በተደጋጋሚ በስራ ቃለመጠይቅ/ ኢንተርቪው ጊዜ የሚጠየቁ ጥያቄዎች፡፡

 

በተደጋጋሚ በስራ ቃለመጠይቅ/ ኢንተርቪው ጊዜ የሚጠየቁ ጥያቄዎች፡፡

በተደጋጋሚ በስራ ቃለመጠይቅ/ ኢንተርቪው ጊዜ የሚጠየቁ ጥያቄዎች፡፡ በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ወደ 30 የሚደርሱ ጥያቄዎችንና ልትሰጡ የሚገባቸውን ምላሾች እንዲሁም ማድረግ የሚገባችሁን ጥንቃቄ በተመለከተ

10 ያህሉን ይዘናል 

1- እስኪ ስለራስህ ንገረን?
ይህ ጥያቄ እንዲሁ በግርድፉ ሲታይ ቀላል ይመስላል ይሁን እንጂ ብዙዎች ገና ከጅምሩ ስህተት የሚሰሩበት ነው፡፡ ብዙ ተጠያቂዎች ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚመስላቸው ስለራሳቸው የህይወት ታሪክ ማውራት ነው ፡ ይሁን እንጂ እንዲያ ለማለት ሳይሆን በስራ ህይወት ላይ ስላለህ ማንነት ፡ የስራ ልምድ ካለህ በዚያኛው የስራ ቦታ ስላስመዘገብካቸውና ስለሰራሀቸው ጥሩ ስራዎች እንዲሁም ጀማሪ ተቀጣሪ ከሆንክ በዩኒቨርሲቲ ቆይታህ ስለነበረህ መልካም እንቅስቃሴ ወይም ስለሰራኸው የመመረቂያ ፕሮጀክት ልታወራ ትችላለህ፡፡ በንግግርህም ወቅት ጠያቂው የመጀመሪያ ምርጫው እንድትሆን ጠቃሚ ነገሮቹ ላይ ትኩረት አድርግ፡፡

2- ስለዚህ የስራ መደብ እንዴት ሰማህ?
ሌላው በተደጋጋሚ የሚጠየቀው ጥያቄ ይሄ ነው ፡ በዚህ ወቅት ማድረግ የሚገባችሁ ነገር በትክክል ስለዚህ የስራ
መደብ የሰማችሁበትን ቦታ በግልፅ ተናገሩ


3- ስለመስሪያ ቤታችን ምንተውቃለህ?
ይህ ጥያቄ ለጠያቂው የሚሰጠው ትልቅ መልዕክት አለ ፡ በተቻለ መጠን ወዳመለከታችሁበት መስሪያቤት ከመሄዳችሁ በፊት ስለ መስሪያቤቱ በቂ ግንዛቤ ሊኖራችሁ ይገባል ፡ ተልዕኮውን, አላማውን, ራዕዩን በግልፅ ልትረዱ ይገባል እናንተም በዚሁ መስሪያቤት ተልዕኮ አላማና ራዕይ ውስጥ ልታበረክቱ ስለምትችሉት ነገር በአጭሩ ተናገሩ፡፡
ያመለከታችሁበት መስሪያ ቤት ድህረገጽ ካለው About የሚለውን በመጫን መረጃውን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ አልያም በአንዳንዶቹ ዘንድ ገና ወደ ግቢያቸው ስትገቡ ተገቢውን መረጃ በሆነ ቦርድ ወይም በአንዳች ነገር በግልፅ ተፅፎ ታገኙታላችሁ፡፡
ለዚህ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ለስራው የሰጣችሁትን ትኩረት ያሳያል፡

4- ለምን እዚህ መቀጠር ፈለክ ?
ብዙውን ግዜ ቀጣሪዎች በቅጥር ወቅት ሊቀጥሩ የሚፈልጉት በተቻለ መጠን ልህቀቱ ጥሩ የሆነውን ሰው ነው እናም ለሚጠየቀው ጥያቄ አሳማኝ መልስ መስጠት አንዱ ማሳያ ነው፡
★የእናንተ መስሪያ ቤት ትኩረት አድርጎ በሚሰራባቸው ዘርፎች ላይ ብሳተፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደማበረክት ስላመንኩኝ፡፡
★ መስሪያ ቤቱ ትልቅ እና መልካም እንቅስቃሴዎችን እያስመዘገበ በመሆኑ እኔም የዚህ አካል መሆንን ስለምፈልግ፡፡
★ ያመለከታችሁበት መስሪያ ቤት የሚሰጠውን አገልግሎት በመለየት እንደዚያ አይነት ግልጋሎት የሚሰጡ ቦታዎች ላይ መሆን በህይወታችሁም ላይ እንዲሁም ለህሊነሠችሁ የሚሰጠውን እርካታ ተናገሩ፡፡


