የአእምሮ ህክምና ጥናቶች በጭንቀት የሚሰቃዩ ሰዎች ለሱሰኝነት ይበልጥ ተ

ጭንቀት እና ሱሰኝነት

 

Image result for ጭንቀት እና ሱሰኝነት

 

ጭንቀት ማለት በስሜትም ሆነ አካለዊ በሆነ መንገድ ሰውነታችን ጠንካራ የአእምሮ ኬሚካሎችን(neurochemicals) እና ሆርሞኖችን ለማመንጨት የሚገደድበት ሁኔታ ነው፡፡ ይህም ኬሚካላዊ ለውጥ ሰውነታችን ጭንቀት የፈጠሩብንን ነገሮችን እንድንቋቋም ያግዘናል፡፡

 

ጭንቀት የተለያዩ ደረጃዎች አሉት

የአጭር ጊዜ ጭንቀት ፦ ይህ ደረጃ ሰውነት ምቾት የማይሰማበት እና ድንገተኛ የሆነ መፍዘዝ እና ጥሞና የሚስተዋልበት ነው።

የረዥም ጊዜ ጭንቀት፦ የዚህ መንስኤ የሚባሉት ጠንከር ያሉ እክሎች፤ ለምሳሌ ህመም፣ ፍቺ፣ ወይም የቅርብ ሰው በሞት መለየት ወዘተ ሲሆን አደገኛ የጤና ቀውስ እስከማስከተል የሚያደርስ ነው። ድንገተኛ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥር ክስተቶች (ለምሳሌ የተፈጥሮ አደጋ፤ አመጽ ወይም  የሽብር አደጋ) post-traumatic stress disorder ያስከትላል።

የአእምሮ ህክምና ጥናቶች በጭንቀት የሚሰቃዩ ሰዎች ለሱሰኝነት ይበልጥ ተጋላጭ እንደሆነ ያሳያሉ

 

ጭንቀት እና የሰውነታችን ግብረመልስ

በጭንቀት  ወቅት የሰውነታችን  የበሽታ መከላከል ስርዓት፣ የአእምሮ ክፍል እንዲሁም የልብ እና የደም ዝውውር  ስርዓቶች ምላሽ ይሰጣሉ።

አእምሮ በሚጨነቅበት ጊዜ  ሰውነታችን አካላዊ የሆነ (የልብ ምት መጨመር፤የእጅ መዳፍ ማላብ እና ከባድ ራስ ምታት) ምላሽ ይኖረዋል።ይህ በጊዜያዊነት የሚሰጥ ምላሽ  ሲሆን በዘላቂነት ግን  እንደ ጀርባ ህመም፣የደም ግፊት፣ የእንቅልፍ ማጣት እና ለውሳኔ መቸገር አይነት ችግሮችን ያስከትላል። በተደጋጋሚ በጭንቀት ውስጥ መሆን በሰውነት ውስጥ ከፍተኛ የጭንቀት ሆርሞኖች ምርት እንዲኖር በማድረግ የጤና ቀውስ ያስከትላል።

 

በጭንቀት ጊዜ ሰውነታችን CFR ይሚባል ሆርሞን ያመነጫል፡፡ አንዳድ እፆችም በተመሳሳይ መልኩ CFR እንዲመነጭ ያደርጋሉ፡፡

 

ጭንቀትን መቆጣጠር

ጭንቀት ከልክ እንዳያልፍ መቆጣጠር የምንችለው ነገር ነው። ጥረትን ግን ይጠይቃል፡፡ ጭንቀትን ለመቆጣጠር ከሚያስችሉ ነጥቦች መሃከል፦

 

ራስን መንከባከብ፦

ጤናማ የአመጋገብ ስርዓት፣ መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እና በቂ የእረፍት ጊዜ ማበጀት

 

ትኩረት ማድረግ፦

በህይወት ለሚገጥሙ ችግሮች ተገቢውን  ትኩረት መስጠት፡፡ እራስን ሳያስጨንቁ ቀስበቀስ ችግሮችን መፍታት

 

እውነታን መቀበል፦

ያቀዱት ነገር ካልተሳካ ለሚቀጥለው ሙከራ ዝግጅት ማድረግ አልያም ትኩረትን ወደ ሌሎች እድሎች ማዞር

 

መወያየት፦

ጥሩ አድማጭ ከሆነና ለችግሩ መፍትሄ ሊሰጥ ከሚችል ሰው ጋር መወያየት

በአደንዛዥ እፆች ውስት ራስን ከመደበቅ ይልቅ በጤናማ መልኩ ጭንቀትን መቆጣጠር እጅግ እስፈላጊ ነው፡፡

የአደገኛ ዕጽ  ሱሰኝነት  እውነታዎች እና  ልማዳዊ  አመለካከቶች

 

ልማዳዊ  አመለካከት 1 – አደንዛዥ እፆችን መጠቀም ለጤና ጠንቅ ነው ነገር ግን ከጭንቀት ያድናል

እውነታው – አብዛኞቹ እፆች ጨንቀት ሰውነታችን ላይ የሚፈጥረውን አይነት ለውጥ ይፈጥራሉ፡፡ ብሎም የረጅም ጊዜ ሰሰኝነት ይበልጥ ለጭንቀት ተጋላጭ ያደርጋል

 

ልማዳዊ  አመለካከት 2 – ሁሉም ጭንቀት መጥፎ ነው

እውነታው- ከመጠን ያላለፈ ጭንቀት ችግሮችን ለመፍታት ሊረዳ ይችላል፡፡ ነገር ግን ለረጅም ጊዜ በጭንቀት ውስጥ መኖር የስነልቦናም ለአካላዊ ጤናም አስጊ ነው፡፡

 

ልማዳዊ  አመለካከት 3 – ሁሉም ሰው ጭንቀቱን በተመሳሳይ መንገድ ያስተናግዳል

እውነታው- ሁሉም ሰው እንደየማንነቱ ከጭንቀት ለመላቀቅ ይሞክራል

 

የጥናት ግኝቶች

National institute on drug abuse ባደረገው ጥናት ጭንቀት እና የአደገኛ ዕጽ  ሱሰኝነት     ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለ ያሳያሉ። ጭንቀት  ከአደገኛ ዕጽ  ሱሰኝነት ጋር በሚመሳሰል ሁኔታ ጤና ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። ከዚህም በተጨማሪ ጭንቀት የሚያጠቃቸው ሰዎች በቀላሉ ለሱስ ተጋላጭ ሲሆኑ ከሱስም በቀላሉ መላቀቅ ያዳግታቸዋል።

ምንጭ፡-studentethiopia

 

  

Related Topics