Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

‹‹ያዢልኝ ቀጠሮ ቦታ ምረጪና

 

 

ወይ ሐረር ወይ ሸገር አጫውቺኝ ነይና›› እያለ ከምድር ባቡር ጋር አስተሳስሮ በሚጫወተው ዜማው እንዲሁም ‹‹አይሽ አይሽና ይመጣል እንባዬ››፣ ‹‹እንዲያው ጉም ጉም››፣ ‹‹መልካም ልደት›› ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በደሴ ወይዘሮ ስሂን ትምህርት ቤት የሙዚቃ ባንድ ጋር በመሆንና ሙዚቃ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በመጫወት ወደ ጥበቡ የዘለቀው ድምፃዊና ጊታሪስት መስፍን፣ በተለያዩ ሙዚቃ ቤቶች 22 ካሴቶች ማሳተሙ ይነገርለታል፡፡

 

መስፍን ሕይወቱን ‹‹የመንፈስ አረቄ የነፍስ እህል ውኃ›› እየተባለች ከሚነገርላት ሙዚቃ ጋር ብቻ አላቆራኘም፡፡ የአድማጮችን ኅሊና የሚኮረኩሩ ብሂልን ከባህል ያዛመዱ፣ ነውን ከነበር የሚያጣቅሱ ሥራዎቹን በሙዚቃው ብቻ ማስተላለፍ አልተወሰነም፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ትውልድን ለማነፅ እንደ አባቶቹ አርዓያነት ያለውን የአስተማሪነት ሙያን በመፍቀድና ከመምህራን ትምህርት ኮሌጅ በመዝለቅ ሙያውን ጨብጧል፡፡ ሲያስተምር፣ ሲያዜም፣ ጊታር ሲጫወት ኖሯል፡፡

 

አስተማሪነቱ የቀለም ትምህርት ብቻ አልነበረም፡፡ በዘመኑ ወጣት ከነበሩ አሁን አንጋፋ ድምፃውያን ዕውቀቱን አልነፈጋቸውም፡፡ አንዱ ማሳያ የታዋቂው ድምፃዊ ንዋይ ደበበ ምስክርነት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበር ድረ ገጽ ላይ እንደተመለከተው፣ ‹‹ድምፃዊ ንዋይ ደበበ ዜማዎችን ሲፈጥር በፉጨትና በእንጉርጉሮ ሲሆን፣ ከአንድ ወቅት በኋላ በቦክስ ጊታር እየተጫወተ የሚያቀነቅነውን ዝነኛ ድምፃዊ መስፍን አበበ ለሥራ ወላይታ በመጣ ጊዜ የማግኘት ዕድሉ አጋጥሞት፣ ለዜማ መለማመጃ የቦክስ ጊታር አጨዋወት እንዳስተማረው ይታወቃል፡፡››

 

ከአባቱ አቶ አበበ ወልደ ማርያምና ከእናቱ ከወ/ሮ ወይንሸት ተሾመ በ1944 ዓ.ም. የተወለደው መስፍን አበበ፣ በአሥራዎቹ ዓመታት በተማረው ሙያ በድምፃዊነትና በሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋችነቱ እንዲሁም በመምህርነቱ ይታወሳል፡፡

 

ባደረበት ድንገተኛ ሕመም ግንቦት 25 ቀን 2008 ዓ.ም. በ64 ዓመቱ ያረፈው ድምፃዊና መምህር መስፍን፣ ሥርዓተ ቀብሩ በማግስቱ በብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን እኩለ ቀን ላይ ተፈጽሟል፡፡

 

ድምፃዊ፣ ሙዚቀኛና መምህር መስፍን ባለትዳርና የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነበር፡፡

 

ምንጭ፡-ሪፖርተር ጋዜጣ