ፕሪንተር ሲሰራ ቆይቶ አላትምም የሚሉባቸዉ ምክንያቶች ምንድን ናቸዉ

ፕሪንተር ሲሰራ ቆይቶ አላትምም የሚሉባቸዉ ምክንያቶች ምንድን ናቸዉ

 

Image result for printer

 

ፕሪንተሮች ሲሰሩ ቆይተዉ አላትምም የሚሉባቸዉ ምክንያቶች በርካታ ናቸዉ፡፡ በውስጣዊና በዉጫዊ ችግሮች ብለን ከፍለን ልናያቸዉ እንችላለን፡፡ውስጣዊ ችግሮች ከሚባሉት ውስጥ በማወቅ ሆነ ባለማወቅ ፕሪንተሩን ከኮምፒዉተሩ ጋር ተስማምቶ እንዲሰራ የሚያደርገዉ driver softeware በተጠቃሚዉ አማካኝነት ሲጠፋ (delete ሲያደርግ) እና ይህ ፕሮግራም ኮምፒዉተር ባጠቃዉ ቫይረስ እንዳይሰራ  ሲደረግ ወይም እንዲቀሳቀስ (startup እንዲያደርግ) የሚያግዘዉ የሶፍትዌር አካል ሆኖ ተብሎ በቫይረሱ እንዲጠፋ ሲደረግ ነዉ፡፡

ውስጣዊ  በችግሮች ከሚባሉት ደግሞ ከኮምፒዉተሩ ወደ ፕሪንተሩ መልክት ይዞ የሚጓዘዉ ገመድ (data cabel)ሲቋረጥ በመሰኪያ ጫፎች (pins) ላይ ጉዳት ሲደርስ ወይም ሲሰበሩ በዋነኝነት ይከሰታል፡፡ ስለሆነም ፕሪንተር አላትም ሲል ከኮምፒዉተሩ ኋላ የተሰካዉን ገመድ በየጊዜዉ እየሰኩና እየነቀሉ መጠቀም ጉዳት ያስከትላል፡፡ ዘመናዊ ፕሪንተሮች ስለሚጠቀሙ ከዚህ ችግር የጸዱ ናቸዉ፡፡ የኤሌትሪክ ሀይል የሚያመጣዉ ገመድ ላይ ጉዳት ከደረስ ፕሪንተሩ ሊነሳ ስለማይችል ምንም አይነት ትዕዛዝ ተቀብሎ ሊያትም አይችልም፡፡

የፕሪንተሩ የቀለም ቋት (Toner) ጥርሶቹ መበላት ሌላዉ ችግር ነዉ፡፡ ይህ ችግር ነዉ፡፡ ይህ ችግር ከተከሰተ ፕሪንተሩ ሲያትም ድምጽ ያወጣል፡፡ ሌላኛዉ እና ብዙዎቻችን ልብ የማንለዉ ችግር ፕሪንተሩ ውስጥ ወረቀቱ ሲቀረቀር (Jam) ፕሪንተሩ ማተም የማይችል መሆኑ ነዉ፡፡ የተጨማደዱ እና የተቀዳደዱ ስስ ወረቀቶች ፕሪንተር  ውስጥ ማስገባት ችግሩን ይፈጥራል፡፡ የፕሪንተሩ የቶነሩን በማውጣት የተቀረቀረዉን ወረቀት ሣይበጫጨቅ ያዉጡት፡፡ፕሪንተርዎን በማይጠቀሙት ጊዜ ያጥፉት፡፡ እድሜዉ ይረዝምልዎታል፡፡

ምንጭ፡- አዲስ ጉዳይ 2002 ዓ.ም

 

  

Related Topics