Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ቦርጭ ለመቀነስ የሚረዱ ምክሮች

 

ቦርጭ ለመቀነስ የሚረዱ ምክሮች

 

Image result for ቦርጭ ለመቀነስ

 

1.   ቁርስ ይመገቡ፡ ይህ የሚጠቅም አይመስልም ግን በጣም አስፈላጊ ነዉ፡፡ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ከእንቅልፋችን በነቃን በአንድ ሰዓት ዉስጥ ቁርስ መመገብ የኢንሱሊን መጠንን ያረጋጋል፡፡

 

-    በቁርስ ሰዓት እንደ እንቁላል፣ አቮካዶና የለዉዝ ቅቤ የመሳሰሉ ባለ ከፍተኘ ፋይበር ምግቦችን መመገብ ለመፈጨት ጊዜ የሚወስዱ በመሆናቸዉ ቶሎ እንዳይርበንና በምሳ ሰዓት ብዙ እንዳንመገብ ያግዙናል፡፡ በዚህም ምክንያት የካሎሪ አወሳሰዳችን ይቀንሳል፡፡

-    ጣፋጭ ቁርሶችን ያስወግዱ፡፡ እንደ ኬክ፣ ፓንኬክ እና ፍሬንች ቶስት የመሳሰሉትን ይተዉ፡፡

 

2.   ዉጥረትን ይቀንሱ፡ ስንጨነቅና ስንወጣጠር በሰዉነታችን ዉስጥ የሚመነጨዉ ኮሪስቶል የተባለዉ ሆርሞን የቦርጭ ሁኔታን እንደሚያባብስ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ዉጥረትን ለመቀነስ የሚረዱ ጥቂት ስልቶች-

 

-    በቂ እንቅልፍ ይተኙ፡፡ የእንቅልፍ እጦት የመነጫነጭ ስሜት ከመፍጠሩም ባሻገር በትንሽ በትልቁ እንድንወጣጠር ያደርገናል

 

-    ፈታ ለማለት ጊዜ ይመድቡ፡፡ ምናልባትም ከምሳ እረፍትዎ ላይ 15 ደቂቃ ወስደዉ ብቻዎን በመሆን ይመሰጡ (አይኖን በመጨፈን በጥልቁ ይተንፍሱ፤ ዉጥረቶን ለመቀነስ ይሞክሩ)፡፡ የሚያስደስቶትን ነገር ያድርጉ- ሙዚቃ ያድምጡ፣ ሻወር ይዉሰዱ፣ ሻማ ያብሩ፣ ዮጋ ይስሩ ወዘተ

 

-    የሚያስጨንቁ ነገሮችን ከመኝታዎ አካባቢ ያርቁ! የቢሮ ወረቀት፣ አሳይመንት የመሳሱትን አልጋዎ ላይ ይዘዉ አይዉጡ፣ ትተዋቸዉ መኝታ ቤት ይግቡ፡፡ አይምሮዎ በተወሰነ መልኩ ነፃ ይሆናል፡፡ የሞባይል አላርምን ለመተዉ ይሞክሩ- ምናልባትም ተፈጥሯዊ ከእንቅልፍ የመነሳት ጥበብን (ለምሳሌ መጋረጃ ከፈት በማድረግ በፀሀይ ብርሃን መንቃት) ይለማመዱ፡፡ ሞባይላቸዉን ከመኝታ የሚያርቁ ሰዎች የተሻለ እንቅልፍ ይወስዳቸዋል፡፡

 

3.  ፈጠን ያለ ወክ ያድርጉ፡ ፈጠን ያለ እርምጃ ማድረግ ቦርጫችንን በእጅጉ እንድንቀንስ ያግዘነል፡፡በተለይም ጂምናዚየም ገብተዉ ለመስራት ጊዜ በማይገኝበት በዚህ ጊዜ ይህ በቀላሉ ልናደርገዉ የምንችለዉ ስፖርት ነዉ፡፡ ሊፍት ከመጠቀም ይልቅ ደረጃዉን በእግር መዉጣት፣ ታክሲ ከመጠቀም በእግር መሄድ (በተለይ ጠዋትና ማታ- እኛ ምን አጋፋን?:)

 

