10 ባለ ክብረ ወሰን የሰዉነት ክፍሎች

ድንቃ ድንቅ

 

10 ባለ ክብረ ወሰን የሰዉነት ክፍሎች

  1. ቀጭን ወገብ (15 ኢንች)

15 ኢንች ወይም 38 ሴንቲ ሜትር የሚለካዉ የካቲ ጁንግ ቀጭን ወገብ የሰዉነት ቅርጽ ‹‹ስምንት ቁጥር›› እብደሚያስመስለዉ ምንም ጥርጥር የለዉም፡፡ ካቲ በ2007 ሰባት ዓ.ም ጊነስ የአለም ክብረ ወሰን መጽሀፍ ላይ ለመዉጣት ከሰዉነት ላይ ጥብቅ የሚል ጠንካራ የዉስጥ ልብስ (ኮርሴት) ለአመታት ለብሳለች፡፡ ካት በአሁኑ ወቅት በህይወት ያለች የቀጭን ወገብ ክብረ ወሰን ባለቤት ብተሆን፤ በዚህ ዘርፍ ሪኮርዱን የያዘችዉ 13 ኢንች ወይም 33 ሜትር የሚለካ ወገብ ያላት ኤቴል ግሬንጀር ናት፡፡

 

  1. የግራ አዉራ ጣት (ርዝመት 10.2)

ሉዊ ሁዋ macrodactyly በተባለ እንግዳ ኣይነት በሽታ የሚሰቃይ ቻይናዊ ነዉ፡፡ በሀምሌ 2007 ዓ.ም ሻንጋይ ውስጥ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል በተኛበት ወቅት የግራ አዉራ ጣቱ 10.2 ኢንች (25.9 ሴንቲ ሜትር) ርዝመት ነበረዉ፡፡ የቀዶ ጥገና ሀኪሞች ሀምሌ 20 ቀን የሉዊ ጣቶችን መጠን ለመቀነስ ሰባት ሰዓታት የወሰደ ኦፕራሲዮን አድርገዉለታ፡፡ ሀኪሞች በሂደቱ አምስት ኪሎ ግራም የሚዝን ስጋና አጥንት አዉጥተዉለታል፡፡

 

  1. ረዥም ምላስ (2.7 ኢንች)

ጀርመናዊቷ ተማሪ አኒካ ኢርምለር ሰባት ሴንቲ ሜትር በሚረዝመዉ ምላሷ ስሟን በጊነስ የአለም ክብረ-ወሰን መጽኀፍ ላይ ማስመዝገብ ችላለች፡፡ ሀምበርግ አጠገብ የምትገኘዉ ታንግስቴድት ከተማ ነዋሪ የሆነችዉ የዐስራ ሁለት አመቷ ታዳጊ በብስኩት የቀረበላትን አይስክሬም ከስሩ መላስ ትችላለች፡፡ ጓደኞቿ ግን፤ ይህም ለማድረግ ጣቶቻቸዉን መጠቀም አለባቸዉ፡፡

 

  1. ረዥም ጥፍር (በመኪና አደጋ እስኪቆረዉ ድረስ)

ከ1979 ዓ.ም ወዲህ ጥፍሮቿን ያልቆረጠችዉ የኡታህ ግዛት ተወላጅ ለ. ሬድሞንድ፤ 8.65 ሜትር በ28 ጫማ ከ4.5 ኢንች) እስኪደርሱ ድረስ እየተንከባከባች አሳድጋለች፡፡ በዚህም መሰረት የአለማችን ባለረዝዥ ጥፍር ባለቤት በመሆን ስሟን በጊነስ የአለም ክብረ-ወሰን መጽሀፍ ላይ ማስፈር ችላለች፡፡ የሚያሳዝነዉ ግን፤ በየካቲት 2009 ዓ.ም በደረሰበት የመኪና አደጋ ጥፍሮቿን አጥታለች፡፡

 

  1. የአለማችን ረጅሙ የጆሮ ጸጉር (ከ13 ሴንቲ ሜትር በላይ)

ህንዳዊ ግሮሰሪ ባለቤት  ራድሃካንት ቫድፓይ አንድ የህይወት ግብ አለዉ፤ የአለማችን ረዥም የጆሮ ጸጉር ባለቤት መሆን፡፡ ራድሃካንት በ2003 ዓ.ም. 13.2 ሴንቲ ሜትር በሚረዝመዉ የጆሮ ውስጥ ጸጉር ስሙን በጊነስ የአለም ክብረ ወሰን  መጸሀፍ ላይ ማስመዝብ ችሎ ነበር፡፡ ይሁንና፤ በዚህ ዉጤት ልረካዉ ራድሃካንት የጆሮ ጸጉር የበለጠ እንዲረዝምለት እያደረገ ነዉ፡፡

