የብርቱካን ልጣጭ አለም እስካሁን ከደረሰችባቸው የኮሌስትሮል መድሃኒቶች

የብርቱካን ልጣጭ አለም እስካሁን ከደረሰችባቸው የኮሌስትሮል መድሃኒቶች ይልቅ ጠቀሜታ አለው ተባለ

 

 Image result for orange

አንድ ጥናት ከእንግሊዙ Research Institute of London and Ontario እንደሚያሳየው ከሆነ በብርቱካን ልጣጭ ላይ ያለው nobiletin የተሰኘው ተፈጥሯዊ ንጥረ ነገር ከፍተኛ የሆነ የኮሌስትሮልን መጠን ከማንያውም ሰውሰራሽ መድሃኒት በተሻለ መልኩ እንደሚቀንስ ያሳያል።

ጥናቱ ከጉበት የሚመረቱትን VLDL እና LDL  የተሰኙ  በሰውነት ውስጥ ያለውን ኮሌስትሮል ለማዘዋወር የሚረዱ ኘሮቲኖችን በመቀነስ እና በዚህ ንጥረ ነገር አማካኝነት የሚፈጠረውን  እጅግ ከፍተኛ የሆነ የኮሌስትሮልን መጠን መቀነስ እንደሚቻል ያሳያል።

ይሄው የብርቱካን ልጣጭ በይዘት 70% ያህሉ የተፈጥሮ ዘይት ሲሆን በውስጡም ባሉት limonene እና linalool በተባሉ ንጥረ ነገሮች አማካኝነት ረቂቅ ተዋህሲያንን በአጥጋቢ ሁኔታ ማጥፋት ይቻላል፤  ይህም ብቻ አይደለም free radicals የተሰኙ ካንሰርን ጨምሮ ሌሎች ሜታቦሊክ ችግሮችን ሊያመጡ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችንም በአግባቡ እንዲወገዱ ይረዳሉ።

የሚገርመው ሃቅ ግን ይህ አይደለም፤ የብርቱካን ወይም የመንደሪን ልጣጭ ይሄን ሁሉ ጥቅም እየሰጠ ስላልጣፈጠ ብቻ በአመት ከ700,000 ቶን በላይ በቆሻሻ መልክ ይወገዳል።

ምንጭ፡-ethiohakim.net

 

  

Related Topics