ብጉርን ለማጥፋትና ለመከላከል እራሳችን ቤት ውስጥ ልንጠቀማቸው የምንች

ብጉርን ለማጥፋትና ለመከላከል እራሳችን ቤት ውስጥ ልንጠቀማቸው የምንችላቸው ዘዴዎች

 

Image result for ብጉር

 

ብጉርን ለማጥፋት ከሚከተሉት ዘዴዎች አንዱን ወይም የተወሰኑትን በድርርብ መጠቀም ይቻላል።(ግን አለማብዛት ይመከራል)

1) dermitologists የሚያዙትን ቅባቶች መቀባት:-

ከነዚህ መካከል

- salicylic acid

- retinal product

- benozoll peroxide

አንዳንዶቹ ናቸው።

2) asprin ኪኒን ወቅጦ ትንሽ ውሃ ተጨምሮበት በማደባለቅ ብጉሩ ላይ መቀባት። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ፊትን መታጠብ

3) በረዶ ብጉሩ ላይ ከ20 - 30 ደቂቃ የሚያክል ጊዜ መያዝ

4) ብጉሩ እስኪጠፋ በየቀኑ ተለቅ ባለ ዕቃ የፈላ ውሃ አድርጎ እንፋሎቱ ለተውሰነ ያህል ጊዜ ፊትን እንዲመታ ማድረግ

5) ነጭ ሽንኩርት በደንብ ከትፎ ወይም ለሁለት ሰብሮ ብጉሩ ላይ መቀባት ወይም መያዝ። ከዛ መታጠብ

6) ማር ብጉሩ ላይ ቀብቶ ለሚችሉት ያህል ጊዜ ማቆየት። ከዛ ለብ ባለ ውሃ መታጠብ

7) ፓፓያ ጨፍልቆ ብጉሩ ላይ ተቀብቶ የሚቻለውን ያህል ጊዜ ማኖር። ከዛ በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ

8) የሙዝ ልጣጭ(የውስጡን በኩል) ፊትን ቀብቶ የተወሰነ ያህል ጊዜ ቆይቶ መታጠብ።

9) toothpaste(የጥርስ ሳሙና) (ጄል ባይሆን ይመረጣል) ብጉሩ ላይ(ብጉሩ ላይ ብቻ) በመቀባት ለተወሰነ ጊዜ ማቆየት። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ መታጠብ

 

ከዋና ዘዴዎች አንዳንዶቹ ናቸው

ብጉር እንዳይነሳብዎት በቀላሉ ማድረግ የሚችሏቸው ነገሮች

1)  ፊትን በየቀኑ በመታጠብ ንጽህናውን መጠበቅ

2) ፊት ደረቅ እንዳይሆን moisturizers መጠቀም

3) አለመጨነቅ

4) የትራስ ልብስ ንጽህናን መጠበቅ

5) ውሃ በቂ መጠጣት

6) makeup የሚጠቀሙ ከሆን

"noncomedogenic" የሚል ምልክት ያለበት ፈልጎ መቀባት። noncomedogenic የሆኑ makeup ብጉር አይቀሰቅሱም

7) የተፈበረኩና ቅባት በተለይ ዘይት የበዛባቸው ምግቦች አለማዘውተር

ከዋናዎቹ አንዳንዶቹ ናቸው።

ምንጭ፡- tekamii