የመርሳት በሽታን በእጅጉ ይከላከላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የአንጎል ህዋ

15 የአፕል [የቱፋህ] የጤና በረከቶች

 

Image result for አፕል [ቱፋህ]

1. ጤናማና ነጭ ጥርስ እንዲኖሮት ያስችላል፡፡

2. የመርሳት በሽታን በእጅጉ ይከላከላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የአንጎል ህዋሳትን እርጅና በመዋጋት የማስታወስ ችሎታን ያነቃቃል፡፡

3. የተለያዩ የነቀርሳ ህመሞችን ይዋጋል፡፡

4. አፕልን መመገብ በስኳር በሽታ የመያዝ ዕድልን ይቀንሳል፡፡

5. የኮልስትሮል መጠንንም ይቀንሳል፡፡

6. ለልብ ጤንነትም ይረዳል፡፡

7. የፓርኪንሰን በሽታን ይከላከላል፡፡

8. የሀሞት ጠጠር እንዳይፈጠር ይረዳል፡፡

9. ተቃራኒ ለሚመስሉት ለተቅማጥና ድርቀትም ፍቱን መድሀኒትነቱ ይነገርለታል፡፡ ይህም በአፕል ውስጥ ያለው ፋይበር የተመጠነ ውሀ በመምጠጥ ብቃቱ ሳቢያ የተከሰተ ነው፡፡

10. ከሆድ ህመም ይከላከላል፡፡

11. የኪንታሮት በሽታ አንዳይከሰት ይከላከላል፡፡

12. ለበርካታ የጤና ጠንቆች ምክንያት የሆነውን የክብደት መጨመርንም ይከላከላል፡፡ አፕል በፋይበር የዳበረ ስለሆነ አፕልን የምንመገብ ከሆነ ከፍተኛ የካሎሪ መጠን ያላቸውን ምግቦች መመገብ አያሻንም፡፡

13. በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ሰውነታችን የሚገባውን መርዛማ ንጥረነገሮች የሚያጣራውን ጉበታችንን በማጣራት ከፍተኛ ግልጋሎት ይሰጣል፡፡

14. የሰውነትን በሽታ የመከላከል ብቃት ያጠነክራል፡፡

15. ዓይንን ከካታራክት እንደሚከላከልም በቅርብ ጊዜያት የተከናወኑ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡

ምንጭ፡-By Fillaah Ibnu Falaah

 

  

Related Topics