ልናስወግዳቸው የሚገቡ ጎጂ ልማዶች በመፀዳጃ ቤት ስልክ መጠቀም

ልናስወግዳቸው የሚገቡ ጎጂ ልማዶች በመፀዳጃ ቤት ስልክ መጠቀም

 

 Image result for toilet

 

በመፀዳጃ ቤት ስልክ መጠቀም፦

በዚህ አምድ ስር ያልተገቡ የምንላቸውን ልማዶች የምንዘረዝር ሲሆን፤ ልማዶቹ ያላቸውን ጎጂ ጎን እና እንደአስፈላጊነቱ ከልማዶቹ መላቀቅ እንዴት እንደሚቻል ሳይንሳዊ የሆኑ መላዎችን እንጠቁማለን።

ስልክን በመፀዳጃ ቤት የመጠቀም ልምድ የብዙዎቻችን እንደሚሆን ይታመናል። በመፀዳጃ ቤት ውስጥ የሚኖረንን አጭር ቆይታ  እንደባከነብን በመቁጠር ስልካችንን የመነካካት እና አልፎ አልፎም ጌም የመጫወት ልማድ ሊኖረን ይችላል።

ይህ ልማድ መቅረት ያለበት በሁለት መሰረታዊ ምክልያቶች ነው። በቅድሚያ ጀርሞች ስልካችን ላይ እንዲገኙ የሚያደርግ ሲሆን ከመፀዳጃ ቤት ከወጣን በኋላ እጆቻችንን በሳሙና እንኳ የታጠብን ቢሆን መልሰን በጀርም የተሞሉ እንዲሆኑ እናደርጋለን።

በሰገራ መውጫ አካላችን ላይ የሚደርስ ጉዳት (Hemorrhoids)

በሁለተኛነት ይህ ስልክን በመፀዳጃ ቤት ውስጥ መጠቀም ረዥም ቆይታ እዚያው እንዲኖረን ስለሚያደርግ በሰገራ መውጫ አካላችን ላይ የማይገባ ግፊት እንዲፈጠርና ለከፋ የጤና ቀውስ እንድንጋለጥ መንስኤ ይሆናል። በዚህ ልማድ የተጠቃን እንደሆነ መፍትሔው ወደ መፀዳጃ ቤት ስንገባ ስልካችንን ይዘን ባንገባ ይመከራል።

ምንጭ፡-http://selamall.com/

 

  

Related Topics