ያው ሁላችንም እንደምናውቀው ኮልጌት፣ ቡርሽና ውኃ ያስፈልጋል፡፡

አፍና ጥርስን እዴት አድርጎ ማጽዳት ይቻላል?

 

Image result for የጥርስ ንፅህና

 

ያው ሁላችንም እንደምናውቀው ኮልጌት፣ ቡርሽና ውኃ ያስፈልጋል፡፡ በሃገራችን በኢትዮጵያ ደግሞ መሟጪያ የሚጠቀሙም ይኖራሉ፡፡ ያው ለመጥቀስ እንጂ አፍና ጥርስን ለማጽዳት እራሱን የቻለ ትንሽ ጥበብ ወይም ዘዴ አለው፡፡ ምክንያቱም ዘዴ የሚያስፈልገው አፍና ጥርስ ሳሙና ውስጥ ተነክሮ ሳይጸዳ የወጣ ልብስ እንዳይመስል ነው፡፡ ሳይጸዳ ግን ተነክሮ ብቻ የወጣ እንዳይሆን ለማለት ነው፡፡ አፍና ጥርስን ለማጽዳት በጎልጌቱ የጥርስን ዙሪያ መቦረሽ እንደጀመሩ አፍን አ አ አ ብሎ ምላስን ካወጡ በኋላ እዛው ቀስ ብሎ በቡርሹ ምላስን በኮልጌት መቀባት፡፡ ከዛም ጥርስን መቦረሽ መቀጠል፡፡ ለምሳሌ ለሶስት ደቂቃ አካባቢ በኤለትሪክም ሆነ በጅ ቡርሽ ከቦረሹ በኋላ አፍ ውስጥ ጎልጌቱ ከምራቅ ጋር ፈሳሽ ስለሚሰራ አፍን ገጥሞ ምላስን 360 ዲግሪ እያስሽከረከሩ የጉንጭን ግድግዳ ዙሪያ በምላስ መፈተግ ወይም መጥረግ፡፡ ይህ በሚደረግ ጊዜ አፍ መዘጋት አለበት፡፡ አንድ ደቂቃ አካባቢ ሊበቃ ይችላል፡፡ መጨረሻ ላይም ምላስን አ አ አ አ ብሎ ምላስን ጎልጉሎ በምላስ መጥረጊያ የምላስን አናት ለምሳሌ ለ30 ሰኮንዶች ማጽዳት፡፡ ምላስ መጽዳቱ የሚታወቀው የተፈጥቶ ስጋ መልኩ ከታየ ነው፡፡ የቆሸሸ ምላስ ጥቁር ወይም ቡናማ ነው፡፡ ምላስን ሲያጸዱ የግድ በጣም ወደ ውስጥ መግባት አያስፈልግም፡፡ ምክንያቱም ሊያስመልስ ስለሚችል ነው፡፡ ከዛም በንጹህና በቀዝቃዛ ውኃ ተጉመጥምጦ መጨረስ፡፡ የሁሉም ጠቅላላ ሂደት 5 ደቂቃወች አካባቢ ይወስዳል፡፡ ከጥርስ በተጨማሪ ምላስና የጉንጭ ዙሪያ የጠቀስኩት የምግብ ፍርፋሪና ጣም ምላስና ጉንጭ ላይ ስለሚቀር ከትንሽ ቆይታ በኋላ ቫክተሪያ ሰርቶ ሽታ ስለሚፈጥር ነው፡፡ ዞሮ ዞሮ ጥርስን ብቻ ቦርሾ ምላስና የጉንጭን ዙሪያ መተው ትርጉም የለውም፡፡

 

ከጥርስ በተጨማሪ ምላስና የጉንጭ ዙሪያ የጠቀስኩት የምግብ ፍርፋሪና ጣም ምላስና ጉንጭ ላይ ስለሚቀር ከትንሽ ቆይታ በኋላ ቫክተሪያ ሰርቶ ሽታ ስለሚፈጥር ነው፡፡ ዞሮ ዞሮ ጥርስን ብቻ ቦርሾ ምላስና የጉንጭን ዙሪያ መተው ትርጉም የለውም፡፡

የቀን ውሎንስ እንደት ወዋል ይቻላል?

