የወንዶች የውበት መጠበቂያ ዘዴዎች የተስተካከለ የቆዳ ሁኔታ

የወንዶች የውበት መጠበቂያ ዘዴዎች  የተስተካከለ የቆዳ ሁኔታ

 

Image result for የወንዶች የውበት መጠበቂያ

 

ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የተዋበና የተስተካከለ ቆዳ እንዲኖራቸዉ ይፈልጋሉ ፣ ለዚህ ነዉ ቫዝሊን ለወንዶች የቆዳ ውበት አጠባበቅ ልዩ ትኩረት የሚሰጠዉ፡፡ በጸሀይ ቃጠሎ፣ በጉዳት፣ ወይም በብጉርና በመሳሰሉ ነገሮች ምክንያት ወንዶች ጥቋቁር የቆዳ ላይ ነጠብጣቦችና የተዥጎረጎረ የቆዳ ቀለም ይበዛባቸዋል፡፡ቆዳን በመንከባከብ ረገድ ባላቸው ደካማ ልምድና በዕድሜ መጨመር ምክንያት ወንዶች አስቀያሚ የፊት ገፅታን ለመለወጥ ይቸገራሉ፡፡ ይሁንና በ Vaseline MEN በመታገዝ በእርግጠኝነት ጥቋቁር ነጥብጣቦችንና ቡራቡሬ የቆዳ ቀለሞችን ከቆዳ ላይ ማስወገድ ወይም መቀነስ እንችላለን፡፡

 

በተለያዩ ምክንያቶች ቆዳ ላይ ጥቋቁር ነጥብጣቦች ሊወጡ ይችላሉ፡፡ አንዱና ዋነኛው ችግር የፀሃይ ቃጠሎ ነው፡፡ አትዮጵያ ዉስጥ ሲኖሩ ደግሞ አብዛኛዉን ጊዜ ከቤት ውጪ ጸሐይ ላይ ማሳለፍ የተለመደ ነዉ፡፡ ምንም እንኳ የጸሐይን ሙቀት ቢወዱትም የፀሃይ ብርሃን አደገኛ ጨረሮች ቆዳዎ ዉስጥ ዘልቀው የመግባት ሃይል ያላቸውና ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሱ ጨረሮች ናቸው ፡፡ ሰዉነታችን ይህን የቆዳ ጉዳት ለመከላከል ሜላኒን የተሰኘዉን (ለቆዳ ቀለም የሚሰጥ) ንጥረ ነገር ያመርታል ፡፡ በዚህም የተነሳ ጥቋቁር ነጠብጣቦች ቆዳ ላይ መውጣት ይጀምራሉ፡፡ ይህ ክስተት ጠቆር ባለ ቆዳ ላይ ይበልጥ ይጎላል፡፡

 

በጉዳት ምክንያት የተከሰቱ ጠባሳዎችና በፈረጡ ብጉሮች ፣ እንዲሁም ቆዳ ውስጥ በበቀሉ ፀጉሮች የተነሳ ቆዳ ላይ ጥቋቁር ምልክቶችና ነጠብጣቦች ሊወጡ ይችላሉ፡፡ በዚህ የተነሳ ሁሉም ነገር ያበቃለት ሊመስልዎ ይችላል፡፡ ይሁንና ጤነኛ ቆዳ እንዲኖርዎ ለማድረግ አሁንም ዕድሉ አለዎት፡፡

 

ውብና የተስተካከለ ቀለም ያለው ቆዳ ይኖርዎት ዘንድ የሚረዱ አንዳንድ ጥቆማዎችን እንደሚከተለው አቅርበንልዎታል፡፡

 