4.   ሙሉ ለሙሉ የላሙ ምግቦችን አይምረጡ፡ በየሰፈራችን ተሰልፈን የምንገዛዉ የፉርኖ ዳቦ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነዉ፡፡ ስንዴ ዉስጥ ያለዉ አስፈላጊ የምግብ ይዘት ተመጦ ያለቀ በመሆኑ ለጤና አይመከረም፤ ይልቁንም ብዙ ሂደት ያልተካሄደባቸዉ እንደ እንጀራና የሐበሻ ዳቦን መምረጥ ተገቢ ነዉ፡፡

 

5.   ብዙ ዉሃ ይጠጡ፡ ብዙ ዉሃ መጠጣት ቦርጭ ለመቀነስ ይረዳል፡፡ ነገር ግን ይህ የሚሰራዉ የሚበሉትን ምግብ መጠን ከቀነሱ ነዉ፡፡ በቀን ዉስጥ እስከ 8 ብርጭቆ ዉሃ መጠጣት ከሰዉነተችን መርዛማ ኬሚካሎች እንዲወገዱም ይረዳል፡፡

 

-    ቤቨሬጅ የሆኑ አልኮሎችን (ቢራ፣ ድራፍት፣ ጠላ፣ ጠጅ…) በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሱ፡፡ ለስላሳዎችን ከቻሉ ይተዉ፤ ቦርጭ ለመቀነስ ብቻ ሳይሆን ለጤናዎም በማሰብ

 

6.  ስፖርት ይስሩ፡ ሩጫ፣ ገመድ መዝለል እና ሌሎች የልብ አቅምን የሚያጎለብቱ እንቅስቃሴዎች ማድረግ ቦርጭን ይቀንሳል፡፡ ቦርጨዎ እስኪጠፋ ድረስ ጡንቻን የሚያዳብሩ አንቅስቃሴዎችን አይስሩ ምክንያቱም ቦርጫችን እንዲጠነክር እንጂ እነዲቀንስ አያደርግም

 

7.   የሚመገቡትም ምግብ ይቀንሱ ግን ይህንን ሲያደርጉ የሚመገቡትን ምግብ ጥራት እና ተስማሚነት ያሻሽሉ፡፡ አትክልትና ፍራፍሬን ያዘዉትሩ፡፡

 

8.   ጥሩ የፋት ምግቦችን ይመገቡ፡ እንደ አቮካዶ፣ ለዉዝ እና ስኳር የሌለዉ ጥቁር ቸኮሌት ሆዳችን አካባቢ ቦርጭ እንዳይከማች ይረዳሉ፡፡ በተቻሎት መጠን እነደ ማርጋሪንና ኩኪስ የመሳሰሉ ምግቦችን ያስወግዱ- ቦርጭን ያባብሳሉ፡፡

 

9.   ቦርጭ ያለዉን ጉዳት ያስቡት፡ በዋነኝነት ቦርጭ መቀነስ የሚገባን አምሮብን እንድንታይ ሳይሆን የጤና ጉዳት ስላለዉ ሊሆን ይገባል፡፡ የልብ ህመም እና ስኳር የመሳሰሉ ህመሞች ቦርጭ ይመቻቸዋል፡፡ ስለሆነም በቅድሚያ ስለጤናችን ብለን ቦርጫችንን ለመቀነስ ከሰራን ዉበቱ ከዚያ አብሮ ይመጣል

 

ተጨማሪ ምክሮች

 

-    ዉሃ ከምግብ በፊትና በኋላ ይጠጡ፡፡ ከምግብ በፊት የሚጠጡት ሆዶን ስለሚሞላሎት ብዙ እንዳይበሉ ይረዳዎታል፡፡ በኋለ የሚጠጡት ሆድ እቃዎን ያፀዳሎታል

 

-    አንድን ምግብ ከመመገብዎ በፊት ለምን ሊበሉ እንደሆነ ያስቡ፡፡ እዉን ርቦት ነዉ ወይስ 6፡00 ወይም 6፡30 ሆኖ የምሳ ሰዓት ስለደረሰ ነዉ የሚበሉት? ካልራበት በቀር ምግቡን አይብሉት፡፡ የመመገብ ዉሳኔያችንን ለሆዳችን እንጂ ለጭንቅላታችን አንስጠዉ፡፡

 

-    ገመድ መዝለል ከሩጫ በላይ ቦርጭን ያጠፋል

 

-    በዛ ያለ ቁርስ፣ መለስተኛ ምሳና ትንሽዬ እራት ይመገቡ፡፡ ለዉጡን ያዩታል፡፡

 

 ምንጭ፡-foodsheal