ማስቲካ ማኘክ ለጤና ጠቀሜታ አለው የለውም የሚለው በርካታ ጊዜ አከራካሪ

ማስቲካን የማኘክ ጥቅሞች እና ጉዳቶች

 

 Image result for ማስቲካ

 

ማስቲካ ማኘክ ለጤና ጠቀሜታ አለው የለውም የሚለው በርካታ ጊዜ አከራካሪ ጉዳይ ሲሆን እናስተውላለን።

ማስቲካ ማኘክ ከጥንት ጀምሮ የሚዘወተር ተግባር ሲሆን፥ ግሪካዊያን የአፍ ጠረናቸውን ለማስተካከል ይጠቀሙበት እንደነበርም ይነገርለታል።

አሁንላይ ግን ማስቲካን ማኘክ በዓለማችን ላይ በስፋት የሚተገበር ሆኗል።

ታዲያ ይህ በብዙ ሰውች ዘንድ የሚዘወተረው ማስቲካን የማኘክ ተግባር ላይ በጤናው ዘርፍ የተለያዩ ሀሳቦችን የሚያስተናግድ ሲሆን፥ ይህም አንደኛው ወገን ማስቲካን ማኘክ ጠቀሜታ አለው ሲሉ በሌላኛው ወገን ያሉት ደግሞ የለም ይሀ ተግባር ለጤና ጠንቅ ነው ሲሉ ይስተዋላሉ።

እኛም ዛሬ ማስቲካ ማኘክ ያለውን ጉዳት እና ጠቀሜታዎች ልናካፍላችሁ ወደድን።

 

ማስቲካን ማኘክ የሚያስገኘው የጤና በረከቶች

ማስቲካ ማኘክ የሚያስገኘውን የጤና ጠቀሜታ ስናስቀድም፥ እንደ ፈረንጆቹ በ2013 በጃፓን የተካሄደው ጥናት እንደጠቆመው ማስቲካን ማኘክ የአእምሮ ንቃታችን በ10 በመቶ ከፍ እንዲል ያደርጋል ይላል።

 

ይህም ማስቲካ አዘውትረን የምናኝክ ከሆነ የምናስብበትና ነገሮች ላይ በተሻለ መልኩ ውሳኔ ለመስጠት ያስችለናል።

ማስቲካ በምናኝክበት ጊዜ አእምሯችን ውስጥ የደም ዝውውሩ እንዲፋጠን በማድረግ ከስምንት የማያንሱ የአእምሯችን ክፍሎች እንዲነቃቁ ማድረግ ያስችላልም ተብሏል።

በተለይም በፈተና ወቅት ማስቲካን ማኘክ አእምሯችን እንደነቃቃ ስለሚያደርግ በተሻለ መልኩ ፈተናውን የመስራት እድላችንን ከፍ ሊያደርግልን ይችላል ሲሉም ጥናቱን ያካሄዱ ተመራማሪዎች ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ማስቲካን ማኘክ የአፍ ውስጥ ጤናን ለመጠበቅ ያስችላል የተባለ ሲሆን፥ ይህም የድድ ማበጥ፣ መቁሰል እና መድማት እንዳያጋጥመን ይረዳናልም ተብሏል።

እንዲሁም ለጥርሳችን ጤንነት እና ጥንካሬ ማስቲካን ማኘክ ይመራል።

 

ማስቲካን ማኘክ የሚያስከትለው ጉዳት

በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት ተብሎ የሚነገርለትን ማስቲካ የተለያዩ ተመራማሪዎች በበኩላቸው የለም የለም ማስቲካ በጤናችን ላይ ጉዳት ያስከትላል ይሉናል።

ይህንን ሲያብራሩም ማስቲካን አዘውትረው የሚያኝኩ ሰውች በማስቲካ ምክንያት ለተለያዩ ችግሮችም ይጋለጣሉ ሲሉም ይሰማሉ።

በተለይ ማስቲካን አዘውትረው የሚያኝኩ ሰውች ማስቲካ የምግብ ፍላጎት እንዲጨምር ስለሚያደርግ ከልክ ላለፈ ውፍረት የመጋለጥ እድላቸው የሰፋ ነውም በለዋል።

በሌላ በኩል ማስቲካን አዘውትሮ ማኘክ ያልተመጣጠነ የመንጋጋ ጡንቻ እንዲኖረን ያደርጋል ሲሉም ተናግረዋል።

በተለይ ማስቲካን በአንድ የቅጣጫ ማለትም በአንደኛው የመንጋጋ ክፍላችን ብቻ አዘውትረን የምናኝክ ከሆነ ለከፍተኛ የመንጋጋ መገጣጠሚያ ችግር እንድንጋለጥ ያደርገናል በለዋል።

በተጨማሪም አዘውትረን ማስቲካን የምናኘክ ሰዎች አየር ወደ ሆዳችን ሳይቋረጥ እንደይገባ እድል ስለሚከፍት ለሆድ መነፋት እና ለሌሎች የሆድ ህመም ችግሮች ያጋልጠናልም ይላሉ።

ስለዚህም ከማስቲካ የሚገኘውን ጠቅም ለማጘኘት ማስቲካን ሁሌም አዘውትረን ከማኘክ ይልቅ የምናኝክበትን መጠን በመቀነስ የአፋችን ውስጥ ጤንነት መጠበቅ እና የአእምሯችንን ንቃት መጨመር ከማስቲካ ተጠቃሚ መሆን እንችላለንም ተብሏል።

ለዚህም ማስቲካን አዘውትሮ አለማኘክ የና የስኳርነት ወይም ጣፋጭነት ባህሪ የሌላቸውን ማስቲካወች መጠቀምም ይመከራል።

 

ምንጭ፦ stethnews.com

 

 

 

  

Related Topics