በቂ እንቅልፍ አግኝተው ሲነሱ የሚሰማ የመንፈስ እርጋታ እና ሰላም በሌላ

የእንቅልፍ ጥቅሞች

 

በቂ እንቅልፍ አግኝተው ሲነሱ የሚሰማ የመንፈስ እርጋታ እና ሰላም በሌላ በምንም ሊተካ የማይችል ነው። የሰው ልጅ በቀን ውስጥ ከ6-8 ሰአት የሚሆነውን ግዜ በእንቅልፍ ማሳለፍ እንዳለበት ተደጋግሞ ይነገራል። እንቅልፍ ሰውነታችን እና አእምሮአችን የሚያርፍበት የጤናማ ህይወት አካል እንደሆነ የሚያስረግጡት ባለሙያዎች በቂ እንቅልፍ በመተኛት የሚገኙ ጥቅሞችን ዘርዝረዋል።

• የማስታወስ ችሎታን ማዳበር :- ተኝተን ለምን ህልም እንደምናይ ባለሙያዎች እስካሁን ያልደረሱበት ቢሆንም በእንቅልፍ ግዜ አእምሮአችን በውስጡ የያዘውን መረጃ የማሰባሰብ እና የማስተካከል ስራ ይሰራል። ፋይሎችን ቦታ ቦታ እንደማስያዝ ማለት ነው። በዚህ ግዜ ነው እንግዴ ነገሮችን ማስታወስ አለማስታወሳችን የሚወሰነው።
• ረጅም እድሜ ለመኖር :- የልባችንን አሰራር በማጎልበት ፣ ሰውነት ውስጥ ያለ የኬሚካል ብዛት በማመጣጠን እና አጠቃላይ ህይወታችንን በጥሩ መልኩ በመጨመር እድሜን ከእንቅልፍ ጋር ያጣጥሙት።
• የፈጠራ ችሎታን ማሻሻል :- ድርሰት ለመጻፍ ብዕሮን ከማንሳትዎ በፊት ወይም ስዕል ለመሳል ብሩሽ ከመጨበጥዎ በፊት ጥሩ እንቅልፍ ቢያገኙ ይመረጣል።
• ንቃትን መጨመር :- በቂ እንቅልፍ አለመተኛት እንዴት እንደሚያንገላጅጅ ያቁታል መቼም።
• ጥሩ የሰውነት ክብደት :- ክብደት ለመቀነስ የምግብ ቁጥጥር ወይም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ መጀመር ካሰቡ በቂ እንቅልፍ ማግኝተትንም ከሚደረጉ ነገሮች ዝርዝር ውስጥ ያስገቡ።
• ጭንቀትን መቀነስ :- በዚህ ወከባ በበዛበት ውስብስብ አለም ውስጥ በእንቅልፍ በሚገኝ እርጋታ ጭንቀትዎን ይቀንሱ።
• ሰውነትን መጠገን :- ሰውነታችን በእንቅልፍ ግዜ ብዙ ፕሮቲኖችን በማምረት የተጎዱ ሴሎችን ይጠግናል

ምንጭ፡- .alifradio.

 

  

Related Topics