የጨጓራ ህመም በሆድ እቃ ክፍል አካባቢ ደጋግሞ የሚከሰት የማያቋርጥ ቁርጠ

ጨጓራ ህመምን እንዴት እንከላከል

 

Image result for ጨጓራ ህመም

 

የጨጓራ ህመም በሆድ እቃ ክፍል አካባቢ ደጋግሞ የሚከሰት የማያቋርጥ ቁርጠት ሲሆን ህመሙ ወደ ጎን አጥንት አካባቢም ጨምሮ ሊሰማ ይችላል፡፡

ብዙን ጊዜ የሚከተሉት ምልክቶች ከአንድ እና ሁለት በላይ ሆነው ሊታዩ ይችላሉ፡-

 - የሆድ ቁርጠት(በላይኛው የሆድ ክፍል ላይ) 

 - ማቅለሽለሽና ማስመለስ

 - ማስጋሳት

 - እምብርት አካባቢ የሚሰማ ህመም 

 - ሆድ መንፋት

 - ምግብ በሚወሰድበት ጊዜ ቶሎ መጥገብ

 

ብዙብዙ መንስኤዎችም እንደ ምክኒያትነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡-

-  ምግብ በጨጓራ ውስጥ ብዙ ጊዜ ሲቆይና የHCL አሲድ መጠን እየጨመረ ሲመጣ       

-  ጨጓራ ከመጠን በላይ ሲለጠጥ 

-  በ H.Pylori ባክቴሪያ አማካኝነት 

-  በተያያዥ የውስጥ ደዌ ምክንያቶች 

-  በPsychological ጭንቀት፣ ድብርትና ውጥረት ዋናዋናዎቹ ናቸው፡፡

 

ወደ ህክምናው ስንመጣ፡-

1. አንድ ሰው የጨጓራ ህመም ብቻ እንደሆነ ህመሙ ማወቅ በራሱ ትልቅ እረፍት ይሰጣል፤ ነገርግን ደጋግሞ የሚከሰተውን ህመም ለማስቀረት የሚቀሰቅሰውን ምክንያት ማወቅ ተገቢ ነው፡፡     

ደጋግሞ የሚሰማ ጭንቅት፣ድብርት እና የአእምሮ ውጥረት ካለ የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት ማማከር ተገቢ ይሆናል፡፡

2.  ሌላው ደግሞ የምግብ ማስተካከያ ማድረግ ነው ይህም ሲባል፡- ቅባትነት ያልብዛበት ምግብ መመገብ፣ በአንድ ጊዜ ብዙ ምግብ ከመውሰድ ይልቅ በመጠን አነስ ያለ ምግብ ቶሎ ቶሎ መውሰድ እና ብዙ ጊዜ ጨጓራ ህመም የሚከሰቅሱ ምግቦችን ማስወገድ ያካትታል፡፡ 

3. ተገቢውን የጨጓራ መድሃኒት ከሃኪም ዘንድ መውሰድ 

4. የጨጓራ ህመም የሚያመጣው H.Pylori ካለ መድሃኒቱን ለታዘዘው ቀን ያህል መውሰድ 

5. እንዳስፈላጊነቱ ሌሎች ተጨማሪ መድሃኒቶች ከሃኪም ዘንድ ሊታዘዝ ይችላል፡፡

 

ምንጭ፡-.ethiohakim

 

  

Related Topics