Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

አንጀሊና ጆሊ የዓለማችን ቀዳማዊ ዝነኛ ሴት ናት ብለን መከራከር እንችል ??

የአንጄሊና ጆሊ ሌላኛው ሕይወት

 

Image result for አንጄሊና ጆሊ

 

አንጀሊና ጆሊ የዓለማችን ቀዳማዊ ዝነኛ ሴት ናት ብለን መከራከር እንችል ይሆናል፡፡ አልፎ ተርፎም አፋችንን ሞልተን ልግስናዋን፣ የዓላማ ጽናቷንና ድፍረቷን በተመለከተ የዓለማችን ምርጥ ሴት ናት ማለት እንችል ይሆናል፡፡ እነኝህ ሁለት ሐሳቦች ጭራሽ የማይገናኙ ይመስሉን ይሆናል፤ የመጀመሪያው ሐሳብ ተጨባጭና ፊት ለፊት በምንመለከተው  እውነታ ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ ሁለተኛ በግል ስሜት ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡ እውነታው ግን ሁለቱም አተያዮች የማይነጣጠሉ መሆናቸው ነው፡፡  አንጆሊና ጆሊ የአለማችን ምርጥ ሴት የሆነችወ የአለማችን ቀዳሚዋ ዝነኛ ሴት በመሆኗ ነው፤ በዙሪያዋ ካሉት ተራ ሴቶች የተለየች መሆኗን ለማወቅ ደግሞ፣ ብዙም አሰቸጋሪ አይደለም፡፡

በእርግጥ፣ ማንኛችንንም አትመስልም፡፡ እንዲያውም፣ ራሷን ካልሆነ በስተቀር ሌላ ሰው አትመስልም፡፡ የዓለማችን ቀዳማዊ ዝነኛ ሴት ካደረጓት ምክኒያቶች መካከል ደግሞ፣ አንዱ ይኸው እሴቷ ነው፡፡ የህይወቷ  ትርጉም በተዋናይነት  በምትሰራው ህይወት ላይ የተመረኮዘ እንዲሆን አትፈልግም፡፡ በዝነኛነት በምትመራው ሕይወቷ ላይ የተመረኮዘ እንዲሆን አትሻም፡፡ እንዲያውም፣ የሕይወቷን ትርጉም በሰውነቷ ላይ የመጻፍ ፍላጎት ስላላት በየጊዜው ትነቀሰዋለች፡፡ በዙሪያዋ ባሉት ወንዶች ዘንድ የወሲብ  ስሜት የሚቀሰቅሰው ሰውነቷ በአሁኑ ወቅት በጣም ቀጥኗል፡፡

ሰዎች አንጄሊናን ያገኛትን ሰው የሚጠይቁት አንድ ጥያቄ አለ፡፡ ጥያቄውም በዳርፋር ስለምታካሂደው ስራ ወይም ወላጆቻቸውን በኤድስ ላጡ ሕፃናት ስለምታደርገው ድጋፍ አይደለም፡፡ ጥያቄያቸው፣ ‘’አማላይ ናት ወይ?’’  የሚል ነው፡፡ ሰዎች ስለሷ የሚያወሩት ለየት ያለች ፍጡር እንደሆነች አድርገው ነው፤ አንድ ሴቷን ተኩላ አማላይ አድርጎ በሚመለከታት ዓይን እነሱም አንጄሊናን ሳይመለከቷት አይቀርም፡፡ አጭር ባትሆንም ሰውነቷ ደቃቃ ነው፡፡ ይሁንና፣ ወርቃማው አካሏ ያብረቀርቃል፡፡ ዓይኖቿና ከናፍርቷ  የፕላስቲክ ቆዶ ጥገና ውጤት ቢሆንም፣ ዝናብ እንደረፈበት አስፋልት መንገድ ያንጸባርቃሉ፡፡ አማላይነቷ   ልክ እንደ ከናፍርቷ የተጋነነ መምሰል ሲገባው ይኸው እሴቷ በእንቅስቃሴዎቿና በውበቷ ጎልቶ ስለሚታይ በዚህ ውስጥ ይዋጣል፡፡ ይሁን እንጂ፣ በካምቦዲ በሚገኘው የዱር አራዊት   ጥብቅ ቦታዋ የእስያ ታይገርን ሕልውና ለማራዘም የምታደርገውን ጥረት በሰውነቷ  አማካኝነትም ከመግለጽ ወደኋላ የማትል ሴት ናት፣ ጀርባዋ ላይ  የእንሰሳውን ስዕል በትልቁ ተነቅሳዋለች፡፡ ይኸው ጥረቷ ሳይሳካ  ቢቀር ቀሪው አንድ ብቸኛ እንስሳ በአንጄሊና ጀርባ ላይ ተነቅሶ እንዲቀር የፈለገች ይመስላል፡፡

