Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ማንበብ አዕምሮን ለማስፋትና እውቀት ለማዳበር አይነተኛ ሚና እንዳለው ይ?

ማንበብ ለጤናማ ህይዎት

 

 ማንበብ ለጤናማ ህይዎት

 

ማንበብ አዕምሮን ለማስፋትና እውቀት ለማዳበር አይነተኛ ሚና እንዳለው ይታመናል።

በማንበብ ራስን ከአላስፈላጊ እና ከአልባሌ ቦታዎች በመጠበቅ እውቀትን መገብየትም ይቻላል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ባለሙያዎች የማንበብ ልማድ ለጤና እና ለደህንነት መልካም መሆኑንም ይመክራሉ።

ከአሜሪካው ያሌ ዩኒቨርሲቲ በተውጣጡ ተመራማሪዎች የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው፥ በሳምንት ቢያንስ ለ3 ሰዓት ተኩል ለሆነ ጊዜ የሚያነቡት ከማያነቡቱ የተሻለ ጊዜ በህይዎት የመቆየት እድል አላቸው።

በቀጣዮቹ 12 አመታት ከማያነቡት በ23 በመቶ የተሻለ በህይዎት የመቆየት እድል አላቸው ብለዋል።

ይህ የሚሆነው ደግሞ ማንበብ ከአንጎል ህዋሳት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ስለሚኖረውና አዕምሮ ላይ እክል በመፍጠር የሞት ሁኔታን የሚያፋጥኑ ሁኔታዎችን ለመቀነስ ስለሚረዳ መሆኑንም ያስረዳሉ።

እንደ ተመራማሪዎች ማንበብ በዚህ መልኩ የጤና ሁኔታን ያሻሽላል፤

ጭንቀትን ያስወግዳል፦ 60 በመቶው የሰው ልጅ ጤና የሚስተጓጎለው ከጭንቀት በመነጨ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ።

ይህ ደግሞ ለልብ እና ተያያዥ የጤና ችግሮች ተጋላጭነትን በ50 በመቶ እንዲሁም በአዕምሮ ውስጥ የሚከሰት የደም መፍሰስን በ40 በመቶ ይጨምራል እንደ ጥናቱ።

በዚህ ዘርፍ የተደረገው ጥናት ታዲያ ማንበብ ሙዚቃ ከማድመጥም ሆነ ንጹህ አየር ለማግኘት ከሚደረግ ሽርሽር ይልቅ ጭንቀትን በ68 በመቶ እንደሚቀንስ ያሳያል።

ሌላው ቢቀር ካፌ ወይም መንገድ ላይ እስከ 6 ደቂቃ ድረስ እንኳን ጋዜጣ የማንበብ ልማዱ ቢኖረን የልብ ምትን ማስተካከል እና የሚከሰት የጡንቻ አከባቢን መቆጣትና መስነፍ ማስተካክል ይቻላል ባይ ናቸው።

በእንግሊዟ ሊቨርፑል ዩኒቨርሲቲ የተደረገው ጥናትም ተመሳሳይ ውጤትን አሳይቷል፤ 38 በመቶ የሚሆኑ ወጣቶች የጭንቀታችን ፍቱን መድሃኒት ራስን መጽሃፍ ውስጥ መደበቅ ነው ብለዋልና።

ለማስታወስ ችሎታ፦ በህይዎት እስካሉ ድረስ ነገሮችን ማስታወስ እና ቦታዎችን መለየት መቻል ከጤናዎ ጋር ተያያዥነት አለው፤ ነገሮችን በረሱ ቁጥር ከማህበረሰቡ የመገለል እድልዎ ከፍተኛ ነውና።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በኋለኛው የእድሜ ዘመን ላይ ከጊዜ ብዛት የመዘንጋት እና ነገሮችን የመርሳት ችግር ሊከሰት ይችላል።

ለዚህ ደግሞ ማንበብን ጨምሮ አዕምሮን ያዝ በማድረግ ማስተዋልን የሚጠይቁ እንደ ቼዝ አይነት ጨዋታዎች ላይ መሳተፉ መልካም መሆኑን ባለሙያዎች ይመክራሉ።

ከ294 በላይ የሆኑና እድሜያቸው 89 አመት የሆኑ አዛውንቶችን ባሳተፉበት ጥናታቸውም ይህን ማረጋገጣቸውን ይገልጻሉ።

በዚህኛው ዘመን አይቀሬ የሆነውን ችግር ለመቅረፍ ያለውን ጠቀሜታ ለመረዳት ባደረግነው ጥናት ይህን ማረጋገጥ ችለናል ነው ያሉት የቡድኑ መሪ ሮበርት ዊልሰን።

