Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

እንደ አሸን በፈሉበት በዚህ ጊዜ የሚጠቅመንን ብቻ እየመረጥን ወደ ሞባይሎ

የስማርት ስልክ አፕሊኬሽኖች

 

Image result for የስማርት ስልክ

 

 

እንደ አሸን በፈሉበት በዚህ ጊዜ የሚጠቅመንን ብቻ እየመረጥን ወደ ሞባይሎቻችን መጫን እንዳለብን ባለሞያዎች ይመክራሉ፡፡በዛሬ የአፕሊኬሽን ጥቆማችን ለአንድሮይድ የስማርት ስልኮች እጅግ ጠቃሚ ስለሆነውአንድሮይድ ሎስት (Android Lost) እናስተዋውቃችኋለን፡፡

ስማርት ስልኮቻችን ላይ የግል ፎቶዎቻችንን፣ ሚስጥራዊ ዶክመንቶችን፣ እጅግ በጣም የምንፈልጋቸውን አድራሻዎችና ሌሎችም በሌላ ሰው እጅ ላይ ቢወድቁ አደጋ ላይ ሊጥሉን የሚችሉ መረጃዎችን አስቀምጠን ይሆናል፡፡ ታዲያ አያድርስና በአንድ መጥፎ አጋጣሚ ስልካችንን ብንጥል ወይም ብንሰረቅ እነዚህን መረጃዎች እንዴት ልንታደጋቸው እንችላለን?

 

አንድሮይድ ሎስት ለእነዚህና ሌሎች ተመሳሳይ መጥፎ ኣጋጣሚዎች መፍትሔን ይዘው ብቅ ካሉ የሞባይል አፕሊኬሽኖች መካከል ይመደባል፡፡

አንድሮይድ ሎስትን ከጎገል ፕሌይ ስቶር ማግኘት የምንችል ሲሆን በድረ-ገፅ ወይም በአጭር የጽሁፍ መልዕክት አማካኝነት ስልካችንን ካለንበት ስፍራ ሆነን እንድንቆጣጠር የሚያስችለን አፕሊኬሽን ነው፡፡

የአንድሮይድ ሎስት ቱል ከሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች መካከል፡-

❒ ከስልካችን የተላኩና የገቡ አጭር የጽሁፍ መልዕክቶችን ለማንበብ፣

❒ ስልካችንን ለመቆለፍ፣

❒ ሚሞሪ ካርድ ላይ ያሉ መረጃዎችን ለመሰረዝ፣

❒ ስልካችንን በጂ.ፒ.ኤስ ወይም በኔትዎርክ አማካኝነት ያለበትን ስፍራ ለማወቅ፣

❒ ጂ.ፒ.ኤስ ለማስነሳትም ሆነ ለማቆም፣

❒ ዋይ.ፋይ ለማስነሳትም ሆነ ለማቆም፣

❒ ሲም ካርድ ሲቀየር በኢሜል ማሳወቅና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡

 

ምንጭ ፡-ኢመደኤ