በስራ፣ በትምህርት፣ በስብሰባ ወይም በሆነ ጉዳይ ምክንያት ጉዙ ላይ ሲቆይ አፍ ስለሚደርቅ ሽታ መፍጠሩ አይቀርም፡፡ ነገር ግን ገና ጧት ከቤት ሲወጣ ንጹህ ሆኖ ካልተወጣ ከምሳም ሆነ ከጉዞ በኋላ ሽታው ይብስበታል፡፡ ከምሳ በኋላ ቡና አለመጠጣት ለአፍ ንጽህና አስተዋጾ አለው፡፡ ልክ ምሳ ከበሉ በኋላ ደግሞ ያው ኮልጌት ምናምን ስለማይኖር እዛው ከሚበላበት ቦታ ፍራፍሬ ካለ፤ በተለይ ፓም መግመጥ፣ ጥርስን በስንጥር መሰቅሰቅና ውኋ ተጎንጭቶ ምላስን 360 ዲግሪ እያስሽከረከሩ የጉንጭን የውስጥ ግድግዳ መጥረግና ከዛም ውሃውን በዛው መዋጥ ይቻላል፡፡ ከ2 - 3 ጊዜ ይህንን ከደጋገሙት ይረዳል፡፡ እዛው የሚበላበት ቦታ ላይ ማድረግ ይቻላል፡፡ መጨረሻ ላይም ውኃ ተጎንጭቶ መዋጥ ለአፍ ንጽህና በጣም ይጠቅማል፡፡ ማስቲካና ሚንት ነገር ለጊዜው እራስን ማታለያ እንጂ ምንም አይረዳም፡፡ እንዳውም ማስቲካ ስናኝክ ብዙ አየር ስለምንውጥ ሆዳችን ውስጥ አየር ያበዛል፡፡ ማስቲካና የመሳሰሉትን ግን ካስፈለገ እንኳን አፍ ውስጥ ብዙ አለማቆየት ነው፡፡ ማስቲካና ሚንትም ለጥርስ ደህንነት ጥሩ መሆናቸው ያጠራጥራል፡፡

 

ምግብ በተወሰኑ ወቅቶች ላይ መብላትና የተጠቀሱትን ዘደወች በመጠቀም የትንፋሽ ሽታን በጣም መቀነስ ይቻላል፡፡ ሰው ለጊዜው ትንፋሼ ይሸታል ብሎ ከተጠራጠረ ወደ ሌላ ሰው በጣም አለመጠጋትና ሲተነፍሱም ለምሳሌ ባፍንጫ መተንፈስ ከትዝብት ያድናል፡፡ አብሮ ለሚኖር ሰው ምናልባት ሽታ ስለተለመደ አይታወቅም፡፡ ከቤት ሲወጣ ግን ለምሳሌ፤ ለስራ፣ ለትምህርት፣ ለስብሰባ፣ ወደ ቤተ ክርስቲያ፣ ጸድቶ መውጣት ለሽታ ብቻ ሳይሆን ለጤንነትም ጭምር በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ አንዳንድ ሰወች በቀላሉ እራሳቸውን ማጽዳት ሲችሉ ከሰላምታቸው በፊት ሽታቸው የሚቀድም አለ፡፡ የፈለገ ወዳጅ ቢሆንም ትንፋሽህ ይሸታል ብሎ ደፍሮ የሚነግር የለም፡፡ ወዳጅ ከሆኑማ ደግሞ ላለማስቀየም ምልክት እንኳን ሳያሳዩ ችሎ መቆየት የተለመደ ነው፡፡ አንዳንድ ሰወችም ሽታ ሲያስቸግራቸው አፋቸውን በጃቸው የሚከልሉ አሉ፡፡ የሰው ልጆች ስንባል እንዲሁ ጥሎብን ሽታና ጠረን ለረጅም ጊዜ ማስታወስ እንችላለን፡፡ ታዲያ የምናውቀው ሰው አንዳንድ ጊዜ ወይም ሁል ጊዜ የሚሸት ከሆነ፤ ገና ሰላም ከመባባላችን በፊት መጀመሪያ የምናስታውሰው መጥፎውንም ሆነ ደህናውን ሽታ ነው፡፡ ስለዚህ ሰው እራሱ ባለቤቱ በቀላሉ ንጽህናውን መጠበቅና ሌላ ሰውንም አለማስቸገር ተገቢ ነው፡፡

ምንጭ፡-tatariw.

 

  

Related Topics