የኢንተርኔት አጠቃቀሞችን ቀለል የሚያደርጉ አቋራጭ ስልቶች

 የኢንተርኔት አጠቃቀሞችን ቀለል የሚያደርጉ አቋራጭ ስልቶች

 

 

ማውስ ማንቀሳቀስ ሳያስፈልገን የኪቦርድ ቁልፎችን ብቻ በመጠቀም የኢንተርኔት አጠቃቀማችን ቀላል እና ፈጣን ማድረግ እንችላለን፡፡

አዲስ ድህረ ገፅ ለመክፈት

በተለምዶ አዲስ የድህረ ገፅ አድራሻ ለመክፈት http:// ወይም www አስቀድመን እንፅፋለን፡፡

 

ይሁን እንጂ የምንፈልገውን ድህረ ገፅ ስም ብቻ ፅፈን ብቻ <Ctrl> እና <Enter> በአንድ ጊዜ ስንጫን http:// ወይም www ከፊት እንዲሁም “.com” ከኋላ በራሱ ጨምሮ ወደ ድረ ገፁ በቀላሉ መግባት ያስችለናል፡፡

 

የድረ ገፁ አድራሻ መጨረሻው “.org” ከሆነ የፈለግነውን ድረ ገፅ ፅፈን  Ctrl + Shift + Enter፤ በ“.net” የሚያልቅ ከሆነ ደግሞ Shift + Enter ወደምንፈልገው ድረ ገፅ እንድንገባ ያግዘናል፡፡

 

ከአንድ አምድ ወደ ሌላ አምድ ለመሸጋገር

በኢንተርኔት የተለያዩ ቅፆችን በምንሞላበት ጊዜ ከአንዱ አምድ ወደ ሌላ ለመሸጋገር Tab ቁልፍን መጠቀም እንችላለን፡፡

ወደ ኋለኛው አምድ ለመመለስ ደግሞ Shift + Tab አቋራጭ ነው፡፡

አዲስ ታብ ለመክፈት – Ctrl + T

የተከፈቱ ታቦችን ለመዝጋት  – Ctrl + W

ከአንዱ ታብ ወደ ሌላ ታብ ለመሄድ – Ctrl + Page Up ወይም Ctrl + Page Down

በቅርቡ የዘጋናቸውን ታቦች እንደገና ለመክፈት – Ctrl + Shift + T

በድረ ገፆች ላይ የፊደላትን መጠን ለመጨመር Ctrl ከዚያም + ፤ ለመቀነስ Ctrl እና – ፤ የፊደላቱን መጠን ወደ ነበረበት ለመመለስ Ctrl ከዚያም 0

መረጃዎችን በአዲስ ገፅ ለመክፈት (Opening link in a new tab) – ልንከፍተው የፈለግነውን ርዕስ ላይ Ctrl ተጭነን ክሊክ ማድረግ፤ ወርድ ላይ ከሆነም የምንፈልገውን የድረ ገፅ አድራሻ በሙሉ መርጠን Ctrlን ተጭነን በመያዝ በአዲስ ገፅ መክፈት እንችላለን።

የተጣራ ፍለጋ ለማድረግ – የምንፈልገውን ጉዳይ በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ ማስገባት

ለምሳሌ፦ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ብለን ጎግል ላይ ብንፈልግ ስለ ኢትዮጵያ አልያም ስለ ኢኮኖሚ የተለያዩ ጉዳዮችን በዝርዝር ያመጣልናል።

 

ይሁን እንጂ “የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ” ብለን ብንፈልግ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ብቻ የተመለከቱ መረጃዎችን ማግኘት እንችላለን።

የድህረ ገፅ አድራሻ መፃፊያ ስፍራን በአጭሩ ለማግኘት –  Alt + D ወይም F6

ጠቃሚ ድህረ ገፆችን ለሌላ ጊዜ ለማስቀመጥ ወይም ቡክማርክ ለማድረግ – Ctrl + D + Enter

ከዚህ ቀደም ያስቀመጥናቸውን የድረ ገጽ አድራሻዎች ለማግኘት – Ctrl + B

ገፆችን እንደ አዲስ በድጋሚ ለመክፈት (refresh ለማረግ)- Ctrl + Shift + R

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማስቆም እና ለማጫወት – K

ምንጭ፦ techworm.net, Fanatech

 

  

Related Topics