በዚህ ተግባር የተሳተፉት ከማይሳተፉት የተሻለ ከልጅነት እስከ እውቀት የነበራቸውን ህይዎት ማስታወስ እና ከድብርት እና ብቸኝነት ተላቀው የተሻለ አካላዊ ቁመናን የተላበሱ መሆኑንም ተናግረዋል።

የተሻለ እንቅልፍ ለማግኘት፦ በዚህ ዘመን ዘመናዊ ስልኮችን መጠቀምና ከመኝታ ሰዓት በፊት ማህበራዊ ሚዲያዎችን ማዘውተር የብዙሃኑ መገለጫ ሆኗል።

እንዲህ አይነት ልማድ ግን ለተቆራረጠ እና ለተዛባ እንቅልፍ እንደሚዳርግ ነው ጥናቶች የሚያሳዩት።

ይህ የሚሆነው ደግሞ ከስልኮቹ የሚወጣው ብርሃን አዕምሯችን የሚያመነጨውን ሜላቶኒን የተሰኘና ለመተኛት የሚረዳን ሆርሞን በሚገባ እንዳይመነጭ ስለሚያደርጉት ነው።

ከዛ ይልቅ መጽሃፍ ገለጥ አድርጎ ማንበብ፥ ከንቃት ወደ እንቅልፍ ለሚደረገው ጉዞ ምቹ እና መፍትሄ መሆኑን ነው ባለሙያዎቹ የሚናገሩት።

ማህበራዊ ተሳትፎን ያሻሽላል፦ መጽሃፍ ማንበብ መደበቂያና ከሌላው አለም መገለያ አድርጋችሁ አታስቡት፤ ከዛ ይልቅ አካባቢን ለማወቅና ለመረዳት ብሎም ማህበራዊውን መስተጋብር መቀላቀያ መንገድ ነው ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች።

ለምሳሌም ለብ ወለድ ማንበብ በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎችን አጠቃላይ ሁኔታ ለመረዳትና ለማወቅ ሁነኛው መፍትሄ ነውም ይላሉ።

ሰዎችን ከመረዳት አኳያም ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፥ እንዳውም ልብ ወለድ የሚያነቡት ከማያነቡት ይልቅ የተሻለ ሰዎችን የማወቅና የመገንዘብ አቅሙ እንዳላቸው ነው በጥናታቸው የገለጹት።

ምናባዊው እሳቤ የእውኑን አለም ገሃድ ለማግኘት እና ለመረዳት የተሻለ እድል እንደሚፈጥርም ነው የሚናገሩት።

 

የማገናዘብ አቅምን ከፍ ያደርጋል፦ ብዙ ባነበቡ ቁጥር ብዙ ነገሮችን ማወቅዎ አይቀርም፥ ይህ ደግሞ በርካታ ልምዶችን በመቅሰም መዳረሻዎን ያሰፋዋል።

ደጋግሞ ማንበብ ታዲያ ነገሮችን በተሻለ እንዲያውቁ በማድረግ የማገናዘብ አቅምን ያዳብራል።

ይህ ሁኔታ ደግሞ ከልጅነት ቢጀምር መልካም መሆኑንም ይመክራሉ።

ለእነርሱ እድሜ የተፈቀደ መጽሃፍን፥ ህጻናት ማንበብ ቢያዘወትሩ በኋለኛው እድሜያቸው የተሻለ የማገናዘብ አቅም አላቸው።

የማንበብ ልምዳቸው ከሰባት አመታቸው የሚጀምር ህጻናት ደግሞ ከፍ ያለ የማገናዘብ ብቃት እንዳላቸውም ነው የሚያስረዱት።

ይህም ከፍ ያለ እሳቤን ማዳበር፣ ተፅዕኖ የመፍጠር አቅምን መላበስ እና ተሰሚነት ያለው ግለሰብም ያደርጋል እንደ ባለሙያዎቹ ገለጻ።

ሁልጊዜም ማንበብ እና ራስን በእውቀት መገንባት ቀላል እና ያልተጨናነቀ ኑሮን እንዲመሩ ከማስቻሉም በላይ የተሻለ ጤናማ ህይዎትን ያጎናጽፋልና አንባቢ ይሁኑ መልዕክታቸው ነው።

 

ምንጭ፦ medicalnewstoday.com/