5- ለምን አንተን እንቀጥርሀለን?
እንዲህ የሚል ጥያቄ ከተጠየቃችሁ አልፈለጉኝም ማለት ነው ብላችሁ እንዳትደነግጡ ይልቁን ደስ ሊላችሁ ይገባል ምክንያቱም በጠያቂው ዘንድ ጥሩ ቦታን አግኝታችኃል ማለት ነው ፡ እናም በዚህ ወቅት
★ እናንተን በመቅጠራቸው በመስሪያ ቤቱ ጉዞ ላይ የእናንተን አቅም በመጨመር ተገቢውን አገልግሎት እንደምትሰጡ፡፡
★ በቡድን እንቅስቃሴ ውስጥ የቡድኑን አንድነት በማጠናከር ለመስሪያቤቱ እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደምታበረክቱ ተናገሩ፡፡
እንዲሁም መሰል ምላሾችን አክበት፡፡


6፡ በሙያህ ጠንካራ ጎኖች አሉኝ ብለህ የምታምናቸው ነገሮች ምንድናቸው?
★ ያሉህን እውነተኛ ጥንካሬዎች ተናገር ፡ እንዲኖርህ የምትፈልገውን ሳይሆን ያለህን ነገር፡፡
★ ከምትወዳደርበት የስራ መደብ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሙያዊ ጥንካሬዎችን አስቀድም፡፡


7- ድክመቶችህ ምን ምን ናቸው?
ሀለሉም ሰው ድክመቶች ቢኖሩበትም ቅሉ በስራ ቃለ መጠይቅ ወቅት እኒህ እኒህ ድክመቶች አሉብኝ ብሎ መናገር አይመከርም ይልቁን የሚታይ ድክመት አለብኝ ብዬ አላምንም ለዚህም ማስረጃ የሚሆነኝ እኔ ባለብኝ ድክመት ምክንያት ነገሮች ተበላሽተውበኝ አለማወቃቸው አንዱ ማሳያዬ ነው ብሎ መመለስ ተገቢ ይሆናል፡፡

8- በሙያህ ያስመዘገብከው ስኬት ምንድነው?
አሁን ልትቀጠርበት ባለው የሙያ ዘርፍ ቀደም ብለህ ያስመዘገብከውን ውጤት ተናገር ፡ የሰራኸውን ነገር መናገር ጉራ አይደለምና ዘና ብለህ ስላበረከትከው ነገር አውራ ፡ ጀማሪ ተቀጣሪም ከሆነክ መመረቂያህ ተግባራዊ ተደርጎ ተሰርቶ ከሆነ እሱን ጥቀስ፡


9-ቀደም ብሎ በነበረህ የስራ ወቅት የገጠመህ ግጭት ወይም አለመግባባት ነበር ወይ? ከገጠመህስ እንዴት ፈታኸው?
አስተውል ጠያቂህ ይህን ጥያቄ የጠየቀህ ስለአንተ ጀብድ ወይም ሌላ ለመስማት ሳይሆን፡ ለችግሮች ምላሽ የምትሰጥበትን መንገድ ለማወቅ ነው ፡ እናም ጉዳዩ ገጥሞህ ከሆነ የፈታህበትን መንገድ ጥበብ በተሞላበት መልኩ መልስ፡፡


10- ከአምስት አመት በኃላ እደርስበታለሁ ብለህ የምታስበው ራዕይ ምንድነው?
የምር ራዕያችሁ የሆነውን ነገር መናገር ተገቢ ነው ፡ ልትደርሱበት የምትፈልጉበትን ቦታ ግልፅ መሆኑን ሊለካ እና ሊደረስበት የሚችል ነገር ተናገሩ ፡ በዛው መስሪያ ቤት እስከ መጪዎቹ አምስት አመታት የመቆየት ሀሳብ ካላችሁ በዛ መስሪያቤት የት ቦታመድረስ እንደምትፈልጉ ጭምር ተናገሩ፡ ይህም ከእነርሱ ጋር የረጅም ጊዜ እቅድን አንግባችሁ እንደመጣችሁ እንዲረዱ ያደርጋቸዋል፡ እናም ከሌሎች ተወዳዳሪዎች በተሻለ ትኩረት እንድትስቡ ያደርጋችኃል ማለት ነው፡፡


እንግዲህ እነኚህንና የመሳሰሉትን ነገሮች ተግባራዊ ማድረግ በቃለመጠይቅ ወቅት የተሻለ ማንነት እንድትላበሱ ያደርጋችኃል ብለን እናስባለን፡፡ 

               ምንጭ፦ ‪#‎ዳናታይም