መነሻው ምን እንደሆነ በዉል ሳያዉቁት በጀርባ ህመም ተሰቃይተዋል

የጀርባ ህመም መነሻ 10 ምክንያቶች

 

 

 

መነሻው ምን እንደሆነ በዉል ሳያዉቁት በጀርባ ህመም ተሰቃይተዋል? የጀርባ ህመም በአደጋ ብቻ ላይከሰት ይችላል የአቀማመጥ ሁኔታ የሚጠቀሙት ጫማ ከመጠን ያለፈ ዉፍርትና ከባድ ነገሮችን ማንሳት የላይኛዉና ታችኛው ጀርባ ህመም ያስከትላል።

በሴቶችና ወንዶች ላይ የጀርባ ህመም የሚያስከትሉ መነሻ ምክንያቶችን በዝርዝር እንመልከታቸው

 

1. የቢሮ ወንበር

የቢሮ ወንበርዎ ለጀርባ ህመም ከፍተኛ አስተዋጽዎ ያደርጋሉ ሲቀመጡ ጎበጥ የሚሉ ከሆነ ጀርባዎ ላይ ጫና ያደርጉበታል አከርካሪ ሊጋመንታችን ከአቅም በላይ ይለጠጥና ዲስካችን የጀርባ አጥንታችን እንዲወጠር ያደርጋል ከጊዜ ብዛት የጀርባ አጥንታችንን በመጉዳት ለጀርባ ህመም ይዳርገናል።

 

2. የሚያደርጉት ጫማ

ጫማ ለጀርባዎ ጤንነት ከፍተኛ ሚና ይጫዎታል የማይገባ/ትክክል ያልሆነ ጫማ አቋምዎን በማዛባት ማዕከላዊ የግራቪቲ ቦታን ያዛባል ይህም በታችኛው የጀርባ ክፍልዎ ላይ ህመም ይፈጥራል።

 

3. የሚተኙበት ፍራሽ

የሳሳ ፍራሽ መጠቀም የታችኛዉን የጀርባ ክፍል እንዲሰምጥ ያደርጋል በተጨማሪም የአከርካሪ አጥንቶችን እንዲዛቡ በማድረግ በጡንቻዎች እና የአከርካሪ መገጣጠሚያዎች ላይ ዉጥረት ይፈጥራል።

 

4. የጀርባ ቦርሳ

የሚይዙት የጀርባ ቦርሳ ትልቅ ከሆነ ብዙ እቃዎችን የመያዝ እድል ይኖርዎታል ተጨማሪ ሸክም በጀርባዎ ላይ መጫን ትልቁ የጀርና ህመም ምክንያት ነው። በአንድ በኩል ያለዉ የሰዉነት ክፍልዎ ላይ ሸክም መጨመር የአከርካሪ አጥንቶች እንዲጎብጡ በማድረግ የጀርና ህመም እንዲከሰት ያደርጋል።

 

5. በሆድ በኩል መተኛት

በሆድ በኩል ተደፍተዉ ሲተኙ በጀርባዎና በአከርካሪ አጥንትዎ ላይ ተጨማሪ ሸክም ይጨምራል በአከርካሪ አጥንትዎ ላይ ተጨማሪ ሸክም ጨመሩ ማለት ደግሞ የሙሉ ሰዉነትዎን ቅርጽ ያዛባዋል ጭንቅላትዎን ወደ ጎን ሲያዞሩት ደግሞ ጭንቅላትዎንና አከርካሪዎት ከመደበኛ አቅጣጫዎ ውጪ አደረጉት ማለት ነው።

 

6. ትከሻ ወይም አንገት

ለረጂም ሰዓት አንገትን አዘንብሎ(ደፍቶ) መቆየት ወይም መጓዝ በትከሻዎቻችን መሀል ያሉትን ጡንቻዎች እንዲዝሉ በማድረግ የላይኛው ጀርባ ክፍል እና የአንገት ህመም ያስከትላል።

 

7. ላኘቶኘና ስማርት ስልኮች

በአለም ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ በኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎቻቸው ፍቅር ስለወደቁ በነዚህ ሰዎች ላይ የጀርባ ህመም የተለመደ ነው። በስራ በተጠመድበት ወቅት ስልክዎትን በትከሻዎና በጆሮዎ መሀል በመያዝ ለረጂም ጊዜ ማውራት የአንገት ህመም ያስከትላል።

 

8. ከመጠን ያለፈ ውፍረት

ከሌሎች በሽታዎች በተጨማሪ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ለጀርባ፣ መገጣጠሚያ እና ጡንቻዎች ህመም ያጋልጠናል። አብዛኛዎቹ በሚኖራቸው ውፍረት በዳሌና በታችኛው የጀርባ ክፍል ህመም ያጋጥማቸዋል።

 

9. እግርን አጣምሮ መቀመጥ

እግርዎን አጣምረው በሚቀመጡበት ጊዜ የአከርካሪ አጥንትዎ ቀጥ ማለት ይሳነዋል ይህም በዳሌ አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎች ከመጠን በላይ እንዲለጠጡ ያደርጋቸዋል። በተጨማሪም የደም ዝውውር በመስተጓጐሉ ምክንያት ቫሪኮስ ቬይን(Varicose vein) ለተባለ በሽታ ያጋልጣል።

 

10. ሲጋራ ማጨስ

በሲጋራ ውስጥ ያለው ኒኮቲን ወደ ዲስክ(Disc) የሚሄደውን የደም ዝውውር በመቀነስ የአከርካሪና ጐን አጥንት ችግር ያስከትላል። በተጨማሪም ካልሲየም በአግባቡ ከሰውነታችን ጋር እንዳይዋሀድ በማድረግ የአጥንት እድገትን ይገታል በመሆኑም ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች ከማያጨሱ ሰዎች በአንድ እጥፍ የጀርባ ህመም ችግር ያጋጥማቸዋል።

ምንጭ፡- ethioc

 

  

Related Topics