Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

የሳምባንና የልብ አሰራርን እንዲሁም የአተነፋፈስ ስርዓትን ያሻሽላል

የአካል በቃት እንቅስቃሴ ጠቀሜታዎች

 

የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች መጠነ ሰፊ ጠቀሜታ ያላቸዉ ሲሆን በዚህ አምድ ስር ዋና ዋናዎቹ እንደሚከተለዉ ተገልፀዋል፣

1. በሁሉም የእድሜ ክልል መሰራት የሚችል ከመሆኑም በላይ ጤናማ እና ረጅም እድሜ ለመኖር ያስችላል፤

2. ከልብ ጋር በተያያዘ የሚመጡ በሽታዎችን፣ እንደ የደም ግፊት ኮሌስትሮል፣ የስኳር በሽታ  እና በተወሰኑ የካንሰር ዓይነቶች የሚመጡ አደጋዎችን (ችግሮችን) ይከላከላል፣ይቀንሳል፤

3. የተመጣጠነና ጤናማ የሰውነት ክብደትና ቅርጽ እንዲኖረን ያስችለናል፤

4. ለአጥንት ጥንካሬ ይጠቅማል፡፡ የሰው ልጅ በ35ኛው የእድሜ ክልል አካባቢ የአጥንቱ ክብደት (Bone mass) እየቀነሰ ይመጣል ይህ ሂደት የአጥንት መሳሳት (Osteoporosis) ያመጣል፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች እንደ ክብደት ማንሳት፣ እርምጃ እና ሩጫ የመሳሰሉት ለአጥንት ጥንካሬን ከማምጣት አንፃር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው፤

5. የጀርባ ህመምን ይከላከላል፡፡ የታችኛውን የጀርባ ክፍልና የሆድ ጡንቻዎችን በማጠንከር የጀርባ ህመምን መከላከል ይቻላል፤

6. አየራዊ (ኦክስጅንን በመጠቀም) የሚሰሩና እንደክብደት ማንሳት የመሳሰሉ የጥንካሬ እንቅስቃሴዎች የሰውነትን የበሽታ የመቋቋምአቅምን ያጐለብታሉ፤

7. ሥርዓተ-ልመትን /digestion/ ያፋጥናል፤

8. የተመቸ እንቅልፍ ለማግኘት ያስችላል። መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያዘወትሩ ሰዎች ከማያዘወትሩት የተሻለና ምቹ የእንቅልፍ ጊዜ በማግኘትና በመንቃት የተሻሉ ናቸው፡፡

9. አንዳንድ መጽሀፎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የአእምሮን ትክክለኛ ሥራ ለማጐልበት እና እንደ አልዚመር (Alzheimer) የመሳሰሉ የአእምሮ በሽታን ለመከላከል እንደሚረዳ ያስቀምጣሉ፤

10. የሳምባንና የልብ አሰራርን እንዲሁም የአተነፋፈስ ስርዓትን ያሻሽላል፤

11. የደም ዝዉዉር እንዲጨምር ያደርጋል፤በዚህም ኦክስጅንና ንጥረ ምግብ ለተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ህዋስ /Tissue/ በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲደርስ ያስችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ሰዉነታችን/አካላችን ስራዉን በትክክል አና በተገቢዉ ሁኔታ ያከናዉናል፤

12. በአጠቃላይ የሰውነት የአሠራር ስርዓትን ያሻሽላል፡፡ ታዲያ ይህንና የመሳሰሉትን ጠቀሜታዎች በዉስጡ አቅፎ የያዘዉን የአካል ብቃት ጠለቅ ብሎ ማወቅና ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ነዉ፡፡ የአካል ብቃት ምንድን ነው? የአካል ብቃት በተለያዩ ምሁሮች የተለያየ ትርጓሜ የተሰጠው ሲሆን የአብዛኞቹ ተመሳሳይነት ያለዉ ነው፡፡ የአካል ብቃት፡ አካልንና አእምሮን አቀናጅቶ አንድን ተግባር በትክክልና በብቃት ያለ ድካም ማከናወን የመቻል ሂደት ማለት ነው፡፡

 የአካል ብቃት ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች አሉት፤

1. ከጤና ጋር ግንኙነት ያላቸው የአካል ብቃት ክፍሎች /Health related physical fitnesscomponents/

2. ከብቃት /ክህሎት ጋር ግንኙነት ያላቸው የአካል ብቃት ክፍሎች /Skill or performancerelated physical fitness components/ናቸዉ፡፡

