ከያኒ ጌትነት እንየው
ጌትነት እንየው በተዋናይነት፣ በአዘጋጅነት እና በጸሐፌ_ተውኔትነት ሁለገብ አስተዋፅኦ ከሚያበረክቱ ከያኒያን አንዱ ናቸው:፡ ጌትነት በ1950 ዓ ም ከአባታቸው ከአቶ እንየው አሰጋኸኝ አና ከእናታቸው ወ/ሮ ውብአለም ዘየለስ ጎጃም ውስጥ በደብረ ማርቆስ አውራጃ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጉጃም፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በጅማ ተምረው በ1974 ዓ ም በቲያትር ጥበባት ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በዲግሪ ተመርቀዋል፡፡ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቲያትር ከተቀጠሩበት ዘመን አንስቶ የተወኗቸው አጫጭርና የሙሉ ጊዜ ተውኔቶች በቁጥር ብዙ ናቸወ፡፡፡ በተጓዳኝ ወጥ ተውኔቶች እና ግጥሞችን ፅፈዋል፡፡ ለምሳሌ ከብዙ በጥቂቶቹ ፦
_ ቁልፉ _ በጌታቸው አብዲ የተጻፈ
_ አሉላ አባነጋ _ በማሞ ውድነህ የተጻፈ
_ ኦማቾቹ _ በኤፍሬም በቀለ የተጻፈ
_ ፍርዱን ለናዓተ _ በተስፋዬ ገሠሠ የተጻፈ
_ የእሪቦኛው ሚዜ _ በመኮንን ዶሪ የተጻፈ
_ ሹሚያ _ በመንግሥቱ ለማ የተጻፈ
_ እንቲ ገን _ ቦሳህሉ ኪዳኔ የተተረጎመ
_ የሺኑሉ ነጋዴ _ በመስፍን ዓለማየሁ የተተረጎመ
_ ውጫሌ አስራ ሰባት _ በታምራት ገበየሁ የተጻፈ
_ ሐምሌት _ በጸጋዬ ገ/መድህን የተተረጎመ
_ በላይ ዘለቀ (ታረካዊ ተውኔት) _ በጌትነት እንየው የተጻፈ
_ ውበትን ፍለጋ _ በጌትነት እንየው የተጻፈ
_ የእግዜር እጣት _ በጌትነት እንየው የተጻፈ
_ እቴጌ ጣይቱ (ታረካዊ ተውኔት) _ በጌትነት እንየው የተጻፈ
_ የቴዎድሮስ ራዕይ (ታረካዊ ተውኔት) _ በጌትነት እንየው የተጻፈ
_ 50 ዓመት ስንት ነው? _ በጌትነት እንየው የተጻፈ
ጌትነት ከተውኔት ሙያ ቸ ው ባልተናነለ በተለያዩ መድረኮች እየተገ ኙ የግጥም ንባብ በማቅረብም ተደና ቂነትን አትርፈዋል ፡፡ በቅርብም በግፍ ለተገደሉት መታሰቢያ “እኝው ነን” በሚል ያቀረበው ግጥም ተጠቃሽ ነው::
ምንጭ፡-ሰዋሰዉ
Related Topics