አንጄሊና ፊልም መስራት ከጀመረችበት ወቅት ወፈፌ ቢጤ ነበረች፡፡ ምንም እንኳ በወቅቱ ልጅ ብትሆንም፣ ወፈፌነቷ ከግብረ- ስጋ ግንኙነት በኋላ የወሲብ አጋራቸውን እንደሚመገቡት የተወሰኑ አይነት ሸረሪቶች በዙሪያዋ ባሉት ዘንድ አግራሞትን  የምትጭር ፍጡር አድርጓታል፡፡ ሰውነቷን መቆራረጧ፣ ንቅሳቶቿ፣ አደንዛዥ ዕፁ፣ ራሷ ይፋ ያደረገችው ወሲባዊ ማጋጣነት፣ እንዲሁም በአንገቷ ላይ  ያንጠለጠለችው የመጀመሪያ ባለቤቷ የቢቢ ቦብ ቶርንተንን ደም የያዘው  ብልቃጥ በእርግጥም ወፈፌ የሚያሰኟት ነበሩ፡፡ አንጄሊና የወፈፌነቷን ወቅት መለስ ብላ በማስታወስ፣ ‘’ወደዚህ ሙያ የገባሁት  ለህይወቴ ትኩረትና ዓላማ ሳይኖረኝ ነው፡፡ ደስተኛም ጤነኛም አልነበርኩም፡፡ ቃለ-ምልልስ ለማድረግ ስቀመጥ እንኳን ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም ነበር፡፡ ለሌላ ሰው የማካፍለው ምንም ዓይነት ነገር  ያለኝ አይመስለኝ ነበር፡፡ ያን ጊዜ ሁሉም ነገር ለእኔ ወር ነበር’’ትላለች፡፡

ይሁንና፣ በጊዜ ሂደት እየበሰለች ሄዳለች፡፡ በ2001 ዓ.ም. በጦርነት ወደዳሸቀችወ ሲዩራ ሊዮን ካመራች በኋላ፣ አሰቃቂ የሆኑ ሁኔታዎችን ከተመለከትኩ በኋላ የምኖረውን ሕይወት አስቸጋሪ አድርጌ በመውሰዴ ምን ያህል የዋህ እንደሆንኩ ልረዳ ችያለሁ፡፡ በችግር የተሞላ ሕይወት ምን እንደሚመስል ያወቅሁት በዚህን ወቅት ነው፡፡ የሆነ ሰው በጥፊ መትቶን፣ አንቺ የማትረቢ የካሊፎርኒያ ሴት፣  አለማችን ለብዙ ህዝብ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነች አታውቂም?´በማለት ከተኛሁበት ያነቃኝ ያህል ነበር፡፡  በእርስ በርስ ጦርነቱ መሃል በመገኘቴ በአጭር ጊዜ ውስጥ የበፊቱን ማንነቴን አውልቄ ጣልኩት፡፡ ይህንንም እንዳደርግ ያስገደደኝ ዙሪያ ጀርባዬን ስመለከት የጠቆራረጡ እጆችን እግሮችን በማየቴ ነው ስትል ተናግራለች