1. ከጤና ጋር ግንኙነት ያላቸው የአካል ብቃት

ክፍሎች በአምስት ይመደባሉ እነሱም፡-

ሀ. የጡንቻ ጥንካሬ /Muscular strength/

ለ. የጡንቻ ብርታት / Muscular endurance/

ሐ. የልብ፣የሳምባና የደም ቧንቧዎች ብርታት /

cardiovascular endurance/

መ. የሰዉነት መተጣጠፍ /Flexibility/

ሠ. የሰውነት የስብና ጡንቻ ምጥጥን /body

composition/ ሲሆኑ፤

2. ከብቃት /ክህሎት ጋር ግንኙነት ያላቸው

የአካል ብቃት ክፍሎች ደግሞ፡

ሀ. ፍጥነት /Speed/

ለ. ሚዛንን መጠበቅ /Balance/

ሐ. ማቀናጀት /Coordination/

መ. ቅልጥፍና /Agility/

ሠ. ጉልበት /Power/

ረ. ቅጽበተ-ምላሽ /Reaction time/ ናቸው፡፡

ከጤና ጋር ግንኙነት ያላቸው የአካል ብቃት ክፍሎች መግለጫ

ሀ. የጡንቻ ጥንካሬ /Muscular strength/፡

የጡንቻ ጥንካሬ በጡንቻዎች የአንድ ጊዜ መኮማተር የሚፈጠር የኃይል /ጉልበት/ መጠን ወይም የሰውነት የኃይል ማመንጨት ችሎታ ማለት ነዉ፡፡ ለማንሳት፣ለማንቀሳቀስ ወይም ለመተግበር ጠቀሜታ አለው፡፡ ጥንካሬ ለሁሉም ዓይነት ስፖርቶች በተለይም ለአትሌቲክስ የውድድር ተግባራት በተለያየ መጠን ለሁለቱም ፆታዎች አስፈላጊ ነው፡፡ በጡንቻ ውስጥ የሚገኘው የጡንቻ ክር /Muscle fibber/ የክብደት ማንሳት/resistance/ ልምምድ ወይም እንቅስቃሴ ሲደረግ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ ይህ ምላሽ ጡንቻዎችን ለሥርዓት ነርቭ ሥራ የተሻለና ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡና የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። ይህ ደግሞ ፈቃደኛ ጡንቻዎች /voluntary muscles/ /ለምሳሌ የአጥንት ጡንቻዎች/ ሥራቸውን በተገቢው ሁኔታና በፍጥነት

እንደያከናውኑ ያስችላቸዋል፡፡

 ጥንካሬ በሶስት ዓይነት ይከፈላል

1. ከፍተኛ ጥንካሬ /maximum strength/ ማለት አንድ የተኮማተረ ጡራቻ ሊፈጥረው የሚችለው የመጨረሻ ከፍተኛ ኃይል ማለትነው፡፡

2. ተለጣጭ/ተለስታኪ ጥንካሬ /ኃይል /Elastic strength/ ማለት የጡንቻዎች የመኮማተር ፍጥነትና የእንቅስቃሴ ጥምረት ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ጉልበት/power/ በመባል ያታወቃል፡፡

3. የጥንካሬ ብርታት /Strength Endurance/ የሰውነት የጡንቻዎች ኃይል በማመንጨት የመቀጠል ችሎታ ነው፡፡ የዚህ ጥንካሬ ባህሪ ረዘመ ላለ ጊዜ በተደጋጋሚ በሚደረጉ አካላዊ እንቅስቃሴዎች ላይ የአትሌቱን ብቃትና ውጤታማነትን የሚወስን ነዉ፡፡

ለ. የጡንቻ ብርታት /muscular endurance/

የሰውነት ጡንቻ ወይም ጡንቻዎች አንድን እንቅስቃሴ ወይም ተግባር በተደጋጋሚ ያለ ድካም ለረጅም ጊዜ የማከናወን ሂደት ነው። በተለይ በአትሌቲክስ ዘርፍ ለሚሰማሩ አትሌቶች በረጅም ጊዜ ግብ ወይም ዓላማ የሚሳካ እንደመሆኑ መጠን በእለት ከእለት እንቅስቃሴ ውሰጥ ረዘም ያለ ጊዜ የሚወስድ ርቀት ያላቸውን የአትሌቲክስ ዘርፎች ለማከናወን ከአካል በቃት አንዱ የሆነውን ብርታት ማዳበር ይጠበቅባቸዋል፡፡ብርታት ከሌሎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች በፊት መዳበር ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም ሌሎች የልምምድ ዓይነቶችን ደጋግሞ መስራት አስቸጋሪ ከመሆኑም በተጨማሪ የአካል ብቃት ክፍሎችን በሚፈለገው መጠን ማዳበር በጣም አዳጋች ስለሚሆንነው፡፡

