Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ሮዝመሪ(የጥብስ ቅጠል) በውስጡ የያዘው ካርኖሶል የተባለ ንጥረ ነገር ካን??

የጥብስ ቅጠል የጤና ጥቅሞች

 

Image result for የጥብስ ቅጠል የጤና ጥቅሞች

 

ካንሰርን ይከላከላል

ሮዝመሪ(የጥብስ ቅጠል) በውስጡ የያዘው ካርኖሶል የተባለ ንጥረ ነገር ካንሰርን የመከላከል አቅም እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

✔የማስታወስ ችሎታን ይጨምራል

ከጥንት ጀምሮ ስለዚህ ጥቅሙ የሚነገርለት የጥብስ ቅጠል በውስጡ የያዘዉ ካርኖሲክ አሲድ የአንጎል ነርቮችን የመጠበቅ አቅም ስላለው በህመም ወይም ከእድሜ ጋር በተያያዘ ምክንያት ለሚመጣ የመርሳት ችግር እንዳንጋለጥ ይረዳል፡፡

✔የማይግሬን ህመምን ያስታግሳል

የጥብስ ቅጠልን በሞቀ ውሃ ዉስጥ በመጨመር ለ 10 ደቂቃ መታጠን ማይግሬን ህመምን ያስታግሳል፡፡

✔የፀረ ባክቴሪያነት ጥቅም

ጥናቶች እንደሚያሣዩት ከሆነ የጥብስ ቅጠል እንደ ጨጓራ ባክቴሪያ (H. pylori) እና ሌሎችንም ይዋጋል፡፡

✔ የአፍ ጠረንን ለማስወገድ

የጥብስ ቅጠል ተፈጥሮአዊ የሆነ የአፍ ጠረን ማስወገጃ ነዉ። ትንሽ የጥብስ ቅጠልን በሞቀ ዉሃ ዉስጥ አድርጎ መጉመጥመጥ መጥፎ ጠረንን ያስወግዳል።

✔የቆዳ መሸብሸብን ይከላከላል

የጥብስ ቅጠል በተለያዩ የቆዳ ማለስለሻ ክሬሞች ዉስጥ የሚገባ ሲሆን ቆዳን እንዳየሸበሸብ እና ጤናማ እንዲሆን ይረዳል።

✔በሽታን የመከላከል አቅምን ያዳብራል

የጥብስ ቅጠል በዉስጡ ያለዉ አንቲ ኦክሲደንት፣ አንቲ ኢንፍላማቶሪ እና አንቲ ካርሲኖጄኒክ ንጥረ ነገር የሰዉነታችንን በሽታ የመከላከል አቅምን እንዲዳብር ይረዳል።

በአብዛኛው ጠቀሜታዉ የሚያመዝነው የጥብስ ቅጠል ነፍሰጡር ሴቶች እና የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች ግን በብዛት እንዲወስዱ አይመከርም።

ምንጭ፡-በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር