የአየር ብክለትና የቪታሚን D እጥረት ከአእምሮ የመርሳት ችግር ጋር ግንኙ

የአየር ብክለትና የቪታሚን D እጥረት ከአእምሮ የመርሳት ችግር ጋር ግንኙነት አላቸው ተባለ

 

የአየር ብክለትና የቪታሚን D እጥረት ከአእምሮ የመርሳት ችግር ጋር ግንኙነት አላቸው ተባለ

 

አእምሯችን በተለያዩ ምክንያቶች ለመርሳት ችግር ይጋለጣል ይላሉ ተመራማሪዎች።

ተመራማሪዎቹ በቅርብ ይፋ ባደረጉት ጥናት ላይ አንዳስታወቁት፥ የአየር ብክለትና የቪታሚን D እጥረት አእምሮን ከሚጎዱ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው ብለዋል።

በስኮትላንድ ከሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኤዲንበርግ እና ሌሎች የዓለም ክፍሎች የተወጣጡ ተመራማሪዎች ለመርሳት ችግር የሚዳርጉ የተለያዩ ምክንያቶችን ዘርዝረዋል።

ከነዚህም ውስጥ የአየር ብክለት፤ የኢታሚን D እጥረት እና ለተለያዩ አይነት የፀረ ተባይ መድሃኒቶች የተጋለጡ ሰዎች የአእምሮ የመርሳት ችግርን የማዳበር እድላቸው ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በምንጠጣው ውሃ ወስጥ የሚገኘው ከመጠን በላይ የብረት መዓድን /ሚነራልስ/ ሰዎች እንደ አልዛይመር ላሉ የመርሳት ችግር እንዲጋለጡ ያደርጋል ብለዋል።

እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ፥ እዚህ ጋር ልብ ልንለው የሚገባን ነገር ከላይ የተዘረዘሩት ምክንያቶች ከመርሳት ችግር ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተለዩ ናቸው እንጂ እስካሁን ማረጋገጫ አልተሰጣቸውም።

የጥናት ቡድኑ መሪ ዶክተር ቶም ሩስ፥ጥናቱን ለመስራት የተነሳነው የአእምሮ የመርሳት ችግር በሰዎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት በምን መልኩ ሊከሰት የችላል የሚለውን ለመለየት ነው ብለዋል።

በጥናታችንም አካባቢያችን ላይ የሚስተዋሉ ነገሮች ከችግሩ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው መለየት ችለናል የሚሉት ዶክተር ቶም፥ በነዚህ ዙሪያ የሆነ ነገር መስራት እንዳለበን ምልክት ሰጥቶናል ብለዋል።

አሁን በሰራነው ጥናት ከፍተኛ የሆነ የአየር መበከል እና የቪታሚን D እጥረት ከአእምሮ የመርሳት ችግር ጋር ግንኙነት አንዳላቸው ማረጋጋጥ ችለናል ሲሉም ዶክተር ጄፍ ያብራራሉ።

እንደ ዶርከት ጄፍ፥ ቀጣዩ ስራ እነዚህ ነገሮች እንዴት የመርሳት ችግርን ያስከትላሉ የሚለው መለየት እና ችግሩን ለመቅረፍ ምን ማድረግ አለብን በሚለው ዙሪያ እንሰራለን ብለዋል።

 

ምንጭ፦ www.huffingtonpost.co.uk

 

 

 

  

Related Topics