 ብርታት በሁለት ይከፈላል፤

1. አየራዊ ብርታት /Aerobic endurance/

አየራዊ ማለት ከኦክስጅን ጋር ማለት ሲሆን አየራዊ ብርታት ማለት ኦክስጅንን በመጠቀም ለጡንቻ ሥራና እቅስቃሴ የሚሆን ኃይል ረዘም ላለ ጊዜ ማመንጨት ማለት ነው፡፡ አየራዊ ብርታት ልምምድ ወደ ልበ-ትንፈሳ ሥርዓት / cardio-respiratory system/ ማጠናከርና በጡንቻ ውስጥ ያለውን አየር /Oxygen/ የመጠቀም ችሎታን ወደ ማስጨመር ያመራል። አየራዊ ብርታት በተቆራራጭና ወጥ የሩጫ ልምምድ /continuous and interval training/ ማዳበር ይቻላል፡፡

2. ኢ-አየራዊ ብርታት /Anaerobic endurance/

 

ኢ-አየራዊ ማለት ያለ ኦክስጅን ማለት ነው። በሰውነት ውስጥ ተከማችቶ የቆየን ኃይል  በመጠቀም ጡንቻዎች እንዲሰሩ የሚፈቅድ የኃይል ሥርዓትን የሚገልጽ ነው፡፡ በተለይ እንደ ሽምጥ ላሉ ሩጫዎች በጣም ጠቃሚ ነዉ፡፡ ኢ-አየራዊ ብርታትን በድግግሞሽ የሩጫ ልምምድ /repetition training/ ማዳበር ይቻላል፡፡

ሐ. የልብ፣የሳምባና የደም ቧንቧዎች ብርታት / cardiovascular endurance/

የልብ፣የሳምባና የደም ቧንቧዎች ብርታት ማለት፡ ልብ፣ሳንባና የደም ቧንቧዎች በቂ የሆነና በኦክስጂን የበለጸገ ደም ቀጣይነት ባለዉ የአካል እንቅቃሴ ሂደት በስራ ላይ ላለ ጡንቻ ማድረስ መቻል ማለት ነዉ፡፡ የዚህ ብርታት መጎልበት የልብ ጡንቻ መጠንከርና በመጠን መጨመርን፤ የሳምባ አየር የመያዝ አቅም እና የደም ቧንቧዎች የመለጠጥ አቅም ማደግን የሚያስችል ሲሆን፤ደም እና ኦክስጂን በተገቢዉ ሁኔታ ለሰዉነት ክፍል በበቂ መጠን እንዲደርስ፤ እንዲሁም የደም ቧንቧዎች ከልብ የሚወጣዉን ደም በቀላሉ የመቀበልና የማድረስአቅምን ይፈጥራል፡፡

መ. የሰዉነት መተጣጠፍ /Flexibility/

 የሰዉነት መተጣጠፍ ማለት የሰውነት የመገጣጠሚያ ክፍሎችን መጠነ ሰፊ በሆነ ተፈጥሮአዊ የእንቅስቃሴ መጠን/range of motion/ የማንቀሳቀስ ችሎታ ነው፡፡ እያንዳንዱ የሰዉነት መገጣጠሚያ የተለያየ የሰዉነት መተጣጠፍ መጠን/ደረጃ አለዉ፡፡ ስለዚህ የመተጣጠፍ እንቅስቃሴዎችን በምናሰራበት ወይም በምንሰራበት ወቅት ይህንን የተለያየ የአካል ክፍሎች የሰዉነት መተጣጠፍ ደረጃ ከግምት ዉስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነዉ፡፡

ሠ. የሰዉነት የጡንቻና የስብ ምጥጥን /Body composition/

የሰዉነት የጡንቻና የስብ ምጥጥን ማለት የሰዉነት ከስብ ነጻ የሆነዉ ክፍል ማለትም ጡንቻ፣አጥንት፣ደም፣የዉስጥ አካል ክፍሎችና የሰዉነት ፈሳሾች/muscle, bone, blood, organs, and fluids/ እና ስብ የሆነዉ ክፍል /adipose tissue/ ምጥጥን ማለት ነዉ፡፡ ይህ የሰዉነት አካል ክፍል የስብና የጡንቻዎች ምጥጥን ተከታታይ በሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች የሚስተካከልና የሚደረጅ ሲሆን፤ሰዉነት የተስተካከለና ዉብ የሆነ አቋም እንዲኖረዉ ከማስቻሉም በላይ ከሰዉነት የስብ መጨመር ጋር ተያይዞ ከሚመጡ ችግሮችና በሽታዎች እንደ የደም ቧንቧ መጥበብ፣የልብ በሽታ አና የመሳሰሉትን ለመከላከል ያስችላል፡፡

ምንጭ፡-/media/Booklet