 

  1. ረጅሙ እግር ከ4 ጫማ በላይ

በጊነስ የአለም ክብረ ወሰን መጽሀፍ መሰረት ሉሲያዊቷ ስቬትላና ፓንክራቶቭ የእግሮቿ ርዝመት ከሎሎች የአለማችን ረዥሟ ሴት ባትሆንም እግሮቿ 132 ሴንቲ ሜትር (4.4 ኢንች) ይረዝማል፡፡ ከወገብ በላይ ያለዉ የሰዉነቷ ክፍል አጭ በመሆኑ ቁመቷ 196 ሴንቲ ሜትር (6.5 ኢንች) ነዉ፡፡ የእግሯ ቁጥር 46 በመሆኑ ጫማ ለመግዛት 1992 ዓ.ም እስከ 1995 ዓ.ም. በዩ.ኤስ አሜሪካ የሴቶች ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ነበረች፡፡

 

  1. ረዥሙ አፍንጫ (4.5 ኢንች)

በ19 49 ዓ.ም. በቱርክ የተወለደዉ ሜህሜት ኦዝዩሬክ የአለማችን ረዥሙ አፍንጫዉ ሀምሌ 6/2007 ዓ.ም. በተላከበት ወቅት 4.5 ኢንች (8.8 ሴንቲ ሜትር) ርዝመት ነበረዉ፡ ሜህሜት በአሁኑ ወቅት በቱርክ የምትገኘዉ አርትቪን ከተማ ነዋሪ ነዉ፡፡

 

  1.  ብዙ ጣቶች (25)

ፕራሚኒያ ሜናሪያን ዴቬንድራ ሃርኔ ባላቸዉ የጣት (የእጅና የእግር) ብዛት የአለም ክብረ ወሰንን የሚያጋሩ ህንዳዉያን polydactylism በተባለዉ የጤንነት እክል ሳቢያ እያንዳቸዉ በአጠቃላይ 25 ጣቶች አላቸዉ፡፡ የእጃቸዉ ጣቶች 12 ሲሆን የእግራዉ ደግሞ 13 ጣቶች አላቸዉ፡፡

 

  1. ረዥሙ የሽፋሽፍት ጸጉር (3.7 ኢንች)

በኒዮርክ ግዛት የሳራናክ ከተማ ነዋሪዉ ፍራንክ ኤምስ ስሙን በጊነስ የአለም ክብረ ወሰን መጽሀፍ ላይ ለማስፈር 3.7 ኢንች (9.6 ሴንቲ ሜትር) ርዝመት ያለዉ የሽፋሽት ጸጉር አስፈልጎታል፡፡በ2003 ዓ.ም. በዚሁ ረገድ ዝግጁት እንዳላደርግም ለረዳ ይችላል፡፡ በጊስ ሀላፊነቶች ጋር በስልክ ተገናኝቶ አዲስ ክብረ-ወሰ ባለቤት መሆን እንደተረጋገጠ ለጋዜጠኞች ሲናገር፤ ‹‹የሸፋሽፋቴ ጸጉር ይህን ያህል እንዴት ሊረዝም እንደቻለ አላዉቅም፡፡ ሁሌ እያደገ ነዉ››፡፡

 

10. ረዥሙ የሴት ጢም (11 ኢንች)

የኢሊኖይ ግዛት ነዋሮዋ ቪቪያን ዊለር በጢሟ ውስጥ ካሉት ጸጉሮቿ መካከል ረዥሙ 11 አንች (27.9 ሴንቲ ሜትር) በመሆኑ የአለማችን ረዥም የሴት ጢም ባለቤት በመሆን ታድላለች፡፡ አባቷ የሰባት አመት ልጅ እያለች መላጨት እንድትጀምር ቢነገራትም፤ቪቪያን ከ1993 ዓ.ም. ወዲህ ተላጭተዉ አታዉቁም፡፡ ይህን በማድረግ የአለማችን ረዥም የሴት ጢም ባለ ክብረ-ወሰን ልትሆን ትችላለች፡፡

ምንጭ፡- እቴጌ 2002 ዓ.ም