በሞባይሎ ኢንተርኔት ሲጠቀሙ ሂሳቦ በቶሎ እንዳያልቅ ማድረጊያ ዘዴ

 በሞባይሎ ኢንተርኔት ሲጠቀሙ ሂሳቦ በቶሎ እንዳያልቅ ማድረጊያ ዘዴ

 

Image result for mobil internet

 

ይቺ ኢንተርኔት የሚሏት ነገርከመጣች እና የእነ Facebook, Viber ምናምን ቡዳ ከበላን ጀምሮ እኮ ስልካችን እንደ ቀዳዳ ኪስ ሳንቲም ይዛ ማቆየት ተሳናት ጎበዝ። እናማ ይሄ ነገር ከእኔ አልፎ ብዙ ወዳጆቼን ሲያስመርር ባስተዋልኩ ጊዜ የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ተሰማኝና ጥናቴን አካሄድኩ።

 

አሁን ባለኝ መረጃ መሰረት ፍራንካችንን ከስልካችን ዘርፈው የሚያሸመጥጡት ዋነኛ ምክንያቶች ሁለት ናቸው፤ አንደኛው fraud call የሚሉት ነገርዬ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ background data roaming ነው። ከዚህ በመቀጠል ስለሁለቱ ምንነት እና እንዴት ችግሩን መፍታት እንደምንችል እናያለን።

 

Fraud call፦ ማለት በእኛ ስልክ ውስጥ ባለ ሂሳብ እኛ ሳናውቀው ሌሎች (hackers) ሲጠቀሙበት ማለት ነው። ይሄ ሂደት ብዙ ጊዜ በእኛ ሃገር የሚፈጠር ባይሆንም አንድ አንድ ጊዜ እንደሚከሰትአስተውያለሁ፤ ስልኮ በ fraud call ሲጠቃ በራሱ ጊዜ ወደማያውቁት የውጪ ስልክ ቁጥር ይደውላል ነገር ግን የተደወለውን ቁጥር call register ውስጥ ማግኘት እንዲሁም ባትሪውን ከልነቀሉት በስተቀር ጥሪው እንዲቋረጥ ማድረግ አይቻልም ስለዚህ እርሶ ሳያውቁ ስልኮን በኪሶ ወይም በቦርሳዎ ውስጥ አስቀምጠው ብሮትን ወስዶ ያለምንም መረጃ ይጠፋል ማለት ነው። fraud call የሚደወልበትን ቁጥር ለማወቅ ግድ ስልኮትን ማየት የሚችሉበትን ቦታ ማስቀመጥ ይኖርቦታል ወይንም ኢር-ፎን ሰክተው ሙዚቃው ሲቋረጥ ወዲያውኑ ስልኮ ለይ የሚታየውን ስልክ ቁጥር መመዝገብ ይኖርቦታል በመቀጠልም ወደ ቴሌ በመደወል የመዘገቡትን ቁጥር በማሳወቅ መፍትሄ ማግኘት ይችላሉ።ስልኮ በ fraud call መጠቃቱን እርግጠኛ ለመሆን ካርድ ከሞሉ በኋላ ለተወሰነ ጊዜ ያክል ምንም ጥሪ ሳያከናውኑ እና ኢንተርኔት ሳይከፍቱ በመታገስ የስልኮ ሂሳብ መጉደል አለመጉደሉን በማየት ማረጋገጥ ይቻላል።

 

Background data፦ ይሄ በአብዛኛው/ሁሉም ማለት ይቻላል የ Android ስልክ ተጠቃሚዎች ጋር የሚስተዋል ሲሆን ብዙዎቻችን ግድ ሳንሰጠው ስልካችን ኢንተርኔት ሲከፈት automatically sync የሚያደርገው data ብዛት እኛ ከምንጠቀመው በ 7 እና 8 እጥፍ ካርዳችን እንዲቆረጥ ያደርጋል ይህንን ለማስተካከል የሚከተለውን ቀላል step በመከተል ማስተካከል ይቻላል

 

1. የስልኮን setting ይክፈቱ

2. በመቀጠልdata usage የሚለውን icon ይጫኑ

3. Mobile data የምትለዋን box check ያድርጉ( የስልኮን ኢንተርኔት ያብሩ)

4. እዚሁ ገፅ ላይ እያሉ ወደታች ዝቅ ያድርጉት፤ ስልኮ ኢንተርኔት የሚጠቀሙ applicationችን በቅደም ተከተል ያሳዮታል ይህ ማለት ከላይ የተቀመጠው application ብዙውን ሳንቲሞትን የሚወስደው ነው ማለት ነው።

5. እዚህ ላይ ከሚታዮት ዝርዝሮች መሃል ብዙ Mega Bite የሚጠሙትን በየተራ በመጫን እና ወደታች በመውረግ restrict background data የሚለውን box check ያድርጉ።

 

ብዙ ጊዜ Google play store, Instagram, Google services የመሳሰሉት applications ብዙ data ስለሚጠቀሙ restrict ማድረጉን አይዘንጉ። ነገር ግንእነ viber,2go,whatsapp የመሳሰሉትን የቻት ማድረጊያ applicationች restrict ባያደርጓቸው ይመረጣል ምክንያቱም ከሌላ ሰው የተላከሎትን ሚሴጅ applicationኑን ካልከፈቱት በቀር automatically ለእርሶ እንዳይደርስ ስለሚገታው ነው። ማንኛውም አይነት ጥያቄ ካሎት ከታች ካለው ክፍት ቦታ ላይ comment ያድርጉ እኔ በአፋጣኝ መልስ ለመስጠት እሞክራለሁ፤ቸር ይግጠመን አመሰግናለሁ።

 

ምንጭ፡-studentethiopia

 

  

Related Topics