ቀይ የወይን ጠጅ ከዚህ በዘለለም በርከት ያሉ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት

የቀይ ወይን ጠጅ የጤና በረከቶች

 

Image result for ወይን ጠጅ

 

በቀን ውስጥ አንድ የወይን ብርጭቆ ቀይ የወይም ጠጅ የምንጠጣ ከሆነ በርከት ያሉ የጤና ጠቀሜታዎች አለው ተብሏል።

ቀይ የወይን ጠጅን ከረጀም የስራ ቀን በኋላ አንድ ብርጭቆ መጠጣት እራሳችንን ዘና ለማድረግ እና ለማረጋጋት ይመከራል።

ቀይ የወይን ጠጅ ከዚህ በዘለለም በርከት ያሉ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት ጥናቶች ይጠቁማሉ።

በቀን አንድ ብርጭቆ የወይን ጠጅ መጠጣት ከሚያስገኛቸው የጤና በረከቶች መካከልም፦

በቶሎ የማርጀት እድላችንን ይቀንሳል፦ በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደ ጥናት ላይ እንደተገለጸው በቀይ የወይን ፍሬ ልጣጭ ላይ የሚገኙ ንጥረ ነገሮች ሰውነታችንን ተሎ እንዲያረጅ ከሚያደርጉ በሽታዎች የሚከላከሉ ፕሮቲኖችን በመያዙ ቀይ የወይን ጠጅ በቶሎ እንዳናረጅ ይረዳናል ብለዋል።

የማስታወስ ችሎታችንን ይጨምርልናል፦ አንድ ብርጭቆ ቀይ የወይን ጠጅ በውስጡ ባለው ሬስቬራቶል በተባለ ንጥረ ነገር አማካኝነት አእምሯችን በቀላሉ እንዲያስታውስ ያደርጋል።

ለልብ ህመም እንዳንጋለጥ ይረዳናል፦ አንድ ብርጭቆ ቀይ የወይን ጠጅ መጠጣት ለለብ ህመም የመጋለጥ እድላችንን በእጅጉ እንደሚቀንስ ተመራማሪዎች ተናግረዋል።

ቀይ ወይን በውስጡ ባለው  ታኒናስ ንጥረ ነገር አማካኝነት ልባችን ጤነኛ እንዲሆን ስለሚያደርግ ቀይ የወይን ጠጅ ለልብ ህመም እንዳንጋለጥ ይረዳናል ተብሏል።

ለዓይን ጤንነት፦ ቀይ የወይን ጠጅ ለዓይናችን ጤንነትም ፍቱን ነው ተብሏል።

ጥናቶች እንዳመላከቱት ቀይ የወይን ጠጅ የሚጠጡ ሰዎች ለዓይን በሽታ የመጋለጥ እድላቸው በ32 በመቶ ዝቅ ያለ ነው።

ለካንሰር እንዳንጋለጥ ይረዳናል፦ በቀይ የወይን ፍሬ ልጣጭ ላይ የሚገኘው ፕሮቲን የካንሰር ሴልን በመግደል ለካንሰር በሽታ የመጋለጥ እድላችንን በእጅጉ እንዲቀንስ ሰለሚያደርግ አንድ ብርጭቆ ቀይ የወይን ጠጅን መጠጣት ይመከራል።

የጉንፋን በሽታን ይከላከላል፦ ቀይ ወይን በውስጡ ባለው አንቲ ኦክሲደንት አማካኝነት በጉንፋን እንዳንያዝ ያደርጋል።

ተመራማሪዎቹ እንዳስታወቁት በሳምንት እስከ 14 ብርጭቆ ቀይ የወይን ጠጅ የሚጠጡ ሰዎች በጉንፋን የመያዝ እድላቸው በ40 የወረደ ነው ብለዋል።

 

ምንጭ፦ ideadigezt.com

 

  

Related Topics