የእከክ መፍትሄዎች

 

እከክ የሚሳክኩ ጥቃቅን ሽፍታዎች በሰውነት ላይ እንዲወጣ ሲያደርግ፣ በእብጠቶች መካከል ጠቆር ያሉ የመርፌ ጫፍ የሚመስሉ ቅርፊቶችይታያሉ። እከክ በተለይ በልጆች ላይ የተለመደ ሲሆን፣ አብዛኛውን ጊዜ በጣትና በጣት መካከል፣ በእጅ አንጏ፣ በወገብና በአባላዘር ብልት አካባቢ ይታያል። መነሻው ጥቃቅን የሆኑ ነፍሳት ቆዳን በስተው ሲገቡ ነው። አንድ የቤተሰብ አባል ከተያዘ በጣም ተላላፊ በመሆኑ ሁሉም ቤተሰብ መታከም ይኖርበታል። ንጽህና በጣም አስፈላጊ ነው። መላ ሰውነትን ታጥቦ በቀን አንድ ጊዜ ልብስን መቀየር ተገቢ ነው። ልብሶች የአልጋ ልብስ ጭመር ታጥበው ፀሃይ ላይ መሰጣት ይኖርባቸዋል። የብረትም ይሁን የእንጨት አልጋዎች በነጭ ጋዝ ማጠብ ያስፈልጋል።

የቤት ውስጥ መፍትሄዎች

 • ነጭ ጋዝ (ፓራፊን) እና የአትክልት ዘይት

 
 
 
  1. አንድ ኩባያ ነጭ ጋዝ ከአንድ ኩባያ የአትክልት ዘይት ጋር በመደባለቅ ማዘጋጀት።
  2. በቀን  2 ጊዜ ለ2 - 3 ቀናት ሰውነትን በሞላ ታጥቦ እከኩ በሚታይበት አካባቢ መቀባት።
  3. ይህ ህክምና በማንኛውም የጥገኛ ትሎች ለሚመጣ የሚያሳክክ ነገር ጥሩ ሲሆን፣ ማሳከኩን አስታግሶ ትሎቹን (ወደ ሌላ የሰውነት አካል እንዳይዛመቱ) ይከላከላል።
 • የነጭ ሽንኩርት ዘይት
 
 
 
   1. አንድ የሾርባ ማንኪያ በትንሹ የተከተፈ ሽንኩርት ማዘጋጀት።
   2. ነጭ ሽንኩርቱን ከ2 የሾርባ ማንኪያ የአትክልት ዘይት ጋር በብርጭቆ ውስጥ መቀላቀል።
   3. በቀዝቃዛ ቦታ (2 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ የሙቀት መጠን ባለበት ቦታ) ማስቀመጥ (ለሶስት ዎራት አስቀምጦ መጠቀም ይቻላላ)።
   4. የነጭ ሽንኩርቱን ዘይት በሽታው ባለበት ቦታ ላይ ማሸት።
 
ምንጭ      
የተፈጥሮ መድኃኒት ሕክምና በምድር ወገብ ሞቃታማ አካባቢ (በዶ/ር ዲቴር ሹሞል ፤ ትርጉም:- በተሾመ ነጋሽ ካሣየ )

 

  

Related Topics