እርግዝና ከጽንስ መፈጠር ጀምሮ እስከ ልጅ መውለድ ባለው ጊዜ ውስጥ ብዙ ሂ

ስለ እርግዝና ጠቅላላ መረጃ

 

                                                            

 

እርግዝና ከጽንስ መፈጠር ጀምሮ እስከ ልጅ መውለድ ባለው ጊዜ ውስጥ ብዙ ሂደቶችን ያልፋል። ይሄ ሂደት በተለይ ለአዲስ ወላጆች እንግዳ ስለሚሆን ግራመጋባትን ሊፈጥር ይችላል። ስለሆነም እርግዝናን ከማረጋገጥ ጀምሮ የጽንሱን መፈጠር ተከትለው ስለሚከሰቱ የሰውነት እና ስሜታዊ ለውጦች አውቆ መዘጋጀት ይገባል።

ጽንስ

የወንድ የዘር ፈሳሽ በሴቷ ብልት ውስጥ በተፈጥሮአዊ የግብረ ስጋ ግንኙነት ወይም በሰውሰራሽ መንገድ ከፈሰሰ በኋላ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዘር ህዋሶች ከታችኛው የሴቷ የብልት ክፍል ወደላይ በመዋኘት በሴቷ የዘር ማስተላለፊያ ቱቦ ውስጥ የተዘጋጀ እንቁላል ካገኙ በእንቁላሉ ዙሪያ ያለውን ቅርፊት ለመስበር ይሞክራሉ።

 

የቆዳ መለጠጥ ምልክት (Stretch mark) እና የቆዳ መጥቆር

90% እናቶች በእርግዝና ወቅት በሚጨምሩት ኪሎ ምክንያት የቆዳ መለጠጥ ምልክት በሰውነታቸው ላይ ይወጣባቸዋል። ሲጀምር ቀይ ወይም ደማቅ ሐምራዊ፣ እየቆየ ሲሄድ ነጭ ሆኖ የሚጎረጉደው ይህ ምልክት ትክክለኛ ምክንያቱ ይህ ነው ባይባልም በእርግዝና ጊዜ ባሉ የሆርሞን እና የሰውነት ለውጦች አማካኝነት እንደሚመጣ ይታወቃል።

መንታ እርግዝና

መንታ እርግዝና የሚፈጠረው እንቁላል በሚለቀቅበት ወቅት (ovulation) ሁለት እንቁላሎችን አዘጋጅተሽ እነርሱ ከሁለት የወንድ የዘር ህዋሶች ጋር ስለተዳቀሉ ወይም አንድ እንቁላል ከአንድ የዘር ህዋስ ጋር ተዳቅላ የፈጠረቻት የፅንስ ህዋስ ለሁለት ተከፍላ ሁለት ፅንሶች በመስራቷ ነው።

ከእርግዝና ዜና ጋር የሚሰሙ ስሜቶች

ብዙዎች ልጅ ሊወልዱ እንደሆነ ሲያውቁ በጣም ደስተኛ ይሆናሉ። አንዳንድ ወላጆች ግን የተደባለቀ ስሜት ሊኖራቸው ይችላል። ለእናቶች እርግዝና የሰውነት እንዲሁም የአስተሳሰብ ለውጥ ይፈጥርባቸዋል። ለአባቶች እውነት እውነት አልመስል ሊል ይችላል።

በማህፀን ውስጥ የጽንስ አቀማመጥ

ጽንስ በማህፀን ውስጥ የተለያዩ አቀማመጦች ይኖሩታል፡፡ እስከ 36ኛው ሳምንት ድረስ ማህፀን ውስጥ በቂ ቦታ ስለሚኖር ጽንሱ እንደፈለገው ይገለባበጣል፡፡ በየጊዜው በመገለባበጥ የተለያዩ አቀማመጦችን ስለሚይዝ ከ36 ሳምንት በፊት ያለው አቀማመጥ ሲወለድ የሚኖረው አቀማመጥ ላይሆን ይችላል፡፡ ሲወለድ የሚኖረውን አቀማመጥ ከ36 ሳምንት በኋላ ይይዛል፡፡

የህጻኑ (ፅንሱ) የሆድ ውስጥ እንቅስቃሴ

የልጅሽ እንቅስቃሴ ልጅሽ እድገት እያሳየ እንደሆነ ያመላክታል፡፡ በተጨማሪም ከአንቺ ጋር ያለውን ግንኙነት ያጠነክርልሻል።

የወር አበባ መጥፋት

ለወር አበባ መጥፋት ወይም መዘግየት ዋነኛ ምክንያት እርግዝና ቢሆንም ከእርግዝና በተጨማሪም የተለያዩ ምክንያቶች ይጠቀሳሉ።ብዙ ሴቶች የእርግዝና ጥርጣሬ የሚኖራቸው የወር አበባ ከሚመጣበት ጊዜ ሲዘገይ ነው። የወር አበባ ዘገየ ማለት ግን በእርግጠኝነት እርግዝና ተከሰተ ማለት አይደለም።

ምንጭ፦ethioclinic

 

  

Related Topics