ከፍተኛ የደም ግፊት ካለብዎት የሚከተሉትን ምግቦች መመገብ ያቁሙ!

ለደም ግፊት ማይመከሩ ምግቦች

 

ከፍተኛ የደም ግፊት በሽታ ካለብዎት የሶዲየም(sodium) እና ስብ(ፋት) ይዘታቸው በጣም ዝቅተኛ የሆኑ ምግቦች እንዲመገቡ ይመከራል፡፡ የሚከተሉት ምግቦች ዝርዝር ሊያቆሟቸው ወይም የአወሳሰድ መጠናቸውን መቀነስ ያለብዎት ምግቦች ሲሆኑ ምናልባት ከምግቦቹ ዝርዝር ውስጥ እጅግ በጣም የሚወዱት ምግብ ተካትቶ ሊሆን ይችላል፡፡

 

1. ቀይ ሥጋ (Red Meat)
ጤናማ የምግብ ገበታ በመጠን ያነሰ ትራንስ ወይም ሳቹሬትድ ፋት ብቻ ይኖረዋል፡፡ የዚህም ምክንያት ፋት ያላቸው ምግቦች ለልብ እና ለደም ቧንቧዎች ጥሩ ስላልሆኑ ነው፡፡

 

2. ስኳር (Sugar)
ተጨማሪ ካሎሪ የያዙና እና ከፍተኛ የስኳር መጠን ያላቸው ምግቦች የሰውነት ክብደት እንዲጨምር ያደርጋሉ፡፡ ከፍተኛ የሰውነት ክብደት መጨመር ለደም ግፊት መከሰት ከፍተኛ አስተዋጽዎ ያበረክታል፡፡ ከፍተኛ የሰውነት ክብደት ሲኖረን ልብ ላይ ጫና በመፍጠር የደም ፍሰት እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡

 

3. ጨው (Salt)
ሶዲየም በብዛት ስምንጠቀም/ስንወስድ የደም ግፊት መጠናችን በፍጥነት ይጨምራል፡፡ በተጨማሪም ልብ እና የደም ቧንቧዎች በቀጥተኛ ሁኔታ ይጎዳሉ፡፡

 

4. አልኮል (Alcohol)
ከመጠን ያለፈ የአልኮል መጠጥ መጠጣት የደም ግፊታችን ከፍ እንዲል ያደርገዋል፡፡ ከፍተኛ የደም ግፊት በሽታ ያለባቸው ሰዎች አልኮል መጠጥ እንዲጠጡ አይመከርም፡፡

 

5. የወተት ተዋጽኦዎች (Whole Milk)

ወተት ጥሩ የካልሲየም መገኛ ነው፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ የስብ መጠን ያላቸው የወተት ተዋጽኦዎች ከሚፈለገው በላይ ስብ ሰውነታችን እንዲያገኝ ያደርጋሉ፡፡ አንድ ኩባያ ወተት 8 ግራም ፋት ሲኖረው ከዚህ መካከል 5 ግራም የሚሆነው ሳቹሬትድ ፋት ነው፡፡ ሳቹሬትድ ፋት ደግሞ ከልብ ህመም ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡

 

6. ሳውርክራውት(sauerkraut)

ሳውርክራውት ብረት(አይረን)፣ ፋይበር እና ቫይታሚን ሲ ና ኬ በውስጡ የያዘ ሲሆን በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራል፡፡ በተጨማሪ የካሎሪ መጠኑ ዝቅተኛ ሲሆን ግማሽ ኩባያ ሳውርክራውት 13 የሚሆን ካሎሪ በውስጡ ይዟል ነገር ግን 460 ሚ.ግ. ሶዲየም በውስጡ ይዟል፡፡

 

7. ፒክልስ(pickles)
ፒክልስ በቫይታሚን ኬ(vitamin k) የበለፀገ ሲሆን የካሎሪ ይዘታቸው ዝቅተኛ ነው ነገር ግን የሶዲየም መጠናቸው በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ መካከለኛ መጠን ያለው ፒክልስ 570 ሚ.ግ. ሶዲየም በውስጡ ይዟል ስለዚህ ከፍተኛ የደም ግፊት ካለብዎ አመጋገብዎን ይቀንሱ ወይም ያቁሙ፡፡

 

መልካም ጤንነት!!
ምንጭ፡- ኢትዮ ጤና

 

  

Related Topics