ግርግር በበዛበት የከተማ ኑሮ ከጭንቀት መውጫ መንገዶች

ግርግር በበዛበት የከተማ ኑሮ ከጭንቀት መውጫ መንገዶች

 

ግርግር በበዛበት የከተማ ኑሮ ከጭንቀት መውጫ መንገዶች

 

በከተማ አካባቢ መኖር ዘመናዊውን አለም ይበልጥ ለመቅረብና በርካታ የስራ አማራጮችን ለማግኘት ይረዳል።

ከመረጃ እና ከወቅታዊው የአለም ሁኔታ ጋር አብሮ ለመሄድ እንደሚያግዝም ይታመናል።

የህክምና እና ስነ ልቦና ባለሙያዎች ደግሞ ካለው ጠቀሜታ ባሻገር በርካታ ችግሮች እንዳሉት ይናገራሉ።

አለም ላይ በርካታ ከተሞችን ባዳረሰው ጥናታቸው የከተማ ነዋሪዎች በገጠር አካባቢ ከሚኖሩት በ21 በመቶ የበለጠ ለጭንቀትና አለመረጋጋት እንዲሁም በ39 በመቶ ከፍ ያለ ደግሞ ለስሜት መረበሽ ተጋላጭ መሆናቸውን ይፋ አድርገዋል።

ከፍተኛ ደምጽ፣ የአየር ብክለት፣ የተጨናነቁ መንገዶች፣ አንድ አይነት እና ተደጋጋሚ የእግረኛ መንገድ ደግሞ ለዚህ ችግር የሚዳርጉ መሆናቸውን በጥናታችን ለይተናልም ብለዋል።

ይህ በከተሞች መኖር የሚያመጣው ጉዳይ ነው ያሉት አጥኝዎቹ፥ የየዕለት ሁኔታዎች አዕምሮን የመረበሽና የማስጨነቅ አቅም እንዳላቸውም ይገልጻሉ።

በጀርመን ፍሊየንደር ክሊኒክ የህክምና ባለሙያና ከአዕምሮ ጤና እና ጭንቀት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ላይ የሚሰሩት ዶክተር ማዝዳ አድሊ ከተሜነት ከአዕምሮ ጤና ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው ያስረዳሉ።

እንደ እርሳቸው ከተማ መኖር አዕምሮን በቀጥታ ይጎዳል ማለት ሳይሆን አብዝቶ የሚጨነቅበት ጉዳይ ጋር እንዲሟገት እንደሚያደርገው ነው የሚያስረዱት።

እናም ወከባ በበዛበት ከተማ መኖር የሚያስከትለውን ጫና ለመቋቋም እነዚሀን እንዲያደርጉ ይመክራሉ፤

መናፈሻ ስፍራዎችን ማዘውተር፦ የሚኖሩበት አካባቢ ወከባ እና ግርግር ከበዛበት ከዚህ ወጣ ባለ እና ፀጥታ ወደሰፈነበት የመዝናኛ ፓርኮች ጎራ ማለትን ይመክራሉ።

በመኖሪያ አቅራቢያዎ ያለው አጠቃላይ እንቅስቃሴ አዕምሮን እረፍት የለሽ በማድረግ እርሰዎንም ለጭንቀትና አለመረጋጋት ይዳርጋልና፥ አረንጓዴ ገጽታ ባላቸው የመናፈሻ ስፍራዎች ለራስዎ ጊዜ ይስጡ።

አካባቢን በደንብ መረዳትና ማወቅ፦ የሚኖሩበትን አካባቢ እንቅስቃሴ፣ መገበያያ ስፍራዎች፣ መዝናኛና መሰል ቦታዎችን መለየትና ማወቅ።

ይህ መሆኑ ደግሞ እጅግ የሚያስጨንቅዎትን ጉዳይ ተገንዝበው ለአዕምሮዎ እረፍትን መስጠት ያስችልዎታል።

ከዚህ ባለፈም ከሚኖሩበት አካባቢ ማህበረሰብ ጋር በመግባባት ነገሮችን ቀለል ባለ መንገድ እንዲከውኑ ይረዳዎታል ነው የሚሉት ዶክተር አድሊ።

ምናልባት የሚረብሽዎት ድምጽ ከየት እንደሚመጣ ማወቁ፣ ለአፍንጫ ምቾት የማይሰጥ ሽታን አካካቢ መለየትና ወደ ስራዎ ሲሄዱ ከግርግር ነጻ የሆነ ጎዳና መውጫን ማወቁም መልካም ነው ይላሉ።

እነዚህን ሁኔታዎች ሲለዩ ሌላ ጊዜ ምን ይሻለኛል እያሉ የሚጨነቁበትን ጉዳይ መፍትሄ አበጁለት ማለት ነው።

የሁሉንም መነሻ ሲያውቁ ቢያንስ ቀድሞ መዘጋጀት ይለምዳሉና አዕምሮዎን የሚረብሽዎን ጉዳይ መፍትሄ አበጁለት ማለት ነው።

እናም በተቻለ መጠን አካባቢን ማወቅና በደንብ መረዳት መቻል ለችግሮች መፍትሄ ማዘጋጃ መንገድ ይሆናልና ያንኑ ያድርጉ።

የእግር ጉዞ ማድረግ፦ በተጨናነቁ ጎዳናዎች መኪና እያሽከረከሩ መሄዱ የባሰ ለጭንቀት ይዳርጋል ይላሉ ባለሙያው።

ይህ ምናልባትም በርካታ ተሽከርካሪዎች ከመኖራቸውና ግርግር ከመብዛቱ አኳያ ሊሆን ይችላልና ያንን ያስወግዱ።

የእግር ጉዞ ማድረግ አልያም ቀለል ያሉ ብስክሌቶችን ተጠቅሞ ወጣ ማለትም ለዚህ መፍትሄ ነው ይላሉ።

ከዚህ ባለፈም የመውጫ መንገድ (የሚረብሹ ነገሮች ሲከሰቱ መፍትሄ መስጫ እና እንደ ማምለጫ) ማዘጋጀቱንም ይመክራሉ።

በእንቅልፍ ሰዓት የሚረበሹ ከሆነ ሌላ የመኝታ አማራጭ ቢኖርዎት፤

ግርግር በሚሆን ሰዓት ብቻዎን የሚያሳልፉበትን አማራጭ መፍጠር፥ ባለሙያዎች ከከተማ የግርግር ኑሮ ጭንቀት መውጫ መፍትሄ ያሏቸው ናቸው።

 

 

ምንጭ፦ cnn.com/

 

  

Related Topics