Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

የእጅ ጣታችን ርዝመት ስለ ማንነታችን ወይም ባህሪያችን ይገልፅ ይሆን

የእጅ ጣታችን ርዝመት ስለ ማንነታችን ወይም ባህሪያችን ይገልፅ ይሆን?

 

 

ከዚህ በታች የምንመለከታቸው ምስሎችም የቀለበት ጣታችንና ሌባ ጣታችን ያላቸውን ርዝመት በማነፃፀር ባህሪያቶቻችን ለማወቅ ያስችላሉ ተብሏል።

ምስሎቹ በጣታችን ርዝመት መሰረት A, B እና C በሚል የተቀመጡ ሲሆን፥ እርስዎም የጣትዎን ርዝመት በመመልከት በየትኛው እንደሚመደብ ከለዩ በኋላ ከዚህ በታች የተቀመጡት መግለጫዎች ከተጨባጭ ማንነትዎ ጋር ይስማማሉ አልያም ይቃረናሉ የሚለውን እንዲመለከቱ ጋብዘናል።

 

1) A

የቀለበት ጣት ከሌባ ጣት መብለጡን የሚያሳይ ነው - ምስል “A”።

በዚህ ምድብ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች የቆንጆ ተክለሰውነት ባለቤት መሆናቸው ይነገራል።

ሌሎች ሊያገኙት የሚጓጉለትን ነገር በቀላሉ ለማግኘት እንደሚችሉም ነው መረጃው የሚያመላክተው።

በተጨማሪም እጅግ በጣም ተናዳጅና ለውሳኔ የፈጠኑና አደጋን ለመቀበል የማይፈሩ ናቸው ተብሏል።

አብዛኞቹ ወታደሮች፣ ኢንጂነሮችና ቼዝ ተጫዋቾች ሲሆኑ የቃላት ድርደራ ጨዋታዎችን በመጫዎት የሚያህላቸው የለም።

የቀለበት ጣታቸው ከሌባ ጣታቸው የሚረዝም ሰዎች አጭር የቀለበት ጣት ካላቸው ሰዎች ይልቅ የተሻለ ገቢ እንደሚያገኙም ሳይንቲስቶች አረጋግጠዋል።

 

2) B

በዚህ ምስል ላይ እንደምንመለከተው የቀለበት ጣት ከሌባ ጣት የሚያጥር ሲሆን፥ አጭር የቀለበት ጣት ያላቸው ሰዎች ከፍተኛ በራስ የመተማመን የተላበሱ መሆናቸው ይነገራል።

ራስ ወዳድነትና ትእቢት ቢጤ የሚያጠቃቸው እንደሆኑም መረጃው ይገልፃል።

ብቻቸውን መሆን የሚያስደስታቸው ሲሆን በእረፍት ስአታቸው መረበሽን አጥብቀው የሚጠሉ ናቸውም ተብሏል።

በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ለመግባት ይፈራሉ የተባሉት ይህ አይነት የጣት አወቃቀር ያላቸው ሰዎች፥ በሌሎች ሰዎች እይታ ውስጥ መግባትን ግን የሚያደንቁና በጣም የሚፈልጉ ናቸው።

 

3) C

ይህ ምስል ደግሞ የቀለበት ጣትና የሌባ ጣት እኩል መሆናቸውን የሚያሳይ ነው።

ሌባ ጣታቸውና የቀለበት ጣታቸው እኩል የሆኑ ሰዎች ሰላም ወዳድ እና ፀብና አለመረጋጋት ባለበት ቦታ ድርሽ ማለት የማያሹ ናቸው።

እነዚህ ሰዎች ለነገሮች ትኩረት የሚሰጡና የተቀናጁ ሲሆኑ፥ ከበርካታ ሰዎች ጋር በቀላሉ የመግባባት ብቃት አላቸው።

ለፍቅር ግንኙነትም ታማኝና ቅን ልቦና ያላቸው መሆኑ የሚነገር ሲሆን፥ አመለ ሸጋና ለፍቅር አጋራቸው እንክብካቤ የሚያበዙና የሚጠነቀቁ አይነት ሰዎች ናቸው።

እስኪ እርሶም ይሞክሩትና ማንነትዎን ይገልፃል አይገልፅም የሚለውን ያረጋግጡ።

 

ምንጭ፦ http://www.healthylifetricks.com/