Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

የፍቅር ህይዎትዎን በስኬት ለማዝለቅ


የፍቅር ህይዎትዎን በስኬት ለማዝለቅ

በህይዎትዎ ደስተኛ ከሚያደርጉ ነገሮች አንዱ ጤናማ የፍቅር ህይዎት መምራት ይጠቀሳል። ለዚህ ደግሞ የእኔ የሚሉትን ትክክለኛ የፍቅር አጋር መምረጥና በፍቅር ህይዎት ውስጥ ልዩነትን ማስወገድ መልካም መሆኑ ይነገራል። እስከ 40 በመቶ የሚደርሱ የፍቅር ግንኙነቶች ባለመግባባት በመለያየት እንደሚደመደሙ የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ። ከዚህ ወጣ ባለ መልኩ ጤናማ የፍቅር ህይዎትን የሚመሩና በግንኙነቶቻቸው ደስተኛ የሆኑ ጥንዶችም በርካቶች ናቸው። ለዚህ አይነቱ ስኬታማ የፍቅር አልያም የትዳር ጉድኝት ደግሞ እንዲህ ብታደርጉ ይላሉ ባለሙያዎቹ። 

በግልጽ መነጋገር፦ ለሁሉም ነገር መነጋገር እና መወያየት ወሳኙ ጉዳይ ነው። የየዕለት ውሎን፣ የስራ ላይ ቆይታን፣ ምናልባት አጋርዎ ያሳለፈውን የምሳ ግብዣ እና መሰል አጋጣሚዎችን የተመለከቱ ጉዳዮችን አጀንዳ በማድረግ መወያየት። ከዚህ ባለፈም በዕለት ውሎ ውስጥ መልካም እና መጥፎ አጋጣሚዎችን የተመለከቱ ውይይቶችን ማድረግም ለሚኖር ጤናማ የፍቅር ህይዎት መልካም ነው። ስለ በጎ ነገሮች ብቻ ሳይሆን ከበድ ስላሉ እና አስቸጋሪ አጋጣሚዎች ጊዜ ወስዶ መወያየቱም ለደስተኛ የፍቅር ህይዎት እንደሚረዳ ነው ባለሙያዎች የሚናገሩት። በማንኛውም አጋጣሚ ከአጋርዎ ጋር በማንኛውም ርዕሰ ጉዳይ ላይ የተወሰነ ደቂቃ ወስደው ይወያዩና ውጤቱን ይሞክሩት። ምናልባት አለመግባባቶች ቢኖሩ እንኳን ስሜትን አላስፈላጊ በሆኑ መንገዶች መግለጹ ትልቁ ችግር ፈጣሪ ነውና ይህን ያስወግዱ ሲሉም ይመክራሉ። ድግግሞሽ አለማብዛት፦ ነገሮችን መደጋገምና ለረጅም ጊዜ ያንኑ ነገር መከወን በፍቅር ህይዎት ውስጥ ለሚከሰት መሰላቸትና አለመግባባት መንስኤ ሊሆን ይችላል። አንድን ነገር መደጋጋም አጋርዎ ከእርስዎ ጋር የሚመራው/የምትመራው ህይዎት አስደሳች ነገር እንደጎደለው ማሰብ እንዲጀምር ያደርገዋል። ምናልባት ሁልጊዜ ማታ ማታ አብራችሁ ራት የምትመገቡበት ቦታን ማዘውተር፥ አጋርዎ ዘወትር በስፍራው የሚያየው ነገር ከጊዜ ብዛት መሰልቸትን ሊፈጥር ይችላልና መሰል ልማዶችን መቀየሩን አይዘንጉ። ከዚህ ውጭም ቤት ውስጥ አልያም ከቤት ውጭ አብረው የሚከውኗቸውን ልማዶች በጥቂቱም ቢሆን መቀየር ለዚህ እንደሚረዳም ባለሙያዎች ያስረዳሉ።


ችግሮችን መቀበል፦ ሁል ጊዜም ቢሆን ከሰዎች ጋር በሁሉም ሃሳብ እና አመለካከት እስማማለሁ ብሎ መጠበቅ አይቻልም። እናም ልዩነቶችን አምኖ መቀበልና የጋራ በሆኑት ጉዳዮች ላይ ጠንክሮ መስራት ያንኑ ማዳበር፥ ችግሮች ባይፈቱ እንኳን አምኖ መቀበል መልካም ነው። ደስተኛ የፍቅር ህይዎት መለኪያው ደግሞ ሁልጊዜም ደስታ ብቻ ሳይሆን ልዩነቶችን አስታርቆ መኖር መቻሉ ላይ ነውና መሰል ጉዳዮችን አምኖ መቀበልን ይልመዱ።ልዩነቶቹ አይጠቅሙም ሳይሆን መሰል ጉዳዮችን እንዴት ማስኬድ እንዳለብዎት ማወቁ እና በሁለታችሁ መካከል ያለውን መልካም ነገር ማጉላትም ለዚህ መፍትሄው ይሆናል።ባልደረባዎን ማክበርና ሃሳቡን ማድመጥ ከወቀሳ ይልቅ ነገሮችን በንግግር መፍታት እና ማስረዳት።


ሰፋ ያለ ጊዜን አብሮ ማሳለፍ፣ አጋርዎ ሃሳቡን ወይም አመለካከቱን እንዲቀይር አለመጠበቅ።ከዛ ይልቅ የሚፈልገውን ነገር ማድረግ እና መከወን፥ ይህ ሲሆን በጊዜ ሂደት የሃሳብ እና አመለካከት መሻሻልን ያመጣልና ይሞክሩት።ከምንም በላይ ቃልን አለማጠፍና ማክበር ደግሞ ለሚኖር ጤናማ ግንኙነት የመጀመሪያው መንገድ ነው።ምንጊዜም ቢሆን ለአጋርዎ ታማኝና ቃል አክባሪ ይሁኑ፥ ያንን ማድረጉ መልካም የፍቅር እና የትዳር ጊዜ እንዲኖር ያስላልና ታማኝ ይሁኑ።

ምንጭ፦ http://www.apa.org/