በፍፁም ችላ ሊሏቸው የማይገቡ 7 የጭንቀት/Depression ምልክቶች

የጭንቀት/Depression ምልክቶች

ከ 10 አሜሪካወያን አንዱ በጭንቀት/Depression / በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ ሊጠቃ እንደሚቸል ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ በተመሳሳይም ይህ ችግር በተለያዩ ሀገራት ባሉ ሰዎች ላይ ሊከሰት የሚችል እና መጠኑ ከቦታ ወደ ቦታም በመጠኑ ይለያያል፡፡ አብዛኛዎቹ የችግሩ ተጠቂዎች ችግሩ እንዳለበቸው የሚያውቁበት አጋጣሚ አነስተኛ ነው፡፡ የጭንቀት/Depression  ምልክቶች ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ የሚለያዩ ሲሆን እነዚህም ድካም፣ ውጥረት እና የማርጀት አዘማምያዎች ናቸው፡፡

በዋናነትም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ምክቶች ከ ጭንቀት/Depression  ጋር በተያያዘ በእርስዎ ወይንም በአቅራብያዎ ባለ ሰው ላይ ሲመለከቱ በፍጹም ችላ ማለት የለቦትም፡፡

 

1-ቶሎ መቆጣት/Irritability

ከጭቀት ጋር በብዛት የሚነሳው ተስፋ መቁረጥና ሀዘን ቢሆንም ከዚሁ በማይተናነስ መልኩ የብስጩነት እና መቆጣት ሁኔታ ከፍተኛ መሆን እና መደጋገም  የሚታይብዎት ከሆነ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ሳያውቁ እየተጠቁ ሊሆን ስለሚችል በፍጥነት  ጊዜ ወስደው ራስዎን ይመርምሩ፡፡

 

2 -ከእንቀልፍ ጋር የተገናኙ ችግሮች

ለአንድ ወይንም ሁለት ምሽቶች የእንቅልፍ አለመተኛት ወይንም መዘበራረቅና እረፍት ማጣት ችግርን ከጭንቀት ጋር ላይገናኝ ይችላል፡፡ የሁንና ለተራዘመ ጊዜ እንቀልፍ መተኛተ አለመቻል ወይንም ለረጅም ጊዜ በእንቅልፍ የማሳለፍ ሁኔታ ውስጥ ካሉ ልብ ሊሉ እና ሁኔታው ከጨንቀት ጋር ሊገናኝ ስለሚችል ራስዎን መመልከት አስፈላጊ ይሆናል፡፡

 

3- ህመም

ሰውነታችንና አእምሮአችን ተቆራኙ ተግባራትን ያከናውናሉ፡፡ በመሆኑም በአእምሮአችን ላይ ለሚፈጠሩ ችግሮች ሰውነታችን የተለያዩ ምላሾቸን ይሰጣ፡፡ ከነዚህም አንዱ በከፍተኛ ጭንቀት እና ውጥረት ውስጥ መሆን ነው፡፡ ስለሆነም በግልጽ ባቃ ምክንያት የጀርባ ህመም፣ ራስ ምታት እና የጡንቻዎች ሀመም ሚስተዋሉ ከሆነ ጊዜ ወስደው ሁኔታውን ሊያጤኑት ይገባል፡፡

 

4- የአቅም ማጣት/ የድካም ስሜት

ጭነቀት የሀይል ማጣትና የድካም ስሜት እንዲሰማ በማድረግ የእለት ተአለት ተግባር ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል፡፡ ይህም በብዛት እቅልፍ ስላልተኛሁ ወይም ስራ ስለበዛብኝ ነው በሚል ችላ ሊባል ይችላል፡፡ ልብ ሊሉት እና ትኩረት ሊሰጡት የሚገባው ጉዳይ ድካም የሚሰማዎት ከወትሮው በተለየ መልኩ ከሆነ፣ ከቀድሞ ይልቅ ለሚሰሩት ስራ ረዘም ያለ ጊዜ ሚወስድብዎት ከሆነ እና ሌላ የድካም ምክንያት ካላስተዋሉ ጭንቀት በከፍተኛ ደረጃ እየጎዳዎት ስለሆነ አፋጣኝ እርምጃ ሊወስዱበት ይገባል፡፡

 

5- የጥፋተኝነት ስሜት

አላስፈላጊ የሆነ የጥፋተኝነት ስሜት እና ጸጸትን የሚያስተናግዱ ከሆነ ይህ ስሜት የጤንነት ስሜት አይደለም፡፡ በሕይወትዎ በተከሰቱ ነገሮች በሙሉ ወይንም በአብዛኛው ራስዎን ሚወቅሱ ከሆነ እና በጸጸት የሚሰቃዩ ከሆነ ቆም ብለው ያስቡ፡፡ ዋና ምክነያቱ የነገሮችዎ አለመሳካት ወይም አጣሁ ሚሉት ነገር ሳይሆን ጭንቀት ሊሆን ስለሚችል ቆም ብለው ያስቡበት፡፡

 

6- Recklessness /  ለአደጋ አጋላጭ ባህርያት

እጅግ ደስተኛ እና ተጫዋች ባህርይ እና ወጣ ያለ ሊባል ሚችል ደማቅ ባህርያት በብዛት በውስጣቸው ጭንቀትና መረበሽ የሚታይባቸው ሰዎች ባህርያት ናቸው፡፡ አዘውትሮ ቁማር መጫወት፣ ልቅ የሆነ ወሲብ፣ የአደንዛዝ እጽና ጫት ተጠቃሚነት አስጨናቂ ስሜቶችንና ሀሳቦችን መሸፈኛ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በቅርብ በሚያውቁት ሰው ወይንም በራስዎ ላይ እዲህ አይነት ወጣ ያለ ባህርይ/አዝማምያ ካዩ ይህ የጊዜአዊ ከጪንቀት መደበቅያ ዘዴዎች እና በሂደትም ወደ ከፋ ደረጃ የሚሸጋገር ስለሆነ እና በቀጣይም ስር ወደ ሰደደ ጭንቀት እና የአእምሮ ህመም ስለሚያጋልጥ በጊዜ መፍትሄ ሊፈልጉለት ይገባል፡፡

 

7- ትኩረት የማጣት ችግር

በስራ ወይንም በውሉዎ ላይ ትኩረት ለማድረግ የሚቸገሩ ከሆነ እና ነገሮች ጨፍግገው ሚታዩዎተ ከሆነ ይህ የጭንቀት/Depression  ምልክት መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡ በጭንቀት ውስጥ ያሉ ሰዎች በብዛት የመዘንጋት እና እቃዎችን የት እዳደረጉ የመርሳት ምልክቶች በስፋት ይታይባቸዋል፡፡ ምንም እንኳን ከጊዜ ወደ ጊዜ ከቴከኖሎጂ ጋር በተያያዘ ነገሮችን የማስታወስ ችሎታ ሊቀንስ ቢችልም በስራዎ ላይ ትኩረት ማጣት እና የውጤታማነት መቀነስን ካስተዋሉ ይህ የጭንቀት ምልክት ስለሆነ ትኩረት ሊሰጡት እና በጊዜ አስፈላጊ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል፡፡

ጭንቀት/Depression  ሊታከም ወይም ሊድን የሚችል የአእምሮ ሁኔታ ሲሆን አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ እርምጃ ካወሰድን ወደ ጤና መታወክ ደረጃ ስለሚደርስ የአእምሮ ጤናዎን ትኩረት ሊሰጡት እና ባለሙያ ወይም ለረዳዎ የሚችል ሰው ሊያገኙ ይገባል፡፡

Source: psychologytoday

 

  

Related Topics