ምንም እንኳን የማንኛውም ሰው ደም የተሰራበት መሰረታዊ ነገር አንድ አይነ

 

የደም አይነቶች – BLOOD TYPES

 

Image result for ስለ ደም አይነት

 

ምንም እንኳን የማንኛውም ሰው ደም የተሰራበት መሰረታዊ ነገር አንድ አይነት ቢሆንም ያንዱ ሰው ደም ከሌላው ይለያል የደም አይነት የተለያየ እንዲሆን የሚያደርገው ነገር በቀይ የደም ሴሎች የውጭው አካል ላይ ያሉ አንቲጂን የሚባሉ ነገሮች ናቸው አንቲጂን ማለት ማንኛውም ነገር ሆኖ ነገር ግን የሰውነትን በተፈጠሮ በሽታ የመከላከል አቅም ወይንም ኢሚዩን ሲስተም ማስቆጣት የሚችል ነገር መሆን አለበት ለምሳሌ ቫይረስ ባክቴሪያ ኬሚካል የአበባ ብናኝ አልያም ሌሎች ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ

 

ደም በሰውነታችን ውስጥ የሚዘዋወር ፈሳሽ ሲሆን ዋና ጥቅሙም ምግብና ኦክሲጂን ለተለያዩ የሰውነታችን ህዋሳት ማቀበልና ከህዋሳት ውስጥ የሚወጣውን ካርቦን ዳይ ኦክሳይድና ሌሎችንም ቆሻሻዎች ማስወገድ ነው የሰውነት በተፈጥሮ በሽታ የመከላከል አቅምም ያለው በደም ውስጥ ነው ደም ፈሳሽ ቢመስልም በውስጡ ግን የተለያዩ ሴሎችንና ሌሎች ፕሮቲኖችን ይይዛል እነዚህም ሴሎች ደም ከውሃ ትንሽ ከፍ ያለ ዴንሲቲ እንዲኖረው ያደርጋል አንድ 70 ኪሎ ግራም የሚመዝን ሰው በአማካይ 5 ሊትር ወይም አንድ ጋሎን ደም ይኖረዋል

 

ደም የተሰራው ከምንድን ነው ?

 

፩ . ሴሎች/ህዋሳት- እነኚህ ከጠቅላላው ደም 45% ሲሆኑ አብላጫውን የሚይዙት ቀይ የደም ሴሎች ናቸው የደም ሴሎች የሚሰሩት በአጥንት መቅኔ ውስጥ ነው

 

ቀይ የደም ሴሎች /Red Blood Cells-RBCs/

ነጭ የደም ሴሎች /White blood cells or leukocytes/

ፕላትሌትስ /Platelets/

 

፪ . ፕላዝማ – ይህ ፈሳሹ የደም ክፍል ሲሆን በአብዛኛው የተሰራው ከውሃ ሆኖ ፕሮቲኖችን እና ሌሎች ነገሮችን ይይዛል ፕላዝማ

ከጠቅላላው ደም 55% ይሆናል

 

ቀይ የደም ሴሎች ኦክሲጂን ለመሸከም የሚያስችላቸው ሂሞግሎቢን የተባለው ሞለኪውል አላቸው በደም ውስጥ ያለው የቀይ የደም ሴሎች መጠን ሄማቶክሪት ይባላል ይሄን ቃል ብዙ ጊዜ በላቦራቶሪ ምርመራ ላይ እናየዋለን መደበኛ መጠኑም 45% ነው የደም ማነስ በሽታ በሚኖርበት ጊዜ መጠኑ ከዚህ ያንሳል

 

ነጭ የደም ሴሎች በዋናነት የሰውነትን በተፈጥሮ በሽታ የመከላከል አቅም የሚገነቡት ናቸው ብዙ አይነት ነጭ የደም ሴሎች አሉ ሥራቸውም እንዲሁ ይለያያል ፕላትሌትስ ደም በሚፈሰን ጊዜ ደም እንዲረጋ የሚያደርጉት ናቸው

 

ስለደም ይሄን ያህል ካልን በቂ ነው በቀይ የደም ሴሎች ላይ ያሉትን የተለያዩ አንቲጅኖች የተለያየ አይነት ደም እንዲኖረን ያደርጋሉ በዚህም ምክንያት 8 የደም አይነቶች አሉ በአብዛኛው የሚታወቁት አራቱ የደም አይነቶች ናቸው እነሱም ኤ.(A) ቢ.(B) ኤቢ.(AB) እና ኦ.(O) ናቸው ነገር ግን ሌላ Rh የሚባል አንቲጂን አለ አንዳንድ ሰዎች ይሄ አንቲጂን ሲኖራቸው ሌሎች ደግሞ የላቸውም ስለዚህ በመደበኛው የደም አይነት ላይ Rh ያላቸው (Rh +) እና የሌላቸው(Rh -) እያልን ስንከፋፍለው 8 የደም አይነት ይኖራሉ ማለት ነው

 

A +, A -, B +, B – , AB + , AB -, O +, O –

 

“A” የደም አይነት A የተባለ አንቲጂን ሲኖረው ፀረ-B የሆነ አንቲቦዲ በፕላዝማ ውስጥ ይኖረዋል ያማለት ቢ. የደም አይነት ወደሰውነታችን ቢገባ ፀረ-ቢ. አንቲቦዲዎች ጥቃት ያደርሱበታል ማለት ነው ለዚህም ነው በደም ልገሳ ጊዜ የሚለገሰው ደም ከበሽተኛው ደም ጋር አንድ አይነት መሆን ያለበት

 

“B” የደም አይነት B የተባለ አንቲጂን ሲኖረው ፀረ-A የሆነ አንቲቦዲ በፕላዝማ ውስጥ ይኖረዋል

 

“AB” የደም አይነት A እና B አንቲጂን ሲኖረው ምንም አይነት አንቲቦዲ አያመርትም ምክንያቱም እራስን ማጥቃት ይሆናል

 

“O” የደም አይነት ምንም አይነት አንቲጂን የሌለው ሲሆን ፀረ-A እና ፀረ-B አንቲቦዲዎች ይኖሩታል

 

“AB” የደም አይነት ምንም አይነት አንቲቦዲ ስለማያመርት ከሁሉም የደም አይነት መቀበል ይችላል የዚህ አይነት ደም ያለው ሰው ሁለገብ ተቀባይ ይባላል/Universal Recipient/ መቀበል እንጂ መስጠት አያውቅም ንፉግ ነው

 

“O” የደም አይነት ምንም አይነት አንቲጂን ስለማይኖረው ለሁሉም ሰው ሊሰጥ ይችላል ስለዚህም ኦ. የደም አይነት ያለው ሰው ሁለገብ ለጋሽ /Universal Donor/ ይባላል መስጠት እንጂ መቀበል አይወድም ቸር ለጋስ ነው

 

 እንግዲህ ደማችሁ ምን አይነት እንደሆን ማወቅ ከፈለጋችሁ ተመርመሩ

ምንጭ፦ ethioclinic

 

  

Related Topics