛየቆዳ ላይ ምልክት እና ህመም ብዙ ጊዜየሚከሰት ችግር ነው።ከሚታዩ የቆዳ ላይ ነጠብጣቦች እናአላስፈላጊ ምልክቶች ጀምሮ ትንሽ ለየት ያሉናያልተለመዱ የቆዳ ላይ መበለዝ እና መጥቆር እንዲሁም ቀለም መቀየር ከታዳጊነት እስከ ወጣትነት ማብቂያ ባለው የእድሜ ክልል አንድ ጊዜ ሊከሰት ይችላል።ታዲያ ይህ የቆዳ ላይ ችግር ገጽታን ማበላሸቱና አስቀያሚ እይታን መፍጠሩ አይቀርም፥ ይሁን እንጅ በቀላሉና ቤት ውስጥ በሚዘጋጅ የሎሚ ውህድ ይህን ችግር ማከም ይቻላል።ሎሚን በመጠቀም ብቻ ባክቴሪያንበመግደል፥ የሚከሰት የቆዳ መቀረፍን፣የተጎዳውን ቦታ ህመም ማስታገስ እና ወደቀድሞ ይዞታው መመለስ፣ ጥርት ያለ ቆዳእንዲኖር ማስቻል እና በተፈጠረው ህመምሳቢያ የተጎዳውን ቦታ በአግባቡ ማከምያስችልዎታል።ለዚህም ሎሚን ከተለያዩ ነገሮች ጋርበማዋሃድ መጠቀምና ህመሙን ማከምይቻላል፤ እንዴት ይዘጋጃል ካሉ ደግሞዝርዝሩን ይመልከቱ።አንዱን ሎሚ ከሁለት በመሰንጠቅ በንጹህየብርጭቆ ውሃ ውስጥ ጨምቆ ማዘጋጀት፥ፊትዎን በንጹህ የፊት ሳሙና ታጥቦ ማድረቅ።ከዚያም ንጹህ ጥጥ ወይም ጨርቅ ነገር ካለበዛ የሎሚውን ፈሳሽ በመምጠጥ በተጎዳውቆዳ ላይ በጥንቃቄ ማዳረስ ያንን የሎሚፈሳሽ ለ10 ደቂቃ ያህል ከቦታውአለማጽዳት።ከተባለው ጊዜ በኋላም በንጹህ ውሃበመለቃለቅ ፊትን ማደራረቅ፥ ይህን ህክምናበቀን ሁለት ጊዜ እስከሚሻለዎት ድረስመደጋገም።ይህን ሲያደርጉ ካቃጠልዎት እናካልተስማማዎት ወዲያው ይታጠቡት።1 የሾርባ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ እና 2የሾርባ ማንኪያ ማርን በንጹህ ብርጭቆበአግባቡ ማዋሃድ እና ለመቀላቀል ያህልትንሽ ውሃ ጠብ ማድረግ።በመቀጠልም ውህዱን በንጹህ እጅበመጠቀም የተጎዳን የቆዳ ክፍል ላይመቀባት እና ለ5 ደቂቃ ያህል ማቆየት።ከዚያም በንጹህ ውሃ በመለቃለቅ ማደራረቅይህንንም በቀን አንድ ዜ ማድረግ።መለስተኛ መጠን ያለው 1 የፈረንጅ ዱባ እና1 የሾርባ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂን

ማዘጋጀት፥ የፈረንጅ ዱባውን በመላጥበአነስተኛ መጠን ቆራርጦ ከሎሚ ጭማቂውጋር ማዋሃድ።ውህዱን በተጎዳው ክፍል ላይ በመቀባትለ20 ደቂቃ አቆይቶ በንጹህ ውሃ ተለቃልቆማድረቅ፥ ይህንን ደግሞ በቀን አንድ ጊዜማድረግ።ሁለት የሾርባ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ እናአንድ እንቁላል ማዘጋጀት፥ እንቁላሉን በንጹህእቃ ውስጥ ማድረግ እና የሎሚ ጭማቂውንቀላቅሎ በደንብ ማዋሃድ።የተቀላቀለውን ውህድ በሶስት በመክፈልበተጎዳው ክፍል ላይ በሶስት የተለያዩጊዜያት ከ5 እስከ 7 ደቂቃ ማቆየት።በንጹህ ውሃ ተለቃልቆ ማደራረቅ እናከህመሙ እስከሚድኑ ድረስ በየቀኑ ይህንመደጋገም።አንድ የሾርባ ማንኪያ የተፈጨ ቀረፋ እናሁለት የሾርባ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂንበሚያስፈልገው የጠብታ ውሃ መጠንበማድረግ ማዋሃድ።በተጎዳው ክፍል ላይ በጥንቃቄ መቀባት እናከ15 እስከ 20 ደቂቃ ቦታው ላይ ማቆየትእና መታጠብ።ምናልባት ቀረፋ ለአንዳንድ ሰዎችስለማይስማማ ጥቂት ውህዱን በተወሰነ ቦታላይ ቀብተው ያለውን ስሜት ይሞክሩት።1 የሾርባ ማንኪያ የተፈጨ ሽንብራ እና 1ፍሬ ሎሚን በንጹህ እቃ በአነስተኛ መጠንውሃ መቀላቀል እና ማዋሃድ።ውህዱን በተጎዳው ክፍል ላይ በመቀባትለተወሰኑ ደቂቃዎች ማቆየት እና በንጽህ ውሃመታጠብ፥ ይህንንም በቀን አንድ ጊዜ እስከሚድኑ ድረስ መቀባት።ከላይ በተገለጸው መንገድ ሎሚን ከተለያዩነገሮች ጋር በመቀላቀል የቆዳ ላይ ሽፍታ እናመሰለ ችግሮችን ማስወገድ ይቻላል።

ምንጭ፦ ማይ ላይፍ ስታይል