በቀጣይነት የተፈጠረው ክስተት ወደ የተባበሩት መንግስታት በመደወል የድርጅቱ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር የበጎ ፈቃድ አምባሳደር መሆኗ ነው፡፡ በመላው ዓለም በጦርነት በዳሸቁ አካባቢዎች የሚገኙ ሠላሳ ያህል የስደተኛ ካምፖችን የጎበኝችው አንጄሊና፣ በሂደት ‹‹የዓለም ዜጋ›› ለመሆን በቅታለች፡፡ በዚሁ ጊዜም እናት ሆናለች በቀዳሚነት ለካምቦዲያው ማሶክስ፣ በቀጣይነት ለኢትዮጵያዊቷ ዛህራ፣ ከብራድ ፒት ለወለችው ቪሎህ፣ በቅርቡ በቬትናማዊው ፓክስ እና ሆናለች፡፡ ከለሊቱ 10፡00 ሰዓት በፖሊሲ ጉዳዮች ዙሪያ ዝርዝር ነጥቦችን የያዙ የኢሜል መልክቶችን በየጊዜው የምትልከውን የ4 ልጆች እናት የአዕምሮ ሰላም አላት ለማት አስቸጋሪ ቢሆንም መስከረም 11 2001 ዓ.ም የኒዎርክ የንግድ ማዕከል መንታ ህንፃዎች ሲፈርሱ ስትመለከት የተለያዩ ባህሎችን ከመቅሰም ያላገኘችውን ትርጉም ለህይወቷ አግኛታለች፡፡

ዳሩ ግን ፣ የዓለማችን ቀዳሚዋ ዝነኛ ሴት የሆነችው ከጊህ ውስጥ ባገኘችው የህይወት ትርጉም አይደለም፡፡ ይህም ክብር ልትቀዳጅ የቻለችው የአሜሪካ ባህል እሷ ካጋጠማት የተለየ ታሪክ ለመግለጽ በመቻሉ ነው፡፡ እራሷን በመላው ዓለም ዙሪያ ካለው በችግር እና በሶቆቃ የተሞላ ህይወት ጋር የመሳስተሳሰር ጠንካራ ፍካጎት ቢኖራትም ሰዎች አሁንም ቢሆን ወፈፌ ናት ብለው በመጠርጠራቸው የዓለማችን ቀዳማዊች ዝነኛ ሴት ለመሆን በቅታለች አንጄሊና ወፈፌነቷ አሁንም አለቀቃትም መባሉ አልፎ አልፎ ከምትሰራቸው ፊልሞች እና ወሬ አሳዳጅ ጋዜጠኖች ከሚያወጧቸው ዘገባዎች ባለፈ ስለሷ ብዙ ነገሮች እንድናውቅ ይረዳናል፡፡ ይሁን እና በየሳምንቱ በ4 ወይም በ5 መጼቶች ሽፋን ላይ ከሚወጡት 4 ወይም 5 አሜሪካዊያን መካከል አንዷ የሆነችው በስራዋ አማካኝነት ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ በፊት ከነዚህ መጼቶች መካከል አንዱ  “ውስብስብ የሆነው ሌላኛው ህይወቷ” በሚል ርዕስ ስር አንጄሊና የሚመለከት ሰፊ ጹፍ አውጥቶ ነበር፡፡ በእርግጥ ጹፉ የዓለም ዜጋ እና እናት ከሆነች ወዲ ያሉትን ታሪኮቿን በሙሉ ማካተት በቻለ ነበር፡፡ ብራድ ፒትን  ከጄኒፈር አኒስተን መንጠቋ፣ አንድ ሳይሆን ሶስት ልጆችን በማደጎ ማሳደጓ፣  የማገጎ ልጆቹዋን ልክ እንደ ወለደቻት ልጇ መንከባከቧ፣ ቤቷ ውስጥ የተደላደለ ኑሮ እየኖረች ፊልም ከመስራት ይልቅ ዓለማችንን አለመችንን ለመታደግ መሯሯጧ፣   እንዲሁም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጣም መቅጠኗ ‘’ውስብስብ ሌላ ሕይወት’’ አላት ለማለት የሚያስደፍሩ ነጥቦች ናቸው፡፡

ጽንፈኛ ስብእና እንዳላት የምታምነው አንጀሊና፣ ጽንፈኝነቷ ዓለም ያነገበ ለመሆኑ ከማሳሰብ ወደ ኋላ አትልም፡፡ የማዶክስ ጆሊ- ፒት ፕሮጀክትን የምትገልጸውም በዚሁ ድባብ ነው፡፡ በሰሜናዊ ምዕራብ ካምቦዲያ በ30 ሄክታር መሬት ማራኪ ተፈጥሮ ባለው አካባቢ በተገነባ ቤት የተጀመረው ፕሮጀክት በአጭር ጊዜ ወደ ትልቅ መንደር አድጓል፡፡ አንጄሊና ቤቱን የገዛችው ማዶክስን በማደጎ ለማሳደግ ከተቀበለች በኋላ ነው፡፡ ማዶክስ የተወለደበትን ቦታ መርሳት  የለበትም በሚል መነሻ ቁጥራቸው እየተመናመነ ቁጥራቸው እየተመናመነ የመጡ የካምቦዲያን ጥቁር ድቦች፣ ዝሆኖችና የታይላንድ ድንበርን አቋረወጠው የሚመጡትን  ታይገሮች ለመታደግ  ከተቋቋመው  ብሄራዊ ፓርክ አጠገብ ‘’በምሰሶዎች ላይ የቆመ ባህላዊ የካምቦዲያ ቤት’’ ያለቸውን ገዝታለች፡፡

