የሐሞት ጠጠር በሐሞት ከረጢት ውስጥ ወይንም ሐሞትን ከጉበት ወደ አንጀት

የሐሞት ጠጠር እንዴት ይከሰታል?

የሐሞት ጠጠር በሐሞት ከረጢት ውስጥ ወይንም ሐሞትን ከጉበት ወደ አንጀት በሚወስዱት ቱቦዎች ውስጥ የጠጠር ክምችት ሲኖር ነዉ፡፡

✔ ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች ምንድን ናቸዉ?

• ከ40 – 50 የዕድሜ ልክ ውስጥ ያሉ ሴቶች

• ነፍሰ ጡር

• ወፍረት

• ቅባታማ ምግቦችን ማዘዉተር

• ስካር ህመም

• በአጭር ጊዜ ክብደትን መቀነስ ናቸዉ

✔ የሐሞት ጠጠር ህመም ምልክቶች

የሐሞት ከረጢት ጠጠር ለረዥም ጊዜ የሕመም ስሜትን ሳያስከትል ሊቆይ ይችላል፡፡

ሐሞት የሚወጣበት ቱቦ በሐሞት ጠጠር በሚዘጋበት ጊዜ በቀኝ ጎናችን የላይኛው ክፍል ላይ እየመጣ የሚመለስ ወይም የማያቋርጥ የሕመም ስሜትን ያስከትላል፡፡

የሐሞት ጠጠር ሕመም ወደ ጨጓራ እና ወደ ቀኝ ትከሻና ጀርባ የመሠራጨት ባሕሪም አለው፡፡ የህመም ስሜቱ የቅባት እህል ከተመገብን በኋላ መባባስ ከጨጓራ ሕመም እንደንለየው ይረዳል፡፡

• ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ

• ምግብ ያለመፈጨት እና የመክበድ ስሜት

• ማስገሳት

• ሆድ የመንፋት ስሜት

• የምግብ ፍላጎት መቀነስ

ከዚህ በተጨማሪ

• የዓይን እና የቆዳ ቀለም ቢጫ መሆን

• ሰውነት ማሳከክ

• የሽንት ቀለም ቢጫ መሆን

• የሰገራ ቀለም መቀየር

• በሰውነት ላይ ቀያይ ነጠብጣብ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡

✔ የሐሞት ጠጠር መፍትሔው ምንድን ነው?

አብዛኛውን ጊዜ ምንም ዓይነት የህመም ስሜት ስለማያስከትል የሕክምና ዕርዳታ ላያስፈልገዉ ይችላል፡፡ ነገር ግን የሕመም ስሜትን ካስከተለ የቅባት ምግቦችን መመገብ ማቆም እና የሕመም ማስታገሻ መድኃኒቶችን መውሰድ ለጊዜው የሕመም ስሜትን ያስታግሳል፡፡

የሐሞት ጠጠር በሐሞት ቱቦ ውስጥ በመቀርቀር የሐሞት መስመርን የሚዘጋ ከሆነ የቀዶ ጥገና መማድረግ ጠጠሩን ማስወገድ ተገቢ ነው፡፡

 

ምንጭ : Dr honeliat

 

  

Related Topics