Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

በሄደበት ቦታ ሁሉ አብሮት የመሚዞር ሀሪ የተባለ ሹፌርም ነበረው፡፡

አንስታይንና ሹፌሩ

 

Image result for አንስታይን

 

አልበርት አንስታይን የrelativity theoryን ለሳይንስ ካበረከተ በኋላ በተለያዩ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች እየተዘዋወረ ሌክቸር ይሰጥ ነበር፡፡ በሄደበት ቦታ ሁሉ አብሮት የመሚዞር ሀሪ የተባለ ሹፌርም ነበረው፡፡ ሀሪ እንያንዳንዱን ሌክቸር ሲከታተል ኖሯል፡፡

 

አንድ ቀን ከሌክቸር በኋላ ሀሪ “ፕሮፌሰር አንስታይን፤ የ relativity ሌክቸሮችህን ለበርካታ ጊዜያት ተከታትያለሁ፡፡ እድሉ ቢሰጠኝ ያለምንም እንከን እንደማቀርበው እርግጠኛ ነኝ” አለው፡፡ አንስታይንም “በጣም ጥሩ፡፡ እንግዲያውስ በሚቀጠውለው ሳምንት ወደ ዳርትማውዝ እናቀናለን፡፡እዚያ ማንነቴን ጠንቅቀው ስለማያውቁ እኔን መስለህ ማቅረብ ትችላለህ፡፡ እኔም ሀሪ እሆናለሁ፡፡”

 

እንደታሰበው ሀሪ ያለምንም ስህተት በግሩም ሁኔታ ትምህርቱን አደረሰ፡፡ አንስታይንም ሹፌሩን መስሎ ሲከታተል ቆየ፡፡ ልክ በንግግሩ መጨረሻ ላይ አንድ ተመራማሪ የተወሳሰበና ለመመለስ ጥልቅ የሂሳብ እውቀት የሚጠይቁ ጥያቄዎችን አዥጎደጎደበት፡፡

 

ሀሪም በዚህ ጊዜ “የዚህ ጥያቄ መልስ እጅግ በጣም ቀላል ነው፡፡ ስለሆነም ሹፌሬ እንዲመልሰው እድሉን ልስጠው፡፡” አለ ይባላል፡፡

 

ምንጭ – puffun.com