በየዕለቱ ቆዳዎ ርጥበት እንዲኖረው ያድረጉ

እንደ አካልዎ ሁሉ የሰውነትዎ ቆዳም ርጥበቱ እንዲጠበቅለት ይፈልጋል፡፡ ውሃ በመጠጣት የሰውነትን የውሃ ፍላጎት ከማሟላት በተጨማሪ ቆዳ በሎሽኖች አማካይነት ርጥበቱ የተጠበቀ መሆን አለበት፡፡ ቆዳን የሚያለሰልሱ፣ ጥቋቁር ነጠብጣቦችን የሚቀንሱና ዥጉርጉር የቆዳን ቀለም የሚያስተካክሉ የቆዳ መንከባከቢያ ምርቶችን ተጠቅመው የፊትዎንና የመላ ሰውነትዎን ርጥበት በመጠበቅ የቆዳ ድርቀትን ይከላከሉ፡፡

 

ጤናማ አመጋገብን ያዘወትሩ

ትኩስ ፍራፍሬና አትክልቶች የሰውነት ህዋሳትን ደህንነት በመጠበቅ ጉዳትን የመከላከል አቅማቸውን ሲያጎለብቱ፣ የዶሮ ስጋና አሳ የመሳሰሉ በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦች ደግሞ ቆዳን ዳግም ወደውበቱና ጤናማ ድምቀቱ በመመለስ ረገድ ትልቅ ጠቀሜታ አላቸው፡፡

 

በቂ ውሃ ይጠጡ

የህክምና ባለሞያዎች በቀን ከስድስት እስከ ስምንት ብርጭቆ ዉሃ መጠጣት የሰውነትዎ ርጥበት እንዲጠበቅና መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ከሰውነትዎ እንዲወገዱ ለማድረግ ያግዛል ሲሉ ይመክሩዎታል፡፡ ይህን ያህል ውሃ መጠጣት እንደሚበዛብዎ ያስቡ ይሆናል፡፡ ይሁንና ከምግብ በፊትና በኋላ አንድ አንድ ብርጭቆ ውሃ ቢጠጡ ራት ሰዓት ላይ ሲደርሱ በቀን ስድስት ብርጭቆ ውሃ ለመጠጣት ቻሉ ማለት ነው፡፡ በቂ ውሃ መጠጣት በድርቀት የተጎዳን ቆዳ ለመታደግም ሁነኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

 

ቆዳዎ የሚያስፈልገው ርጥበት…ርጥበት…ርጥበት

በቀዝቃዛ ወራት ቆዳ ተፈጥሯዊ እርጥበቱን በፍጥነት ያጣል፡፡ ይህ ደግሞ ቆዳዎን ከጉዳት የሚጠብቀውን የላይኛውን የቆዳ ሽፋን ለጉዳት ይዳርጋል፡፡ በዚህ ወቅት የወትሮውን የቆዳዎን ልስላሴና ምቾት ለመጠበቅ ከሌላው ጊዜ በበለጠ ሎሽን መጠቀም ሊያስፈልግዎት ይችላል፡፡ ቦርሳዎ ውስጥ ሎሽን በመያዝ፤ በስራ ቦታዎም መሳቢያ ውስጥ ሎሽንዎን በማስቀመጥ እንዲሁም ሰዎነትዎን ከታጠቡ በኋላና ከመተኛትዎ በፊት ሎሽን በመጠቀም ቆዳዎን በአስፈለገዎ ጊዜ ለመታደግና ፈጣን እፎይታን ለማግኘት ይችላሉ፡፡ ሎሽንን አዘወትሮ በቋሚነት በመጠቀም በቀዝቃዛ ወራት የሚያጡትን የቆዳ ርጥበት መተካት ይችላሉ፡፡

 

እነዚህን ቀላል፣ ግን ደግሞ ዉጤታማ ጥቆማዎችን በዕለት ተዕለት አኗኗርዎ ጥቅም ላይ ማዋል ከቻሉ ሁላችንም እንዲኖረን የምንፈልገውንና ሴቶችም ሊያዩት የሚወዱትን አይነት መልክ ዳግም የራስዎ ለማድረግ ትክክለኛውን መንገድ ተያይዘውታል ማለት ነው፡፡

ምንጭ፡-lookgoodcenter