ብስክሌት አዲስ አበባ ከተማ የገባው በ1893 ዓ.ም. ነው

ብስክሌት

 

Image result for ብስክሌት

 

 አዲስ አበባ ከተማ የገባው በ1893 ዓ.ም. ነው። የመጀመሪያዋ ብስክሌት አዲስ አበባ እንደገባች ምኒልክ ዘንድ ቀረበች። ዳግማዊ አፄ ምኒልክም ብስክሌቷን ተመልክተው ‹‹… ከአሻንጉሊት ትንሽ ሻል ትላለች::…›› ማለታቸውንና ነድተው እንዲያሳዩዋቸውም መጠየቃቸውን ጉኦዶሮፕ ጽፏል። ምኒልክ የብስክሌቷን አነዳድ ከተመለከቱ በኋላ ተደንቀው ‹‹ያልገባኝ ነገር እግር ከመወዛወዝ ካለረፈ ድካሙ ምን ቀረለት›› አሉ። የዕለቱ ዕለትም አነዳድዋን አስተምሩኝ ብለው ካባቸውን ጥለው ልምምድ መጀመራቸውን ቪክቶር ጉኦዶሮፕ ጽፎላቸዋል::

 

ምንጭ፡-ሪፖርተር