‘’አስደሳች ስራ ያለኝ በመሆኔ እድለኛ ነኝ፡፡ የተለያዩ አካባቢዎችን እንድጎበኝና አንዳንድ ጊዜ እራሴን እንድረሳ የሚያደርገኝ ስራ ነው፡፡ ሁሌ ከእንቅልፌ በነቃሁ ቁጥር ዓለም አቀፍ ህግ አጠናለሁ፡፡ ልጆቼ የእኩልነት ስሜት እንዲሰማቸው ሁሉንም የማያቸው በአንድ መልኩ ነው፡፡ ከምወደው ሰው ጋር ያለኝ ግንኙነት ጠንካራና የተሟላ በመሆኑ ደስተኛ ነኝ፡፡ ሕይወቴ እንግዲህ ይኸው ነው፡፡ ከዚህ የተለየ ወይም ሌላ ሕይወት የለኝም፡፡  ሆሊውድን ወይም ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ነገሮች በተመለከተ ጥላቻ የለኝም፡፡ ስራዬ እስከሆነ ድረስ ሁሉንም ነገር ነገር የምቀበለው በደስታ ነው፡፡ ስሞት ግን፣ ሰው በተዋናይትነቴ እንዲያስታውሰኝ አልፈልግም፡፡ ለቅርብ ጊዜ በፊት ያነበብኩት በአንድ ጋዜጣ ላይ የወጣ ጽሑፍ በስተመጨረሻ  ላይ ተዋናይት መሆኔን አይገልጽም፡፡ የተባበሩት መንግስታት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር እንደሆንኩኝ በመግለጹ ትልቅ ኩራት ተሰምቶኝ፣ ስማ ብራድ፣ ተዋናይት ብቻ አይደለሁም አልኩት’’ ብላለች፡፡

ጋዜጠኞች ስለሷ የሰሟቸውን ወሬዎች በየጊዜው ሲጠይቋት፣ ‘’ስልኬ በየቀኑ ይጮሃል፡፡ በጭራሽ፣  እውነት አይደለም ብዬ ከመለስኩላቸው በኋላ ስልኬን እዘጋለሁ’’ የምትለው አንጄሊና አያይዛም፣ ‘’ስልኬ የሚጮኸው አብዛኛውን ጊዜ ብራድና እኔ ከልጆቻችን ጋር ስልሯሯጥ  የሽንት ጨርቃቸውን ስንለውጥ በመሆኑ ሁሌ እንቀልዳለን፡፡ ከልጆቻችን ጋር ስንጫወት ወደተጠራንባቸው ግብዣዎች ለመሄድ ጊዜው የለንም፡፡ ከቤታችን የምንወጣው እንኳን አልፎ አልፎ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ከኛ ጋር የሚተኛው ፓክስ ነው፡፡ ከኛ ጋር መተኛቱ ምቾት የሚሰጠው እንደሆነ ማወቁ ጥሩ ነው፡፡ ብራድና እኔ እስከተገናኘንበት ጊዜ ድረስ ማዶክስ ከኔ ጋር ይተኛ ነበር፡፡ ልጆቹ አብረውን ሲተኙ ደስ ይለናል፡፡ እሑድ ሁላችንም የምንተኛው አብረን በአንድ አልጋ ላይ ነው፡፡ የተወሰኑ ሰዎች አብረው ከኖሩ በኋላ ልጆች ይወልዳሉ፡፡ እኔና ብራድ ግን፣ ሕይወታችንን የጀመርነው በጋራ ከልጆቻችን ጋር ሲሆን ስናረጅም በዚሁ መልክ እንቀጥላለን’’ ስትል ተናግራለች፡፡

 

ምንጭ፡-እቴጌ ቁ፡- 17 የካቲት  2002