ከ6 ወር በኋላም ከተጨማሪ ምግቦች ጋር ቢያንስ እስከ አንድ ዓመት ያህል ጊዜ

ጡት የማጥባት ጥቅሞች 

 

                                                       

 

• የእናት ጡት ወተት ለጨቅላ ሕፃናትም ሆነ እጅግ ከፍተኛ ጠቃሚ የሆነ ለልጅዎ የምግብ ዓይነት ሲሆን ጨቅላ ሕፃናት ከተወለዱ ከ1 ሰዓት በኋላ ጀምረው ለተከታታይ 6 ወራት የጡት ወተት ብቻ መጥባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከ6 ወር በኋላም ከተጨማሪ ምግቦች ጋር ቢያንስ እስከ አንድ ዓመት ያህል ጊዜ ማጥባት ያስፈልጋል፡፡

ጡት የማጥባት ጥቅሞች፡-

ለሕፃኑ

• ከተለያዩ ኢንፌክሽን አምጪ ተሕዋሲያን ይከላከላል እነዚህም፣

1) ተቅማጥ

2) ሳንባ ኢንፌክሽን

3) የጆሮ ኢንፌክሽን

4) የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን

• ለአለርጂ እና አስም ተጋላጭነት ይቀንሳል

• ለስኳር ሕመም ተጋላጭነትን ይቀንሳል

• ለአጥንት ጥንካሬ እና ዕድገት ይረዳል

• ለአእምሮ ዕድገት ጠቀሜታ አለው

• በአፍ ውስጥ ለሚገኙ ጡንቻዎች ጥንካሬ እና ለፊት ጡንቻዎች እድገት ይጠቅማል

• ጤናማ ዓይን እንዲኖራቸው ይረዳል

• የሆድ ድርቀት ይከላከላል

• በሽታን የመከላከል አቅም እንዲኖራቸዉ ያደርጋል

ለእናቲቱ፡-

1. በእናት እና ልጅ መካከል ያለውን ትስስር ይጨምራል

2. ለጡት ካንሰር ሕመም ተጋላጭነት ይቀንሳል

3. ለማኅፀን ካሰር ሕመም ተጋላጭነት ይቀንሳል

4. የአጥንት መሳሳትን ይከላከላል

በእርግዝና ምክንያት የመጣውን የሰውነት ክብደት ይቀንሳል

 

ምንጭ፡-: Health ጤና

 

  

Related Topics