ለጤና እጅጉን ጠቃሚና አስፈላጊ ከሚባሉት አትክልት አንዱ የሆነው ነጭ ሽን

ነጭ ሽንኩርትን ከገበታ ማስወገድ ያለባቸው ሰዎች

 

 

ነጭ ሽንኩርትን ከገበታ ማስወገድ ያለባቸው ሰዎች

 

ለጤና እጅጉን ጠቃሚና አስፈላጊ ከሚባሉት አትክልት አንዱ የሆነው ነጭ ሽንኩርት ከገበታ ባይጠፋ የሚመረጥና አስፈላጊው ነው።

ነጭ ሽንኩርት የተለያዩ በሽታዎችን ቀድሞ ለመከላከልና የተከሰተን በሽታም ለማከም እጅግ አስፈላጊው አትክልት ነው።

ይሁን እንጅ ይህ አትክልት ለሁሉም ሰዎች እኩል መድሃኒትነት የለውም፥ ምክንያቱ ደግሞ ለአንዳንዶቹ ካለው ባህሪ አንጻር እንዲወስዱት አይመከርምና።

ይህን ጠቃሚ አትክልት ለምን መጠቀም እንከለከላለን ካሉ ደግሞ፥ ከታች የተጠቀሱትን ዝርዝሮች ይመልከቱ።

 

ቀደ ጥገና የሚያደርጉ ሰዎች፦

ለቀዶ ጥገና የተዘጋጁ ሰዎች ከህክምናው በፊት ቢያንስ ከሁለት ሳምንት ጀምሮ ነጭ ሽንኩርትን ከገበታ ማስወገድ ይኖርባቸዋል።

ምክንያቱም በቀዶ ጥገና ወቅት የሚከሰት መድማት በነጭ ሽንኩርት ፍጆታ ምክንያት ይበልጥ ሊባባስ ይችላልና።

 

ዝቅተኛ የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች፦

ዝቅተኛ የደም ግፊት በተለምዶ ደም ማነስ ያለባቸው ሰዎች ነጭ ሽንኩርት እንዲወስዱ አይመከርም።

ከተፈጥሮው አንጻር ነጭ ሽንኩርት ለደም ግፊት መቀነስ ምክንያት ስለሚሆን እንደዛ አይነት ተፈጥሮ ያላቸው ሰዎች ባይወስዱት እና ከገበታቸው ቢቀንሱት ይመከራል።

 

የጉበት ህመምተኞች፦

ነጭ ሽንኩርት ማንኛውንም አይነት ባክቴሪያ እና ቫይረስን በማስወገድ በንክኪ የሚመጣ ተላላፊ በሽታን የመከላከል አቅሙ የተረጋገጠ ነው።

ይሁን እንጅ በነጭ ሽንኩርት ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ውህዶች በአንጀት እና በሆድ አካባቢ አብዝተው ስለሚሰራጩ የምግብ መፈጨት ስርአትን ሊያስተጓጉሉ ይችላሉ።

ይህ ደግሞ የማቅለሽለሽ ስሜትን በማስከተል  ጤነኛ የነበረውን የስርአተ ምግብ መፈጨት ሂደት ላይ ችግር ስለሚያስከትል የጉበት ህመምተኞች ነጭ ሽምኩርትን ባይጠቀሙ ይመረጣል።

ከዚህ ባለፈ ደግሞ ነጭ ሽንኩርትን አብዝቶ መጠቀም በሰውነት ውስጥ የቀይ ደም ሴልን ቁጥር በመቀነስ ለደም ማነስ ችግር ስለሚያጋልጥ የዚህ በሽታ ተጠቂዎች እንዲጠቀሙት አይመከርም።

 

የአይን ህመም ያለባቸው ሰዎች፦

የአይን ህመምተኞችም ይህን አትክልት እንዳይወስዱ ይከለከላሉ፥ ምክንያቱም ተያያዥ ችግሮች ከነጭ ሽንኩርት ፍጆታ ጋር ተዳምረው በጊዜ ሂደት ጆሮ አካባቢ የመጮህ እና ተዛማጅ ችግሮች ያስከትላሉና።

ነብሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች፦

በእርግዝና ወቅት ነጭ ሽንኩርት ጠቃሚና አስፈላጊ ቢሆንም በዚህ ወቅት በሚከሰት መለስተኛ ህመም ምክንያት እንደ መድሃኒት መጠቀምና ተደጋጋሚ ፍጆታ አደገኛ ሊሆን ስለሚችል ማስወገድ ይገባል።

ከዛ ባለፈም የሚያጠቡ እናቶች ነጭ ሽንኩርትን አብዝተው መውሰድና ለአንዳንድ ህክምና በሚል ከውህዶች ጋር ቀላቅሎ መጠቀምም አላስፈላጊ ነውና በዚህ ወቅት ያን ከማድረግ መቆጠብ ይገባል።

ከዚህ ባለፈም የማስቀመጥ ህመም የያዛቸው ሰዎች ከህመሙ እስኪፈወሱ ድረስ ከዚህ አትክልት መታቀብ ይገባቸዋል።

ያ ካልሆነ ግን ውስጡ ያለው ውህድ ነገሮችን ስለሚያባብሳቸው አሁንም አሁንም በበሽታው ሊጠቁ ይችላሉ እና ያንን ከማድረግ ይቆጠቡ።

እናም ከላይ ከተጠቀሱት በአንዱ ተጠቂ ከሆኑ አልያም ከቤተሰብዎ አንዱ ከዚህ ጋር ተዛማጅነት ካለው የተባሉትን መንገዶች ቢጠቀሙ መልካም ነው።

ምንጭ፥  myilifestyle.com

 

  

Related Topics