10 በስፋት ጥቅም ላይ የዋሉ የይለፍ ቃላት (Passwords)

10 በስፋት ጥቅም ላይ የዋሉ የይለፍ ቃላት (Passwords)

 

Image result for (Passwords)

 

የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች የማስታወስ ችሎታ አነስተኛ መሆን አልያም ለደህንነታቸው ብዙም አለመጨነቃቸው በተደጋጋሚ ጊዜ ተመሳሳይ እና አጭር የይለፍ ቃሎችን እንዲጠቀሙ ማድረጉ ይነገራል።

ምንም እንኳን ያለፈው የፈረንጆቹ 2015 አመት በሳይበር ጥቃት ከፍተኛ ሪከርድ የተመዘገበበት ቢሆንም የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች አሁንም የይለፍ ቃላቸውን “123456” አድርገዋል የሚል መረጃ ወጥቷል።

 

123456ን የይለፍ ቃል (ፓስወርድ) ማድረግ አደገኛ መሆኑን የሚያውቁም ጭምር አሁንም ይጠቀሙበታል ተብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ “password”፣ “football” እና “baseball” የሚሉ የይለፍ ቃላትም በበርካቶች ዘንድ ጥቅም ለይ እየዋሉ ያሉ የይለፍ ቃላት መሆናቸውን ነው ስፕላሽ ዳታ የተባለ ድርጅት ያወጣው ጥናት የሚያሳየው።

ድርጅቱ ለ5ኛ ጊዜ ባወጣው የጥናት ውጤት በ2015 በምዕራብ አውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካ በርካታ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ከሚገለገሉባቸው የይለፍ ቃላት ውስጥ “123456” እና  “Password” እንደ ከዚህ ቀደሙ ቀዳሚዎቹ ናቸው።

የስፖርት እና ፊልም ርዕሶችም በቀላሉ የሚታወሱ በመሆናቸው የበርካታ ሰዎች ምርጫ እየሆኑ መምጣታቸው ተነግሯል።

 

በ2015 በስፋት ጥቅም ላይ የዋሉ የይለፍ ቃላት ደረጃ

  1. 123456
  2. password
  3. 12345678
  4. qwerty
  5. 12345
  6. 123456789
  7. football
  8. 1234
  9. 1234567
  10. baseball

አብዛኞቹ የይለፍ ቃላት ቁጥሮች ብቻ መሆናቸው በቀላሉ ለመረጃ ዘራፊዎች እንደሚያጋልጣቸውም ተመልክቷል።

ይህ ሁኔታ ከቀጠለም የመረጃ መዝባሪዎች እና የሳይበር ጥቃት ለሚያደርሱ አካላት የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን በቀላሉ እንዲያጠምዱ ያግዛቸዋልና ተጠንቀቁ ተብሏል።

 

ምንጭ፦ www.techworm.net/

 

  

Related Topics